>
5:13 pm - Wednesday April 19, 5228

የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት ማን ነው?!? (አቻምየለህ ታምሩ)

የኦሮሞ ሕዝብ ጠላት ማን ነው?!?
አቻምየለህ ታምሩ
 
* …በጠላት ቁጥጥር ስር ወድቆ ማንነቱን እንዲያጣ፤ ቋንቋው፣ ታሪኩና ባሕሉ ተረስቶ ከሰው በታች ለመኖር እድሉ ሆኖ እንዲቆይ የተደረገው የኦሮሞ ህዝብ….?  ዶ/ር አብይ አሕመድ
ዐቢይ አሕመድ በኦሮምኛ ባደረገው ንግግር «የኦሮሞ ሕዝብ [ላለፉት 150 ዓመታት] በጠላት ቁጥጥር ስር ወድቆ ማንነቱን እንዲያጣ፤ ቋንቋው፣ ታሪኩና ባሕሉ ተረስቶ ከሰው በታች ለመኖር እድሉ ሆኖ ቆይቷል» ሲል ሕዝባዊ ንግግር  አድርጓል። ይገርማል!  እውነታው በኢትዮጵያ ታሪክ በነገድ ላይ  ላይ የተመሰረተ የቋንቋ፣ የነገድ፣ የማንነትና የባሕል ማጥፋት በተሳካ ሁኔታ ያካሄዱት የኦሮሞ አባገዳዎች ብቻ ናቸው። ለዚህ ደግሞ የኦሮሞ የራሱ ትውፊትና አፈ ታሪኩ  የታሪክ ምስክር ነው።
ኦሮሞ ሲስፋፋ ይከተል የነበረውን ፍልስፍና ከመዘገቡ የታሪክ ፀሐፊዎች መካከል አቶ ምስጋናው በላቸው በዳሴ አንዱ ናቸው። አቶ ምስጋናው  በላቸው በዳሴ  የጨቦ ሰው ሲሆኑ  ኦሮሞ አካባቢያቸውን ወርሮ ቋንቋና ባሕላቸው አጥፍቶ በኃይል ኦሮምኛ እንዲናገሩ ካደረጋቸው የኢትዮጵያ ነገዶች መካከል አንዱ የሆነው የክስታኔ  ጉራጌ ነገድ አባል ናቸው።
አቶ ምስጋናው  በላቸው “የጨቦ ኡዳደየሱስ ሕዝብ አጭር ታሪክና ባሕል” በሚል በመጋቢት 1985 ዓ.ም. ከጀርመን በጻፉት የታሪክ መጽሐፋቸው ኦሮሞ በገዳ ስርዓት እየተመራ የጉራጌን ምድር ሲወር የነበረውን ጥፋትና የተከተለውን ፍልስፍና  እንዲህ ይገጹታል፤
“…በዚህ ጊዜ [ኦሮሞ ወደ ግራጌ ምድር በተስፋፋበት ወቅት ማለታቸው ነው] ስለ ቋንቋ የነበረው እምነት ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ” የሚል ሆነ። ትርጉሙም ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ” ማለት ነው።”
ዐቢይ አሕመድ ላለፉት 150 ዓመታት በጠላት ቁጥጥር ስር ወድቆ ማንነቱን እንዲያጣ፤ ቋንቋው፣ ታሪኩና ባሕሉ ተረስቶ ከሰው በታች ለመኖር እድሉ ሆኖ ቆይቷል የሚልለት ኦሮሞ  በገዳ ሥርዓት እየተመራ “ኦሮምኛ የሚናገር ወገናችን ነው ይገብር፤ ኦሮምኛ የማይናገር ጠላታችን ነው ይጥፋ” በሚል  ርዕዮተ ዓለም እየተመራ ሲስፋፋ ያገኘውን የደቡብ ኢትዮጵያ  ሕዝብ ቋንቋ፣ ባሕልና ማንነት በተሳካ ሁኔታ ያጠፋውንና  ከርስቱ  አፍልሶ ሌላውን በገዛ መሬቱ  ላይ ገርባ ወይም  ባሪያና ጭሰኛ አድርጎ ለዘመናት ሲጨቁን የኖረውን ሕዝብ ነው።
ኦነጋውያን ደብተራ የሚሏቸው ሰዎች የጻፉት ታሪክ ሳይሆን የኦሮሞ የራሱ ትውፊትና አፈ ታሪክ የሚነግረን ታሪክ ቢኖር ተገዶ ኦሮምኛ  እንዲናገር ይደረግ እንጂ  ከቦረና ውጭ ያለው ጎሳ ሁሉ ኦሮሞ እንዳልሆነ ነው! እውነተኞቹ ኦሮሞዎች  ኦሮሞ አንጋፋ የሚላቸው ወራሪዎቹ አባገዳዎቹና የነሱ ዘመዶች ብቻ ናቸው። የተቀረው  ኦሮምኛ ተናጋሪ  እንዲሆን የተደረገው ኦሮሞ አልነበረም፤ ኦሮምኛ ግን በአባገዳዎች ተጭኖበት  በግድ እንዲናገር ተደርጓል።
ኦሮምኛ የሚናገር “ቢርመዱዳ እንጡቂና” ኦሮምኛ የማይናገር “ዲና በሌሣ” ከሚለው የኦሮሞ አባ ገዳዎች ርዕዮተ ዓለም በተጨማሪ ከቦረና ውጭ ያለው ኦሮሞ ላለመሆኑ ተጨማሪ የኦሮሞዎች የራሳቸው አፈ ታሪክ ምስክር ነው። በኦሮሞ ትውፊት “Salgan Borana, sagaltamman Garbaa” የሚል አፈ ታሪክ አለ። ትርጉሙም «ከአስሩ ኦሮሞው አንዱ ብቻ ነው፤ ዘጠኙ ገርባ ወይም ወይም በወረራየተያዘ ሕዝብ ነው።» ማለት ነው። ዛሬ ኦሮምኛ ተናጋሪ የሆነው ሕዝብ  ቁጥሩ ጨምሮ የሚታየው የኦሮሞ ቁጥር ብዙ ስለሆነ ሳይሆን ከአስሩ መካከል አንዱ ብቻ የሆነው ኦሮሞ ወርሮ የያዛቸውን  የተቀሩትን ዘጠኙን ቋንቋቸውን፣ የነገድ ማንነታቸውንና ባሕላቸውን በተሳካ ሁኔታ አጥፍቶ የራሱን ባሕልና ቋንቋ ስለጫነባቸው ነው።
ይህ እውነት  ጀርመናዊው የታሪክ ተመራማሪ ኡልሪክ በርካምበር  ከዛሬ ሀምሳ ዓመታት በፊት በአርሲ ባካሄደው ጥናት፤ ጥሊያናዊ የታሪክ ፕሮፌሰር ኢኔሪኮ ቼሩሉ ከዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመታት በፊት በሜጫ ኦሮሞዎ ላይ ባካሄዱት ጥናት ተረጋግጧል። በዲ.ኤን.ኤ.ም ይህንን  በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። የሰላሌና የአምቦ ሕዝብ የዲ.ኤን.ኤ ውጤት ዝምድናው ከምንጃርና ወይም ጅሩ ሕዝብ ጋር እንጂ ከቦረና (እወነተኛው ኦሮሞዎች) ጋር አይደለም። የጅማ ሕዝብ ዲ.ኤን. ኤ. ዝምድናው ከየምና ከካፋ ሕዝብ እንጂ ከኦሮሞ ጋር ምንም ዝምድና የለውም። በወለጋም  እወነተኛ ኦሮሞዎች ከመቶ አስር አይሞሉም። ባጠቃላይ ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ውስጥ  ከቦረና ውጭ ያሉት እውነተኛ ኦሮሞዎቹ  ከብቶቻቸውን እየነዱ ከቦረና  ወጥተው በየአካባቢው  ለም መሬትና ውኃ ሲያገኙ ነባሩን ሕዝብ ገርባ በማድረግ አንጋፋ ሆነው የቀሩት  አባገዳዎችና የነሱ  ልጆች ዘሮች ብቻ ናቸው።
«ምኒልክ  የማንነት ጭቆና አድርሶብኛል» እያለ ሲያላዝን የሚውለው ኦሮሞ ያስገበረው ገርባ ሁሉ ግን  አይኑን ገልጦ ይህንን እንዳይገነዘብ  ያ ትውልድ ያመጣብን የመንጋ  ፖለቲካ ግርዶሽ ሆኖበታል። በመሰረቱ ሰው የመንጋ አካል አድርጎ ራሱን ሲቆጥር ወደ እንስሳነት ይቀየራል። እስከዛሬ ድረስ በጎሰኞች የተቋቋሙት ድርጅቶች ሁሉ ሰውን  እንዳያስብ አርገው ወደ እንስሣ ሲለውጡ የኖሩ ናቸው። አንዳቸውም የኢትዮጵያ የጎሳ ድርጅቶች ለሰው ልጅ  የሚመጥን ጠባይ የላቸው። የኢትዮጵያ የጎሳ ድርጅቶች ሁሉ ሰውን ባሪያ የሚያደርጉ  የባሪያ ኢንተርፕራይዞች ናቸው።  የባሪያ ፀባይ ለጌታው መታዘዝ፣ ስረቅ ሲባል መስረቅ፣ ግደል ሲባል መግደል ብቻ  ነው። የባሪያ ሌላው ተቀዳሚ ተግባር  እንደ ገደል ማሚቶ አቤት እያለ ጌታው ያለውን ሁሉ ሳይመረምር  መድገም ነው። የባሪያ የሕይወት ጥሪ የራስ ፍላጎት፤ የራስ ድምጽ አለመኖር ነው። የኛ አገር የጎሳ ድርጅቶች የሰውን ልጅ ወደዚህ አሕይነት አውርደውታል።  ለሰው የሚነጥን ስብስብ ግን ሁሉም ማሰቢያ ጭንቅላቱ ይሰራል፤ ስለሆነም እንደ አንድ ሰው አያስብም።
ባጭሩ  ኦሮሞ ዐቢይ አሕመድ እንዳለው በጠላት ቁጥጥር ስር ወድቆ ማንነቱን እንዲያጣ፤ ቋንቋው፣ ታሪኩና ባሕሉ ተረስቶ ከሰው በታች ለመኖር እድሉ ሆኖ የቆዬ ሕዝብ ሳይሆን ዛሬ ኦሮምኛ ተናጋሪ ከሆነው ሕዝብ መካከል ከዘጠና በመቶ በላይ የሚሆነውን ኦሮሞ ያልነበረ ሕዝብ  በቁጥጥሩ ስር አውሎ ማንነቱን እንዲያጣ፤ ከርስቱ እንዲነቀል፤ ቋንቋው፣ ታሪኩና ባሕ ሉ ተረስቶ ከሰው በታች እንዲኖር ያደረገ ሕዝብ ነው። ያልተበረዘው የኦሮሞ  አፈ ታሪክና ትውፊት የሚነግረን ይህንን እውነት  እንጂ ዐቢይ አሕመድ ኦነግ  በፈጠራ ታሪክ  ካጨማለቀው ፕሮፓጋንዳ ሳያጣራ ኮርጆ ሊያስተጋባው የሞከረውን የፈጠራ ታሪክ አይደለም!
___
ማስታወሻ፡ ዐቢይ በኦሮምኛ ባደረገው ንግግር ውስጥ  ባርያን ገርባ ይለዋል። ይህ የኦሮሞኛ ቃል ባለፈው ስለ በቀለ ገርባ በጻፍሁት ጽሑፍ ላይ «ገርባ» የሚለው  የኦሮምኛ ቃል ባሪያ ማለት ነው፤ በቀለ ገርባም የኦሮሞ ባሪያ እንጂ ኦሮሞ እንዳልሆነ ያወሳሁትን የሚያጠናክር ነው።
Filed in: Amharic