>

ፍየል "ለካምፋየር!!!" (መስከረም አበራ)

ፍየል “ለካምፋየር!!!”
መስከረም አበራ
እንደ መግቢያ የአይተ አብርሀ ደስታን መረጃ ላቃምሳችሁ፦ 
 ህወሓት 16 ፍየሎችን አሰረች! ይለናል….የዓረና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የተምቤን ዓብዪ ዓዲ የዓረና ፓርቲ ፅሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ ዜናዊ አስመላሽ ጥሪት የሆኑት 16 ፍየሎች በትናንትናው ቀን ነሐሴ 22, 2011 ዓም በህወሓት የታሰሩ ሲሆን 3 ፍየሎች ዛሬ ቢፈቱም 13ቱ ግን እስካሁን እንደታሰሩ ናቸው! ከሰው ወደ እንስሳ እስር Transformation መሆኑ ነው!
—–
የስልጣን ጉዳተኛው ህወሃት በስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን ለስልጣኑ መሰንበት ሲል  ብዙ ነውር አድርጓል፡፡በስልጣን ዘመኑ ሲያደርገው ከነበረው ይልቅ አሁን እያደረገ ያለው ነገር ግን  ስልጣን እንዴት “አብስ ገበርኩ” በሚያሰኝ ሁኔታ እንደሚወድ ያሳብቃሉ፡፡የስልጣን ማጣት ቁጭቱ ሆድ አንጀቱን እርር ሲያደርገው ብድግ ብሎ የስልጣን ዛር ቆሞላቸው አራትኪሎ ቤተመንግስት የገቡ የቀድሞ ታዛዦቹን ሙልጭ አድርጎ ይሳደባል፣ነገ ለስብሰባ ሲጠሩት እግሩን ነቅሎ እንደሚሮጥ እያወቀም “ከነሱ አጠገብ ብቀመጥ ሰው አትበሉኝ” ይላል፣በል ሲለው ደግሞ ‘እኔ እንዲህ ተበድየ ይቅርታ የማይጠይቁኝ ለምንድን ነው?’ ሲል የስድብ ቀላጤ ፅፎ ራሱ ቆሞ ያነባል፣ምላሹ በአራት እጥፍ ተባዝቶ በተረት ታጅቦ ሲደርሰው ከስልጣን መውረዱ፣አሽከርም ቦታ ቀይሮ ዙፋን ላይ መቀመጡ ትዝ ይለዋል-ይችን እውነት ሲያስባት እንባ እንባ ሳይለው ይቀራል?!ምን ያደርጋል እንባውን ዋጥ አድርጎ ከመቀመጥ ውጭ- ተመልሶ ደደቢት አይሄድ ነገር ዘረፋ ወለድ ምቾት ክፉኛ አለስልሶታል!
 ተገመት ቢለው እንጅ ከአዲስ አበባ ተባሮ መቀሌ ከከተመ በኋላ የሚያደርገው ነገር አንዱም ወደ ቀደመ ስልጣኑ አይመልሰውም፡፡ነገረ ስራው ሁሉ የሚያሳብቀው መቀሌ ሆኖ አዲስ አበባን ባሰበ ጊዜ እንዴት አምርሮ እንደሚያለቅስ ነው! ይህን ያሳየን ፈጣሪ ምን ይከፈለዋል?የሆነ ሆኖ የህወሃት ነገር የሞተ ነገር ሁሉ ካልተቀበረ መጠንባቱ እንደማይቀር ብቻ ያሳብቃል እንጅ የሞተ ስልጣን እንደማይዝ እርግጥ ነው! ህወሃት ተመልሶ ስልጣን ይይዝ ዘንድ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ አንድ ቀን በመጣ መብረቅ በአንዴ እልም ብሎ ማለቅ አለበት፤ያ ከሆነ ብቻ ህወሃት አብዝቶ ወደሚናፍቀው ስልጣኑ ይመለሳል!
ሆኖም ህወሃት ተስፋ አይቆርጥም፡፡እድሉ ሆኖ የእሱ ቢጤ ግራ የገባውም አያጣም፡፡ እነዚህን ከእሱ የባሱ ሰባት ጊዜ ያዞረባቸውን ቢጤዎቹን ከምድር ዳርቻ ሰብስቦ የስልጣኑን አርባ እና የሙት አመት ያበላ ያጠጣቸው ይዟል!የሙት አመት ተዝካር መሃራ ታዳሚዎቹን አሰናብቶ የደደቢት ምትክ  ወደ ሆነው አክሱም (ነው ፕላኔት) ሆቴል ሲያመራ ከሁላችን ኪስ በሰረቀው ገንዘብ ውስኪ አና ሬድሌብል ይጠጣ ዘንድ ምግብ ያስፈልገዋል፡፡ አሁን መንግስትነት ስለቀረ የያዘውን ቶሎ ቶሎ ከመብላት ይልቅ የሚዘረፍ ካለ የራስን ለነገ ማሳደር ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለውስኪ ማወራረጃ የፍየል ጥብስ ካማረው በአቅራቢያው ወደ ሚገኘው ባለጋራው ጉረኖ ገብቶ አንድ አስራስድስቱን ፍየል ነድቶ ይወጣል፤ እሳቱን አንድዶ ይጠብሳል፣መስከረም ይጠባል ያንን ሲያነክት!ገና እንደ ናቡከደነጾር ሳር ይበላል…..ከእስር የተለቀቁት ሶስቱ ፍየሎች ጥፍራቸው አለመነቀሉ ይረጋገጥ – ፍትህ ለፍየላት!
Filed in: Amharic