>

ከኤርትራውያን ጋር ለመታረቅ ለእርድ የቀረቡ የመስዋእት በጎች!!! (ወዲ ሻምበል ዘ ብሔረ ኢትዮጵያ)

ከኤርትራውያን ጋር ለመታረቅ ለእርድ የቀረቡ የመስዋእት በጎች!!!
ወዲ ሻምበል ዘ ብሔረ ኢትዮጵያ
* ከኤርትራውያን ጋር ለመታረቅ የግድ አፄ ምኒልክ ወይም የአማራ ህዝብን ለእጅ መንሻ መስዋዕት ማቅረብ አይጠበቅንህም።
የኢትዮጵያ ህዝብና የኤርትራ በተለይ ደግሞ የትግራይ ህዝብ በባህል ሆነ በቋንቋ ስለሚዛመዱ  ሰላምና እርቅ ወርዶ አብረው በመኖራቸው የሚጠላ ሰው ካለ የሰይጣን መልእክተኛ መሆን አለበት።ሆኖም ግን ከወደ ትግራይ ያሉት ጥቂት እብዶች እንደ መምህር ገብረኪዳን እና መምህር መሐሪ ዬሐንስ የመሳሰሉት ከኤርትራ ጋር ለመታረቅ ተብሎ ትላንት ሻእብያ በኢትዮጵያውያን ላይ ትህነግ በኤርትራውያን ላይ የፈፀሙት ግፍ በተለይ መለስ ዜናዊ የአይናቸው ከለር ያላማረንን እናባራርራለን ብሎ ንብረት ሐብታቸው ዘርፎ ፌስታል ተሸክመው እንዲወጡ እንዳልተደረገ ሁሉ።ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንም ንብረት ሐብታቸው ተቀምተው አንዳንዶቹም ታስረው የት እንደደረሱ የማይታወቁ ብዙ ናቸው።
ይሄ ሁሉን በደል ይቅር ለእግዚአብሔር ብሎ እንደማስታረቅ። ትላንት በአይናችን ስላየነው በደል ምንም ሳይተነፍሱ “ለእዚህ ሁሉ የዳረጉን አፄ ምኒልክ እና አማራዎች ናቸው” እያሉ በየመድረኩ ሲጮሁ ስታያቸው ምን ያህል ህሊና ቢሶች እንደሆኑ ትልቅ ማሳያ ነው። ከኤርትራውያን ጋር ለመታረቅ እኮ የግድ አፄ ምኒልክ ወይም የአማራ ህዝብን ለእጅ መንሻ መስዋዕት ማቅረብ አይጠበቅብህም እንዲሁ መታረቅ ይቻላል።
Filed in: Amharic