>
10:13 am - Thursday August 18, 2022

"ሰጎች"  (መስከረም አበራ)

“ሰጎች” 
መስከረም አበራ
 ሰጎች” የሚለው አባባል ራሱ መንጋ የሰውነትም የበግነትም ማንነት የያዘ ነው  “ሰው” እና  “በግ” ከሚለው ቃል የመጀመሪያውን እና የመጨረሻውን ፊደል ወስዶ የተፈጠረ ቃል ነው፡፡
 “ሰጎች”  የመንጋነት ፀባይ በርካታ ቢሆንም በጣም የማይረሳኝ “ሰጎች ለእረኛቸው ሃሳብ እስከመታረድ ይሄዳሉ እርሱ ግን እርዱም ፍርዱም አይደርሰውም ሩቅ ሆኖ የሚታረድም የሚታሰርም ተተኪ ” ሰግ መሰብሰብ ነው” ያለው ነገር ነው፡፡”
ለማንኛውም መንጋ ማለት እረኛው እንደፈለገ የሚያደርገው ሰውም በግም አይነት ተፈጥሮ ያለው ነው፡፡መንጋነት ጭንቅላትን ለማከራየት የመፍቀድ፣ራስን ዝቅ እረኛን ከፍ አድርጎ የማየት እሳቤ ነው፡፡ይህ ሰው ሆኖ መፈጠር የሸለመንንን የታላቅነት ፀጋ ካለመረዳት ራስን የመናቅ ጎስቋላ አስተሳሰብ ከእሳቤ ድህነት  እንጅ ከዘር ጋር ግንኙነት የለውም፡፡ ለዚህ ምስክሩ በሃገራችን ዳርቻ በሁሉም ጥጋጥግ የመንጋነት ዝንባሌ እና ሪኮርድ  መመዝገቡ ነው፡፡
ከሰሜን ጫፍ ተነስትን ብንጀምር አረመኔው ጌታቸው አሰፋ እኔ ነኝ ብለው ቲሸርት ለመብሰው ጎዳና ላይ ወጥተው ፎቶ ሲነሱ የነበሩ ሰዎች፣ጥናት ሊያደርጉ የሄዱ ባለሙያዎችን በድንጋይ ናዳ የገደሉ ሌሎች፣ቡራዩ ላይ ሰው ያረዱ ቢጤዎቻቸው፣ሻሰመኔ ላይ ሰው ዘቅዝቀው የሰቀሉ ዘግናኞች፣ወደ ደቡብ ስንወርድ ሃገረሰላም ላይ ሆስፒታል የገቡ የ85 አመት አዛውንት ከሆስፒታል አውጥተው ከነአስታማሚ ልጃቸው በድንጋይ በዱላ ቀጥቅጠው የገደሉ ለወሬ የማይመቹ አረመኔዎች ሁሉ መንጋዎች ናቸው፡፡
በዚህ ሁሉ መንጋነት ውስጥ ዘረኝነት እንዳለ ባይካድም፤መንጋነትን የሚፈጥረው ግን ዘረኝነት ብቻ አይደለም-ለዘረኝነት መንገድ የሚጠርገው አለማወቅ እንጅ፡፡ አለማወቅ ዘረኝነትን ፀንሳ ጨካኝነትን ትወልዳለች፡፡ ይህ ተጠራቅሞ መንጋን መሰብሰብ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ብልጥ እረኛ ደግሞ በፉጨቱ ብቻ እስከመታረድ/ማረድ በራሳቸው የጨከኑ፣ለምን እታረዳለሁ/አርዳለሁ? እረኛየስ እውነት የሚያምንበት የትግል ዓላማ ካለው ለምን ከፊት ሆኖ አይመራኝም?ለምን ያን ያህል ሩቅ ቦታ ቆሞ ያሰማራኛል? የማይሉ መንጋ ሰጎችን ይሰበስባል፡፡
የመንጋ እና የታጋይ ልዩነቱ ግልፅ ነው፡፡ታጋይ መሪ ሲኖረው መንጋ እረኛ ይኖረዋል፡፡ታጋይ መሪው ሲስት እስከመገሰፅ እና ወደመስመር ወደማስገባት ድረስ የሚሄድ የራሱ ነፍስ እና ስጋ ያለው ሲሆን መንጋ ግን እረኛው ካአፉ ቃል እስኪወጣ ጠብቆ ወደገደልም ቢሆን ለመሄድ ዝግጁ ነው፡፡ከሰሞኑ እረኛ ነኝ ባይ “ውሻ ተብለሃል ድመት ተብለሃል” ብሎ የመንዳት አባዜው ባቀበለው መጠን የብጥብጥ ድቤ ሲመታ መልስ ያለማግኘቱ ነገር በሃገራችን የመንጋነት እሳቤ እየተመናመነ እንደሄደ ተስፋ ሰጥቶኛል በበኩሌ፡፡
በተጨማሪ የአዲስ አበባ ባለደራ ኮሚቴ ከሰሞኑ መግለጫ እሰጣለሁ ሲል እኔን ጨምሮ ለወትሮው የትግል አላማው ደጋፊ የሆንን ወዳጆቼ “ምን የሚባል መግለጫ ነው?”፣ “ባላደራው እስከ መግለጫ መስጠት የሚያደርስ መሪነት በዚህ ሁኔታውስጥ ሊኖረው ይገባል ወይ?” የሚል ሃሳብ ቆም ብለን ከማሰብ እስከ መቃወም ድረስ ሄደን ነበር፡፡
ባላደራው ልክ ነው የሚሉ ወዳጆቻችንንም ሃሳብ ስናደምጥ ቆይተናል፡፡ አንድ ወዳጄ እንደውም ‘ይሄ ባላደራችን በመንገድ ሲያልፍ ያማረ ሰገነት ድንገት ካየ እንኳን እዚች ላይ ነበር መግለጫ መስጠት’ ሳይል ይቀራል ብለሽ ነው” ሲል በጋራ የምንደግፈውን የባላደራ ምክርቤት ላይ ቀልዶ አስቆኛል፡፡የባላደራው ተከታዮች መንጋ እንዳልሆንን ከብዙ ወዳጆቼ ጋር ባደረግነው ውይይት ተረድቻለሁ፡፡መንጋ ባለመሆናችን መሪው የባላደራ ኮሚቴም ካላስፈላጊ አካሄድ ተመልሷል፡፡
መንጋነት በመመናመኑ አዲሱ ዓመት ብሩህ ነው
Filed in: Amharic