>

ይድረስ ለዳንኤል ክብረት ፡- የኢትዮጵያ ጉዳይ በክርስቶስ እጅ የተያዘl መሆኑ ጠፍቶህ ወይስ ..... (ከሸንቁጥ አየለ)

ይድረስ ለዳንኤል ክብረት ፡-
የኢትዮጵያ ጉዳይ በክርስቶስ እጅ የተያዘl መሆኑ ጠፍቶህ ወይስ የአለቅላቂነት ባህሪ ተጥናዉቶህ?
 ከሸንቁጥ አየለ
የኢትዮጵያ ጉዳይ በክርስቶስ እጅ የተያዘ መሆኑ ጥፍቶህ ወይስ የአለቅላቂነት ባህሪ ክፉኛ ተጥናዉቶህ እንዲህ ከወንጀለኞች ጋር ለመሰለፍ ህሊናህ እንቢ ያላለህ? መዝሙረ ዳዊት አንድ ምን ይላል? መዝሙረ ዳዊት 1
1  ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።
የዚህ ሚስጢር በዳዊት አንደምታዉ ላይ በአስደማሚ መልክ ተቀምጧል። አላነበብከዉ ከሆነ ደግመህ አንብበዉ።
አለቅላቂዉ ዳንኤል ክብረት የብሄር ብሄረሰቦች በአል ጅጅጋ ላይ ሲከበር ከመለስ ዜናዊ ጎን ቆሞ መለስን የሚያስንቅ የብሄር ብሄረሰቦች ትንታኔ ሲሰጥ ነበር። እነ መለስንም ሲያወድስ ነበር።
ልክ አቢይ ወደ ስልጣን ሲመጣ ወያኔዎቹን መተቸት እና ማንጓጠጥ ብቻ ሳይሆን አቢይን እንደ መልአክ ማምለክ ደረጃ ላይም ደርሶ ነበር። ይሄዉ አለቅላቂነቱ ሽመልስ የተባለ እንጭጭ ኦነግ ነፍጥኛን ሰበርነዉ ብሎ የተሳደበዉንም ስድብ አስቦበት አይደለም ሲል በኦህዴድ ፋንታ ማስተባበያ ሰጥቶ ነበር።
 ዳንኤል ክብረት አንገታቸዉን ይሁን ወይም ጭራቸዉን አለዚያም ህሊናቸዉን የነጠቃቸዉ ሰዎችም ዳንኤል ክብረትን ተከትለዉ አዎ አዎ አዎ እያሉ ያለቃልቃሉ። ከአለቅላቂዉ ያለቃላቂዉ። ዳኔል ክብረት 45 ቤተክርስቲያናት ሲቃጠሉ ዝም ይላል። ብዙ ሽህ ክርስቲያኖች ሲታረዱ ዝም ይላል። ሚሊዮኖች እየተፈናቀሉ በእምነታቸዉ ሲገፉና አቢያተ ክርስቲይኛት ሲቃጠሉ አያገባዉም እና ዝም ይላል።
ዝም ቢል ማንም አይቀዬመዉም። ምክንያቱም ሀገር ያልቻለዉን እዳ ዳንኤል ይሸከመዉ ብሎ የሚፈርድበት ሰዉ የለም።
 አንጀት የሚያሳርረዉ፡ ቆሽት የሚያደብነዉ ግን አለቅላቂ ሆኖ የብዙሃንን መገፋት ባላዬሁም ካለፈ ብኋላ መድረክ ላይ እየወጣ ከአለቃላቂዎቹ ጋር ጉልበት ያገኙ ሀይሎችን ለማወደስ እና ህዝብ ይቅር እንዲላቸዉ የሚሄድበት እርቀት ነዉ።
ዳንኤል ልብ በል። አታዉቅም እንዳይባል. ታዉቃለህ። የኢትዮጵያ ጉዳይ በኢየሱስ ክርስቶስ እጅ የተያዘ ጉዳይ ነዉ። የኢትዮጵያ ጉዳይ በሰዉ እጂ የተያዘ ጉዳይ አይደለም። የኢትዮጵያ ጉዳይ በኦነጋዉይኝም፡ በህዉሃታዉያንም፡ በግብጾችም ፡ በአረቦችም፡ በምዕራባዊያንም እጅ የተያዘ ጉዳይ አይደልም።
 እናም ቀኑ ሲደርስ አንዴ የዲያቢሎስ ወዳጅ ሆነው ጣኦት ከሚያመልኩ፡ ለአጋንንት ከሚስግዱ ጋር እየተሰለፉ ሌላ ጊዜ ደግሞ የእግዚአብሄር ታቦትን እየተሸከሙ በእግዚአብሄር ፍርድ ላይ ከሚሳለቁ ጋር ክመቀጣትህ በፊት ንስሃ ገብተህ ወይ በአርምሞ ዝም በል።
አይ አደባባይ ላይ እገኛለሁ የህዝብ ድምጽ እሆናለሁም ካልክ እዉነትን እዉነት ሀሰትንም ሀሰት እያልክ ተናገር።
ከዚህ ዉጭ ግን በብልጣብልጥነት አለቃላቂዎችህን አስከትለህ አታለቅልቅ።ይሄ መራራ መልዕክት በአንድ ወቅት ተማሪህ ከነበርኩ ሰዉ ሲደርስህ እንደሚያበሳጭህ ባዉቅም ወደ ልቦናህ ትመለስ ዘንድ ሊያግዝህ ይችል ይሆናል።
ይሄ ሁሉ መከራ በቅድስት ኢትዮጵያ ላይ የሚደርሰዉ ከቶስ ያለ እግዚአብሄር እዉቅና ይመስልሃል? ከጸጉራችሁ አንዲት ዘለላ አለ ሰማይ አምላካችሁ ፈቃድ አትወድቅም ያለ አምላክ ልጄ ሲል የጠራዉን የኢትዮጵያን ህዝብ ጉዳይ የሚዘነጋዉ ይመስልሃል?
ልድገምና ልንገርህ የኢትዮጵያ ጉዳይ በመደሃኒአለም እጅ የተያዘ ጉዳይ ነዉ። በብልጣብልጥነት እና አለቅላቂነት የሚፈታም አይደለም። ፊትህን ወደ ክርስቶስ ሀይላት ወደ እዉነት ዘወር አድርጋት።
Filed in: Amharic