>
5:13 pm - Saturday April 19, 9169

ትልልቆቻችንን ከታሪክ መዝገብ ፍቀን ፣ ገለንና አሳደን ስናበቃ ጉቶዎችን "ዋርካ ሁኑን" የምንል ሆነናል?!? (ስሜነህ ሄርጳሳ)

ትልልቆቻችንን ከታሪክ መዝገብ ፍቀን ፣ ገለንና አሳደን ስናበቃ ጉቶዎችን “ዋርካ ሁኑን” የምንል ሆነናል?!?
ስሜነህ ሄርጳሳ

….ታሪክን እንደ ታሪክነቱ ብቻ መውሰድ። ትናንት የተፈፀሙ የታሪክ ክንውኖችን በዛሬ እይታ ፍርድ አለመስጠት። የታሪክ ክስተቶችን በተፈፀሙበት ሁኔታ፣ ጊዜ እና አውድ ውስጥ ለመረዳት መሞከር…
—-
1.እውነት ለመናገር እኛ ኦሮሞዎች ጥበብ እና ጀግንነት አይወድልንም: : ጥበብን እና ጀግነትን ተገንዝበን አናከብርም:: ጣይቱም ትሁን ምኒሊክ ከ50%  በላይ ኦሮሞ ናቸው:: ነገር ግን ኦሮሞ ሞኝ ነን ; ብዙ ግዜ በ inferiority compex ወደ ሃላ እንቀራለን:: አማራ የወደደው እና ያደነቀው ነገር ሁሉ የአማራ ይመስለናል:: በዚህም ጀግኖቹን እና ጠቢባኑን መጠቀም ሳይችል ለሌሎች አሳልፎ ይሰጣ ል።  ጀግኖቻችን እና ጠቢባኖቻችን በሌሎች hijack ይደረጋሉ::
2.አማራ ብልጠቱ ከየትም ብሄር ብትሆን  ጀግና እና ብልህ ወይም አዋቂ  ከሆንክ ይወድሃል:,ያከብርሃል የራሱ እስክትመስለው ያቀርብሃል:: Because they give high values for knowledge , wisdoms, leadership and heroism . ሞኝ ,ተላላ , አላዋቂ , ፈሪ ከሆነ አማራ የራሱንም መሪ ቢሆን አያከብርም አያደንቅም::
3. በትንሹ ለምሳሌ መንግስቱ ሀይለማሪያም በእናቱም ይሁን በአባቱ ኦሮሞ ነው ; የሚወደው እና ሚደነቀው ግን በአማራ ነው:: ሌሎችም እጅግ ብዙ አሉ እንደ እነ ሎሬት ፀጋየ ገ/መድህንም 100% ኦሮሞ ናቸው ; በጥበባቸው የሚወደዱት እና  ሚከበሩት ግን በአማራው ነው::
4.እዩዋቸው አቢይ አህመድ እና ለማ መገርሳን ; አማራ እንዴት እንዳነገሳቸው ,እንደወደዳቸው, እንዳከበራቸው , ህይወቱን አሳልፎ እንደ ሚስጥላቸው ::
5. እነሱ ግን ከኦሮሞ ህዝብ ተገኝተው , የኦሮሞን ወተት እና ውሃ ጠጥተው አድገው ሳለ ; አማራው አከበራቸው ከፍከፍም አደረጋቸው ምክንያቱም ያየው ብሄራቸውን አይደልማ ; ድፍረታቸውን ,leadership አሰጣጣቸውን , ብልህነታቸውን እና ቅንነታቸውን ነው:
6. የኦሮሞ ችግሩ በድሮው አባገዳ ደረጃ የሚወደሰውን  እና የሚደነቀውን ;  ከብት ጠባቂ ጀግና(0ld fashion warriors)ወይም local heroes እንጅ ; ለnational ጀግና ክብር አይሰጥም:: በዚህም የተነሳ የኦሮሞ ተወላጅ ዘመናዊ መሪዎቻችንን ብዙ እርቀት ሄደው ሀገር የመምራት እንዳይችሉ እንቅፋት እንሆናለን::
7. አሁን ለምሳሌ ኦሮሞ ቄሮ ጅዋር መሃመድ እንወድዋለን እናከብረዋለን እንበል; ጅዋር መሀመድ በ National ደረጃ በአማራ እና በትግራይ በሌላውም ብሄር ተቀባይነት ቢኖረው ; እኛ ኦሮሞዎች ጅዋር ኦሮሞ አይደለም እንላለን ; ምክንቱም ጅዋር local ብቻ ሆኖ ; ኦሮሞ ኦሮሞ እያለ ብቻ እንዲቀር እንፈልጋለን::
በዚሁ ያልተገባ እሳቤያችን ትልልቆቻችንን ከታሪክ መዝገብ ፍቀን ፣ ገለንና አሳደን ስናበቃ ጉቶዎችን ዋርካ ሁኑን የምንል ሆነናል?!?
8.  ለዚህም ነው ምእራብያውያን ; የአንድን ማህበረሰብ ስነልቦና እና የእውቀት ደረጃ ; ወይም values ለማወቅ ወይም ለመረዳት ከፈለግክ  ; ማህበረሰቡ የሚያደንቃቸው ጀግኖቻቸውን ወይም icons ቀርበህ ተመልከት ወይም አድምጥ የሚሉት::
9.  ምሊክንም ይሁን ጣይቱን ያስተዳደሩት ትምህርት በሌለበት ,ሚድያ በሌለበት ,ፌስቡክ በሌለበት የዛሬ 200 አመት ነው ; ስለዚህ በድሮው ዘመን የንጉሳዊ አገዛዝ አስተሳሰብ እንዳኛቸው::
እንግሊዝ አውሮፓም ቢሆን በዚያ ዘመን ; አንድ ግዛት አልገብርም ብሎ ካስቸገረ ; ለምን የእናቱ ልጆች አይሆኑም ; ለ 2 ግዜ ወይም 3 ግዜ ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከንጉሱ ከቤተመንግስት ይላክ  እና ; አሁንም አሻፈረኝ ካለ ተንቂያለው ብሎ የማስፈራሪያ እርምጃ ;  አልገብርም ብሎ ባስቸገረው በግዛቱ ህዝብ ላይ ይወሰድበት ነበር: “”nothing  is personal or hatred”
10. እነሱ አልከተልም ወይም አልገብርም ያላቸውን ህብረተሰብ ; እንደነ ጅዋር 6 አመት ሙሉ በፌስቡክ ህዝብን ለማሳመን ; እንደ ለማ መገርሳ ለማግባባት ምንም ዘመናዊ የመረጃ ማስተላለፊያ እና ሚድያ ሳይኖራቸው ; ሰው ቢገድሉ ወይም ቢያስፈራሩ  ምን ይገርማል ።
እኛ አለን አይደል በዘመናዊው ዘመን ተምረን እና ተፈጥረን የዛሬ 20 ቀን የደቡብ ልጅ እንደኛ ኦሮምኛ አልተናገረም ብለን ;በዚህ በሰለጠነ ዘመን በኮምኔኬሽን ማሳመን አቅቶን inocent ሰው ሻሸመኔ ላይ ዘቅዝቀን  የገደልን እና ያቃጠልን:: በምንሊክ ከተናደድን እኮ ከምንሊክ መማር ነበረብን; እውነተኛ ከሆን where is our practical justification ?
11 ከታሪክ ጋር ተጣልተን ደህና ታሪክ ልንሰራ አንችልም። የሚሻለው ሁለት ነገር ነው – አንደኛ ምሁራን የታሪክ ትርክቶች ውስጥ የተጣመመውን እንዲያቃኑ፣ የተዘለለውን እንዲያካትቱ፣ ወዘተ ለእነርሱ ኃላፊነት መስጠት።
ሁለተኛ ታሪክን እንደ ታሪክነቱ ብቻ መውሰድ። ትናንት የተፈፀሙ የታሪክ ክንውኖችን በዛሬ እይታ ፍርድ አለመስጠት። የታሪክ ክስተቶችን በተፈፀሙበት ሁኔታ፣ ጊዜ እና አውድ ውስጥ ለመረዳት መሞከር። ዛሬ ላይ ጥላ ያጠሉ ክስተቶችን ታሪኩን እንደዘመኑ ባህል (በዘመኑ normal ወይም accepted ነበረና) የተፈፀመ መሆኑን በመቀበል ጥላውን ለይቶ ከዛሬ ላይ ማንሳት ወዘተ።
አለዛ ሀገራዊ መግባባት የሚታሰብ አይደለም። ፖለቲካው እንዲሰክን ከታሪክ ጋር ያለን ጠብ መቆም አለበት። እኛ የዛሬ ነን፤ ትናንት ውስጥ የምንኖር የታሪክ እስረኛ መሆናችን ማብቃት አለበት። ወደፊት ለመራመድ የኋላው መስፈንጠሪያ እንጂ መቸከያ መሆን የለበትም።
Let’s set our standards higher and push forward our Oromo  leaders to the national and global levels by admiring them.
Filed in: Amharic