>

የናዝሬቶች  ተጋድሎና ድል!!!   (ዘመድኩን በቀለ)

የናዝሬቶች  ተጋድሎና ድል!!!
   ዘመድኩን በቀለ
★ ሞተውም ቢሆን አሸባሪውን ኃይል ድባቅ መተውታል። በቁጥጥር ስርም አውለውታል። ቪቫ ናዝሬት!
~ ከጃዋር የወሃቢይ ሰራዊት ለማዳን ከዱከምና ከናዝሬቶች ተማር።
•••
በአይሱዙ ተጭኖ የመጣ ፀጉረ ልውጥ ኃይል በጠዋቱ ናዝሬት እንዲፈስ ተደረገ። ወዲያውኑ በኦሮሚኛ ቋንቋ በመጮህ ተቃውሞ ጀመሩ። ዳውን ዳውን አቢይ። ሚኒልክ ነፍጠኛ ነው። ጃዋር ሌንጨ ኬኛ እያሉ ይቀውጡት ያዙ። ከዚያም የንግድ ድርጅቶችን ወደ ማዘጋትና መዝረፍ። የመኪና መስታወት መሰባበር ጀመሩ።
•••
በዚህም አላቆሙም ይባስ ብለው የከተማውን ህዝብ ወደ መደብደብ ብሎም ባንክ ቤቶችንና ንግድ ቤቶችን ወደ መሰባበር አመሩ። በከተማው እስከ አፍንጫው የታጠቀ የጸጥታ ኃይል ቢኖርም ምንም ዓይነት እርምጃ ለመውሰድ ፈቃደኛ አይደለም። በዚህን ጊዜ ህዝቡ ጉዳዩ የረባሾቹ ሳይሆን የኦሮሚያ ፖሊስና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ መሆኑን አወቀ፣ ተረዳ።
•••
አሸባሪዎቹ ባጃጆች ወደማቃጠል ዞሩ። ከዚያም ወደ አፍሪካ ዱቄት ፋብሪካ በማምራት ፋብሪካውን ለማቃጠል ሙከራ ጀመሩ። በዚህን ጊዜ የናዝሬት ህዝብ መሞታችን ካልቀረ ተጋፍጠን እንሙት እንጂ ዝምም ብለንማ አንሞትም በማለት ራሳቸውን ወደ መከላከል ገቡ። አስገራሚው ነገር ግን አማጽያኑን የናዝሬት ልጆች ያለ ዛሬ አይተዋቸው አለማወቃቸው ጭምር ነው።
•••
በተለይ የናዝሬት የቀበሌ 01እና 02 ወጣቶች ወጥረው በመያዝ ባደረጉት ብርቱ ትግል የጃዋርን ባለ ቆንጨራ ሰራዊት አሯሩጠው በመውገር ገሚሱን በቁጥጥር ስር አውለዋል። በዚህም በተደረገው ፍተሻ አሸባሪዎቹ ከነ መታወቂያ ወረቀታቸውን በቁጥጥር ስር አውለዋል።
•••
የጃዋር ሠራዊት ወደ ናዝሬት የመጣው ከጅማ፣ ከሐረር፣ ከአሩሲ እና ራቅ ካሉ የኦሮሚያ ከተሞች መምጣታቸውን የሚያሳይ መታወቂያ ከመያዛቸውም በላይ እያንዳንዱ አሸባሪ ከሁለት በላይ መታወቂያ ይዘው መገኘታቸው ታውቋል።
•••
የማርያምን ቤተ ክርስቲያን ለማቃጠል የተንቀሳቀሰውን የወሃቢ ሠራዊት የቀበሌ 15እና 12፣ 19፣ እና የቀበሌ 20 ወጣቶች ቤተ ክርስቲያን ለማቃጠል የተደረገውን ሙከራ ከቀበሌ 13፣ 10 እና ከቀበሌ 09 ህዝብ ጋር በመቀናጀት ድል አድርገዋል።
•••
የ ቀበሌ 14 ወጣቶች ደግሞ ባደረጉት ከአሸባሪው ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ በማድረግ ዋጋ የከፈሉ ሲሆን በቀበሌ 01 ቀደም ሲል የኦነግ ባንዲራ ተቀብተው የነበሩ ድልድዮች በትራፊክ ቀለም እንዲቀየሩ ተደርገዋል።
•••
በናዝሬት በተደረገው ፀረ ሰላም ኃይሎች ዘመቻ እስላም ክርስቲያን፣ ኦሮሞ ዐማራ፣ ትግሬ ጉራጌ ሳይባል መላው የከተማው ህዝብ ያለ ብሔር ልዩነት በአንድነት ቆሞ ለሰላም ዋጋ ከፍሏል። በሂደቱም የቆሰሉ፣ የሞቱም፣ ንብረታቸውም የወደሙ ቢኖሩም በአንድ ላይ ቆመው የጃዋርን ሠራዊት አፈር ከደቼ አብልተው ነፃነታቸውን አግኝተዋል።
•••
አሁን ደግሞ በኋላ ምን እንደሚፈጠር ባይታወቅም የኦቦ ለማ መገርሳው መከላከያ ሠራዊት ናዝሬትን ተቆጣጥሯል። አያያዙ ለህዝብ የሚያስብ ይመስላል። ሰው አንዴት በሀገሩ መከላከያ ሰራዊትና በፖሊስ ሰራዊቱ ላይ እምነት እንዲያጣ ይደረጋል? ጭራሽ ከአሸባሪ ኋላ ቆሞ ህዝብ ላይ የሚተኩስ የኦሮሞ ፖሊስ እኮ ነው የገጠመን ጎበዝ?  ይላሉ ናዝሬቶች።
•••
★ የዱከሞችንና የሐረሮችን ተጋድሎ ደግሞ ቆየት ብዬ እመለስበታለሁ። አዲስ አበባም የጃዋር ሠራዊትን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር እሬቻውን አብልታዋለች። እሱንም እመለስበታለሁ።
★ ወዳጄ ወሃቢይ፣ የእነ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ፣ የእነ አቡበከር፣ የእነ አህመዲን ጀበል፣ የእነ ጃዋር መሃመድ ወሃቢ እንደሁ አርዶህ ካልበላህ፣ ደምህን ካላፈሰሰ አይረካም። መፍትሄው በተፈጥሮም በሕግም ድጋፍ አለህና ተደራጅተህ ራስህን ተከላከል። ይኸው ነው። ሃላስ። ቆንጅዬ ምክሬ ናት። ተቀበላት።
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ጥቅምት 12/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic