>

አባ ባህሪይ ዛሬ እየሆነ ላለው እማኝ ቢሆኑ ኖሮ....!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

አባ ባህሪይ ዛሬ እየሆነ ላለው እማኝ ቢሆኑ ኖሮ….!!!
አቻምየለህ ታምሩ
አባ ባሕርይ  ቀና ብለው «ዜናሁ ለጋላ» የሚለውን የዐይን ምስክርነት በዚህ ዘመን መመዝገባቸውን መቀጠል የሚችሉበት እድል ቢያገኙ ኖሮ በአዲስ አበባ ላይ እየተደረገ ያለውን ውርደት እንዲህ ብለው ይተርኩት ነበር፤
« ዐቢይ አሕመድ የሚባል እናቴ ንጉሥ  ትሆናለህ ብላኛለችና ተከተሉኝ የሚል ከወደ አባጅፋር አገር የተነሳ ሞቲ ሰባተኛ ንጉሥ ሆኖ ያለዘውድ በነገሠበት ስምንተኛ ወር ላይ በአባዱላ ጃዋር መሐመድ የሚመራው ሉባ ዱላና ቆንጨራውን ይዞ አዲስ አበባን ከቦ ጭንቀት ውስጥ ጣላት።
ሉባው ኮንዶሚኒየም የሚባል ቤት ካልተሰጠኝ ምድሩንም ሰማዩንም እፈጀዋለሁ እያለ ፎከረ። አባዱላ ጃዋርም መጣሁብህ ብሎ ያገሳ ጀመር። ሉባው ዱላ፣ ሚስማር የተጠቀጠቀበት አጣናና ቆንጨራውን ይዞ ሲገሰግስባት ከተማይቱ ጸጥ እረጭ አለች።
 ጸሎት ጮክ ብሎ የሚጸልይ ቄስና ሸህ እንኳን አልነበረም። የጸሎት ድምጽ ማውጣት ብቻ ሳይሆን  እጣንም ያለ ሉባው ፈቃድ ማጨስ የማይቻል ሆነ። የከተማው ሰው ሉባው ሳይሰልበው ራሱን እየሰለበ እስከመስጠት ድረስ የፈራ ነሆለል ትውልድ ሆነ። አባዱላ ጃዋር መጣሁብህ ብሎ ባገሳ በስምንት ወሩ  ኢሬቻ በሆነ በበነጋታው  በከተማው ሰው ወጪ  የተሰሩ 23 ሺህ ኮንዶሚኒየም የሚባሉ ቤቶች ለሉባው ተከፋፈለ። ወደፊት ከኖርሁ ጉርባዎች ሉባ ሆነው ከነሱ የቀደሙት ያልወጉትን አገር  ሲወሩና ከበው ሲያስጨንቁ ታሪኩን እጽፋለሁ»
Filed in: Amharic