>

ለፖለቲካዊ እሬቻ አንንበረከክም! (ያሬድ ጥበቡ)

ለፖለቲካዊ እሬቻ አንንበረከክም!
ያሬድ ጥበቡ
አስቀድመን እንደተነበይነው ኢሬቻ  በመስቀል አደባባይ ፖለቲካዊ ፕሮጀክት ነው። አንበረከክነው ብለው የፈከሩትም የአዲስ አበባን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ነው። መልእክታቸውም የአዲስ አበባ ባለቤትነታችንን እናሳያችኋለን ነው። እናንተን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማችሁን ይዛችሁ ክርስትያናዊ በአላችሁን እንዳታከብሩ ከልክለን እኛ ግን የኦነግን ባንዲራ ይዘን መስቀል አደባባያችሁን ብንወረው ምን እንዳትሆኑ ነው የሚል መልእክት ነው ሊያስተላልፉልን የሞከሩት። ከተማችንን በአስር ሺህ ባላገር ካድሬዎቻቸው ስለወረሩ የምንፈራቸው መስሏቸዋል።
የአዲስ አበባ ባለቤቶች የሆንነው ስድስት ሚሊዮን የከተማዋ ዜጎች ቤታችን ተቀምጠን ስላየናችሁ የፈራናችሁ እንዳይመስላችሁ። ስድስት ሚሊዮን የከተማ ነዋሪ እንኳንስ 2ሚሊዮን የኦዲፒ ካድሬን፣ 30 ሚሊዮን ገጠሬ መቋቋም ብቻ ሳይሆን መክቶ ማሸነፍም እንደሚችል ለደቂቃም እንዳትጠራጠሩ። ላሰማችሁት ፉከራ፣ ልታሰፈራሩን ላደረጋችሁት ሙከራ፣ በቁጥርና ጦርመሳሪያ ሳይሆን፣ በእውቀትና ወደር በሌለው የነፃነት ጥማት እንጋፈጣችኋለን። ልታስፈራሩን በመሞከራችሁ፣ ሃሞታችንን አኮስትራችሁታል። በድፍረታችሁ፣ ጨክነን ባለን አቅም ሁሉ እንድንቋቋማችሁ ጋብዛችሁናል። ለዚህም እናመሰግናለን።
ለሃሰት ትረካችሁና በዚህም ላነሳሳችሁት የባላገር ካድሬ ጎርፍ አንንበረከክም። የተፈበረከው ትረካችሁ በማስረጃና እውቀት ይፈርሳል። ያነሳሳችሁት ጨዋ ህዝብም ወደ ሃይማኖቱና ታሪኩ ይመለሳል። የኢትዮጵያ ሃቅም በኢትየጵያ ሰማያት ሁሉ ይረብባል፣ ወደሁሉም ጥጋጥጎች ይናኛል። “አንበረከክነው” ብላችሁ አትሳከሩ። ልታንበረክኩት የምትችሉት ነፍጠኝነት የለም። የሌለን ነገር ማንበርከክ አትችሉም።
በባላባቱና በባለጉልቱ እጅ የነበረውን መሬት ለአባቶቻችሁና አያቶቻችሁ ካከፋፈልን 45 ዓመታት ተቆጥረዋል። ነፍጠኝነትና ጋላነት በታላቁ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄና ከሱም አብራክ በወጡት መኢሶንና ኢህአፓ ትግል ከተደመሰሱ 45 ዓመታት ተቆጥረዋል። በነገራችን ላይ ነፍጠኛ ደሞዝ ሳይከፈለው የዘመተ የኢትዮጵያ ሰራዊት ነው። በደረሰበት ለሃገር ሰላምና ደህንነት ጥበቃው፣ መንግስት ደሞዝ ለመክፈል አቅም ስላልነበረው፣ አርሰው የሚያካፍሉት ጭሰኞች አድሎት ነበር። ገበሬው በሰላም አርሶና ነጋዴው በሰላም ነግዶ እንዲበላ እነዚህ ሰላም አስጠባቂ ነፍጠኞች የግድ አስፈላጊ ነበሩ። በነርሱም ተጋድሎ ነው የሃገር ሉአላዊነት ተጠብቆ የቆየው።
እነዚህ ነፍጠኞች ሰላም ከማስከበርም ባለፈ የኢትዮጵያን ከተሞች የቆረቆሩ ባለውለታዎቻችን ናቸው። ነፍጠኞቹ በያዙዋቸው ወታደራዊ ነቁጣዎች ዙሪያ ነው ሸማኔው፣ ቀጥቃጩ፣ ባለሱቁ፣ ሱቅበደረቴው፣ ባለወፍጮው፣ እብዱ፣ ኮማሪው፣ ጠጅጣይው ወዘተ ከመላ የኢትዮጵያ ጥጋጥግ እየተመመ የኢትዮጵያን ከተሞች፣ በተለይ በዛሬው ኦሮሚያ በተሰኘው ክልል ያሉትን ከተሞች የመሠረተው። ስለሆነም የከተሞች   ሥልጣኔ በማምጣትና እናንተንም ከከብት አርቢ የእንክርት ህይወት ወደቋሚ የግብርና ህይወት ስላስገባችሁ ነፍጠኛው ባለውለታችሁ ነው።  ለመሆኑ በባሪያ ንግድ ላይ ከተመሠረተው የጅማ አባጅፋር ከተማ  በቀር የኦሮሞ ብሄረሰብም ሆነ የተለያዩ ጎሳዎቹ የመሠረቱት አንዲት ከተማ መጥራት ይቻላችኋልን? አይመስለኝም። አንድ መጥራት አትችሉም። አሁንም፣ አንድም ከተማ ለመሥራትም ወኔውና ርእዩ የላችሁም። ከዚህ ውስጣዊ ባዶነታችሁና የሥራ ትጋት እጦታችሁም የተነሳ ነው፣ ሌሎች ደክመው ያካበቱትን ጥሪትና ሃብት ለመውረስ የሃሰት ትርክት፣ በሬወለደ ትንተና የምታበዙት።
ኢትዮጵያውያን በመቶዎች አመታት ጥረትና ግረት፣ አበሳና ጣር፣ ለቅሶና ላብ፣ ፍቅርና ትብብር፣ የሰሩዋቸውን ከተሞችና በውስጣቸውም የያዙዋቸውን ሃብቶች መውረስ ነው ቅዠታችሁ። ያለምክንያት አይደለም ቅዠት ያልኳችሁ፣ ህልም ሊሆን ስለማይችል ነው። እያንዳንዱን ሜትር ሳንዋጋ የምትዘርፉት አንድም ንብረት አይኖርም። እያንዳንዱ ፎቅ ላይ ሳንዋጋ ሰብራችሁ የምትገቡበት ኮንዶሚንየም አይኖርም። ከአብራካችን ያልወጣ፣ ቋንቋችንን የማይናገር ፖሊስ የማይጠብቀን ቀን ሩቅ አይደለም። ከአብራካችን ያልወጣ የቀበሌና ወረዳ አስተዳደር የማይኖርበት ቀን ሩቅ አይደለም። ከአብራካችን ባልወጣ ምክርቤት የማንተዳደርበት ቀን ሩቅ አይደለም። ከአብራካችን ባልወጣ ከንቲባ የማንገዛበት ጎህ ሩቅ አይደለም። በፖለቲካዊ እሬቻችሁ፣ ከተማችንንና ህይወታችንን አስፈራርታችሁ ልትቀሙን ማሰባችሁ እጅግ ግልፅ ሆኖልናል። አንፈራችሁም! አንንበረከክም!
Filed in: Amharic