ኤርሚያስ ለገሰ
አቶ ጃዋር ጉድጓድ ምሦ አይጥንም ይሁን እባቡን፣ ቀበሮንም ይሁን ጅቡን … ጉድጓድ የሚምሱት እነሱ ናቸው ብዬ ነው። ዋናው ጉድጓድ የሚምስበት ፤ አይጥ የሆነበት ምክንያት እንደሚባለው በዶ/ር አብይ ዛቻ አይደለም።
አቶ ጃዋር ወደ አይጥነት የተቀየረው የአሜሪካ መንግስት ትኩረት ስላደረገበት ነው።
I.R.S ትኩረት ስላደረገበት ነው። ለዚህ ደግሞ የቅርብ መረጃዎች አሉ። በአሜሪካን ኢንተርናሽናል ሪቬኒው ኤጀንሲ የታክስ ሲስተም አንድ አሜሪካዊ ከአሜሪካ ውጭ ስላፈራው ንብረት አመታዊ ሪፖርት ማቅረብ አለበት ።
ይሄንን አለማድረግ ከፍተኛ ወንጀል ነው። እነ አቶ ጃዋር እንዲህ አይነት እንቅስቃሴ እንደተጀመረባቸው አውቀዋል። አድነው እንደሚይዙትም ጭምር ።
በመሆኑም አቶ ጃዋር ዜግነቱን ማስወገድ አለበት። ከአሜሪካ እስር ከI.R.S ለመዳን።
አቶ ጃዋር ለምርጫ ብሎ ነው፤ ዶ/ር አብይን ፈርቶ ነው የሚባለው ውሸት ነው።
አቶ ጃዋር ጉድጓድ የማሰበትን መሰረታዊ ምክንያት ዶ/ር አብይ ያውቃሉ። ዜግነቱን ለመተው ፕሮሰስ እያደረገ በመሆኑ ይችን አጋጣሚ በመጠቀም የሆኑ የማይተገበሩ የአፍ ማስፈራሪያዎችን ሰንዝረው በእኔ ምክንያት ዜግነቱን ተወ ለማስባል እርሱም በእሳቸው ምክንያት ጉድጓድ እየማሰ መሆኑንና ያ ጎልቶ እንዲንጸባረቅለት የፈለገ መሆኑ ሲታይ በህዝቡ ላይ ድራማ እየተሰራበት መሆኑን በቀላሉ መረዳት ይቻላል።
እውነታው ግን ጃዋር በሚልዮን የሚቆጠር የታክስ ገንዘብ በማጭበርበሩ የአሜሪካ መንግስት ምርመራ እያካሄደበት መሆኑ ነው።