>

አትናገሩ የተባሉ ሰዎች ሚስጥሩን በማዝረክረካቸው የኮንዶሚንየም እደላው እንደቀረ እየተሰማ ነው!!! (መስከረም አበራ)

አትናገሩ የተባሉ ሰዎች ሚስጥሩን በማዝረክረካቸው የኮንዶሚንየም እደላው እንደቀረ እየተሰማ ነው!!!
መስከረም አበራ
ዛሬ የለውጥ አመራሩ ከህወሃት የተለየ ስለሆነ መግለጫ ማውጣት ብዙ እንደማያስፈልግ በግል ጭምር ሲነግሩኝ የነበሩት ኢዜማዎች ዛሬ ምን ታይቷቸው እንደሆነ ባላውቅም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ፓርቲው ያወጣው መግለጫ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ግዛት እንድትሆን መግለጫ ከወጣባት ግንኮ ሰንበትበት ብሏል፡፡ ያኔ እነሱን ጠላታቸው ዝም ይበልና ዝም የሚያደርግ ነገር ገጥሟቸው ነበር፡፡ ዝም ማለታቸው ሳያንስ የእነሱ ፓርቲ ተብየዎቹ ሊሰሩት የሚገባውን ስራ ሊሰሩ፣የአዲስ አበባ ነገር አላስችል ብሏቸው የሚጮሁ ሰዎችን እንደ ነገር ወዳድ አይተው ወቀሳ ቃጥቷቸው ነበር፡፡
 ዛሬ ዝም ካሉበት ወራት የባሰ ምን አደገኛ ነገር አዲስ አበባ ላይ ታይቷቸው እንደሆነ ባይታወቅም አዲስ አበባን የሚያነሳሳ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ህዝብ ኮንዶሚኒየም ይደርሰኛል ብሎ 13 አመት ሙሉ ሲቆብ ኖሮ በቆጠበው ገንዘቡ ማግኘት የነበረበትን ቤት መከልከሉ ሳያንስ በዛሬው እለት 500ሽህ ብር ካሳ እና 500 ካሬ ሜትር ምትክ መሬት  ለተሰጣቸው አርሶ አደሮች ጭምር ተጨማሪ የኮንዶ ሚኒየም ቤት ለመስጠት በህገወጡ ከንቲባ አቅዶ ጨርሶ እንደ ነበር ትናንት ተዘግቧል፡፡
የዘገበው  ታማኙ ምንጭ ዋዜማ ሬዲዮ ነው፡፡
ሆኖም አትናገሩ የተባሉ ሰዎች ሚስጥሩን በማዝረክረካቸው ዛሬ ለጊዜው ይሁን ለዘለቄታው እንደቀረ እየተሰማ ነው፡፡በዚህ ሰዓት ስለ አዲስ አበባ አሰብኩ ባይ አካል ይህን የአምባገነንነት፣የፍርደ-ገምድልነት፣እብሪት ዳርቻ ስለሆነው ድርጊት በግልፅ አንስቶ አቋሙን መግለፅ አለበት፡፡ ይህን የማያወራው የኢዜማ ሽኩርምም መግለጫ አላማው ምን እንደሆነ ገርሞኛል፡፡ መግለጫ ካወጡ ከልብ ማውጣት ነው ካልሆነ እንደቆዩነበት መተው ነው፤ የምን መሽኮርመም ነው!
ኢዜማ “ማንም እንዲታገልላችሁ አትጠብቁ” ማለቱ ፓርቲው  ወደ ነገስታት ሲቀርብ ከህዝብ መራቁን አመላክታኛለች፡፡የአዲስ አበባ ህዝብ እኮ ከኢዜማም ከማንም ላይ እጁን አንስቶ ራሱን ለማዳን ተነስቶ መስራት ከጀመረ ቆየ፡፡እስከዛሬ ኢዜማን ያድነኛል ብሎ ተቀምጦ ቢሆንማ ይሄኔ ከኦሮሚያ ከተሞች እንዳንዱ ሆኖ በቁቤ እየፃፈ ነበር፡፡ ለማንኛውም የኢዜማ መግለጫ እውነትም ምርጫው በቀኑ ሊደረግ ነው እንዴ ከማስባል ባለፈ የሰጠኝ ትርጉም የለም!
  ያልሞተ ሰው ኢዜማ ስለአዲስአበባ ሲሟገት ይሰማል
Filed in: Amharic