>

አያቶላህ ጃዋር የመለስ ዜናዊን ሌጋሲ ለማስቀጠል እየሰራ ነው!!  (ስዩም ተሾመ)

አያቶላህ_ጃዋር የመለስ ዜናዊን ሌጋሲ ለማስቀጠል እየሰራ ነው!! 
ስዩም ተሾመ
 
ዶ/ር አብይን በበቀለ ገረባ የመተካት እቅድ
አያቶላህ ጃዋር “አማራ የኢትዮጵያዊነት ጭብሉን አውልቆ የዘውግ ብሔርተኛ መሆኑ የለውጡ በጣም ጠቃሚ ስኬት መሆኑን ግልጿል። የአማራ ልሂቃን በኢትዮጵያዊነት ጭምብል የራሳቸውን ብሔር ተኮር ፍላጎት ያራምዱ እንደነበር በመግለፅ አሁን ላይ ጭብላቸው ስለወለቀ እውነተኛ ድርድር እና ውይይት ማድረግ ይችላል” ብሏል።
 እንደ ጃዋር አገላለፅ፣ ላለፉት አመታት የተካሄደው ትግል መሰረታዊ ዓላማ በህወሓት መሪነት የተዘረጋውን ጨቋኝ ስርዓት ማስወገድ አሊያም በእኩልነት መርህ ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት አልነበረም። የለውጡ ዓላማ ጨቋኝ ስርዓትን ከስልጣን በማስወገድ ዴሞክራሲያዊ መንግስት መመስረት ቢሆን ኖሮ፤ ለምሳሌ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መቅረቱ፣ የህውሓት የበላይነት ማብቃቱ፣ ራሱ ጃዋር ወደ ሀገር ቤት መምጣቱ፣ ምንም እንኳን ለጃዋር ባይዋጥለትም እንደ ዶ/ር አብይ ያለ የኦሮሞ ተወላጅ የሀገሪቱን ከፍተኛ ስልጣን መያዙ እና የመሳሰሉ ለውጦችን እንደ ስኬት መጥቀስ ይቻላል። ለጃዋር ግን ባለፉት አመታት በተካሄደው ትግል የተገኘው ትልቁ ስኬት የአማራ ልሂቃን እንደ እሱ አገላለፅ የኢትዮጵያዊነትን ጭምብል አውልቀው ጭፍን ብሔርተኛ መሆናቸው ነው። በጃዋር አስተሳሰብ የኦሮሞ ህዝብ የትግል ስኬት የሚለካው ከነፃነት፣ እኩልነትና ፍትህ አንፃር ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት ውድቀት እና የአማራ ብሔርተኝነት እድገት ነው።
በመሰረቱ በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ስር ካልሆነ በስተቀር በዘውግ ብሔርተኞች ምክክር ውይይት ሆነ ድርድር ማድረግ አይቻልም። የአማራና ኦሮሞ ብሔርተኞችን ጨምሮ በሁሉም የዘውግ ብሔርተኞች መካከል የሰከነ ውይይትና ድርድር ማካሄድ አይቻልም። ምክንያቱም የዘውግ ብሔርተኞች አቋም በራስ-ወዳድነት፥ ወገንተኝነት፥ የተጠቂነትና ጥላቻ ስሜትና አመለካከት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ እርስ በርሳቸው መግባባት ቀርቶ መደማመጥ እንኳን አይችሉም። በእርግጥ እንደ ጃዋር ያሉ የኦሮሞ ብሄርተኞች ከመቀሌ እስከ ሱማሌ ካሉ ብሔርተኞች ጋር ሲነጋገሩና ጥምረት መሳይ አጋርነት ሲፈጥሩ ይታያል። ይህ ደግሞ የሆነው ኢትዮጵያዊነት እና አማራ የጋራ ጠላት አድርጎ በማሰብ ላይ የተመሰረተ ነው። ስለዚህ ጃዋር የአማራ ብሔርተኞች አሁን የኢትዮጵያዊነትን ጭምብል ስላወለቁ መነጋገርና መደራደር ይቻላል የሚለው እሳቤ የመለስ ዜናዊን የፖለቲካ ጨዋታ ለመድገም ነው። መለስ ዜናዊ ኢህአፓን አባርሮ፣ ኢህዴንን አፍርሶ ብአዴንን ከሰራ፤ ኢትዮጵያ የምለውን አጥፍቶ ብሔረ-አማራ ብሎ በጠላትነት የፈረጀውን የአማራ ህዝብ ልክ እንደ እሱ ሆኖ የሚበቀልለትይ ድርጅት ፈጠረ። በዚህ መሰረት ከብአዴን ጋር ሆኖ የአማራን ህዝብ ከድህነት አዝቅት ውስጥ መክተቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በተመሳሳይ አያቶላህ ጃዋር የነፍስ አባቱን መለስ ዜናዊ ሌጋሲ ለማስቀጠል ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።
በነገራችሁ ላይ በዶ/ር አብይ እና አያቶላህ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ሰፊ ነው። ለምሳሌ ዶ/ር አብይ የኦዴፓ ሊቀመንበር ሆነ ጠ/ሚ ከሆነ ጃዋር ፍጹም ደስተኛ አልነበረም። መጀመሪያ ላይ “ዶ/ር አብይ በፍፁም የፓርቲው ሊቀመንበር መሆን የለበትም” የሚል አቋም ነበረው። አብይ ጠ/ሚኒስትር ከሆነ በኋላ ደግሞ የጃዋር ምርጫ እና እንቅስቃሴ በሙሉ ዶ/ር አብይን ፈንቅሎ በኦቦ በቀለ ገረባ መተካት ነው። በአጠቃላይ ጃዋር በዶ/ር አብይ ላይ ያለው ጥላቻ ከጌታቸው አስፋ አስር እጥፍ ይበልጣል። በአስተሳሰብ ደረጃ ሁለቱን የሚያስማማ ነገር ፈልጎ ከማግኘት ጌታቸው አሰፋን በቁጥጥር ስር ማዋል ይቀላል።
Filed in: Amharic