>

የጨዋታቸው ሕግ "የበለጠ ጽንፈኛ ወይም አክራሪ ሆኖ ለኦሮሞ አሳቢነትንና ተቆርቋሪነትን ማሳየት!" ነው (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

የጨዋታቸው ሕግ “የበለጠ ጽንፈኛ ወይም አክራሪ ሆኖ ለኦሮሞ አሳቢነትንና ተቆርቋሪነትን ማሳየት!” ነው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ለውጥ የተባለው ድራማ መተወን ከመጀመሩ በፊት ከነበረው ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅም ሳይሆን ለጠባብ ዘውገኛ የጥፋት ዓላማ የቄሮን ሁከት ከጀርባ ሆኖ እየቆሰቆሰ ሀገር ሲያውክ የነበረው ኦሕዴድና መዋቅሩ አሁን ላይ ቄሮ አዲስ አበባ ላይ “ነፍጠኛና ሐበሻ ከአዲስ አበባ ይውጣ!” የሚለውን ሁከትና ረብሻ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ በመውሰድ “ወያኔ ያቃተውን ነገር ኦሕዴድ አድርጎት ቄሮን ልክ ያስገባልናል፣ አደብ ያስገዛልናል!” ብላቹህ ትጠብቃላቹህ ወይ???
አየ እናንተ የዋሃን!!! የአስመሳዩ ዐቢይ ጭፍሮች እነ ሽመልስ አብዲሳ፣ እነ ታየ ደንድአ ምን እንዳሉና ለምን ጉዳይ አንደተዘጋጁ በአደባባይ የነገሩንን እረስታቹህታላ??? ቄሮን እንደበፊቱ ሁሉ ዛሬም ከጀርባ ሆኖ እየቆሰቆሰ የሚያሰማራው ማን ሆነና ነው “ቄሮን አደብ ያስገዙልናል!” ብላቹህ የምትጠብቁት??? በግልጽ እየነገሯቹህ እንኳ አይገባቹህም እንዴ??? ኧረ የእናንተ ጀዝባነትስ ለጉድ ነው!!!
አለ ደግሞ አንዳንዱ “አይ ኦሕዴዶች ‘እኔ የበለጠ አከራለሁ!’ የሚል ፉክክር ከኦነግ ጋር ስለያዙ ነው እንጅ ኦሕዴዶች ውስጣቸው እንደዚህ አያስብም!” የሚል የመጨረሻ ነፈዝ!!!
እነ ነፈዞ ሆይ! የጨዋታቸው ሕግ “የበለጠ ጽንፈኛ ወይም አክራሪ ሆኖ በመገኘት ለኦሮሞ አሳቢነትንና ተቆርቋሪነትን ማሳየት!” እስከሆነ ጊዜ ድረስ ኦሕዴዶች ኦነግ ትናንትና ከፈጀን በላይ ዛሬ እስከመፍጀት ድረስ ሔደው በማሳየት “ከኦነግ የበለጠ ለኦሮሞ ጥቅም እኛ የበለጠ አክራሪ ጽንፈኛ ነን!” እስከማለት ድረስ መጓዝ ላለመፈለጋቸው ምን ማረጋገጫ አላቹህ??? የታዬ ደንድአ፣ የሽመልስ አብዲሳና የሌሎች የኦሕዴድ ባለሥልጣናት ግልጽ የዛቻ ንግግር የሚያረጋግጠው ይሄንን አይደለም ወይ እነ ነፈዞ???
እናስ ታዲያ??? እናማ ሕግ አስከባሪ የሚባል አካል ስለሌለና እየሰማቹህት እንዳለው የጸጥታ አካል ተብየውም የቄሮ ተባባሪ ስለሆነ አዳሜ የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል ፈጦ እንደመጣብህ ተረድተህ በበቂ በመዘጋጀት እራስክን ከጥቃት የመከላከል ሕጋዊና ተፈጥሯዊ መብትህን ተጠቅመህ “ሆ!” ብለህ በመውጣት ሰላምና ደኅንነትህን ማረጋገጥ ካልቻልክ በስተቀር የእንስሳው መንጋ ቄሮና አሰማሪው አውሬው ኦሕዴድ ደመነፍሳቸው በሚመራቸው መሠረት ከዱላ ወደ ሜንጫ ተሸጋግረው የፈለጉትን ነገር ከማድረግ የሚያቆማቸው ወይም ሊያቆማቸው የሚፈልግ አካል የለም፣ በሜንጫ እየተቀነጠስክ የምትጣልበትን ቀን ብቻ እየቆጠርክ መጠበቅ ነው ያለህ አማራጭ!!! ከአሁን በኋላ ህልውናህና ደኅንነትህ በአራዊቱ መንጋ ቄሮ መልካም ፈቃድና ቸርነት ላይ ብቻ የተወሰነ ነው ማለቴ ነው!!!
የሚያሳዝነውና የሚገርመው ነገር የአዲስ አበባ ሕዝብ ሌላውም ህልውናውና ደኅንነቱ በዚህ ዓይነት የከፋ አደጋ ላይ እንደወደቀ እንኳ የገባውና የሚገባውም አለመሆኑ ነው!!! አያሳዝንም???
“ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰም አትሰማ!” ነበር ያሉት አበው??? እንዲያ ሆኖ ነው ነገሩ እየሆነ ያለው ሁሉ አልሞቅህና አልበርድህ ያለው!!! የራስህ ጉዳይ ነዋ!!! እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን ማለት ይቻላል???
Filed in: Amharic