>
1:05 am - Thursday December 1, 2022

በአርሲ ነገሌ አስደናቂው   የተዋሕዶ ልጆች ተጋድሎና ድል!!!  (ዘመድኩን በቀለ)

በአርሲ ነገሌ አስደናቂው   የተዋሕዶ ልጆች ተጋድሎና ድል!!!
 ዘመድኩን በቀለ
* ቄሮ ወሀቢ እስላም ብቻ የሚመስለው ገልቱ ሁላ ተሸወደ። የኦሮሞ ቄሮ ፣ የኦሮሞ የተዋሕዶ ልጆች ከወሃቢው ኦሮሞ ጋር ይከታከቱ ጀመር። ወሃቢይና ፖሊስ አንድ ላይ፣ የኦሮሞና የዐማራ፣ የጉራጌ፣ የደቡብ የተዋሕዶ ልጆች በአንድ ላይ ሆነው ፈጠሙ። ፖሊስም ሸሸ። ወሃቢይም ፈረጠጠ።
 —
 አባ ሜንጫ ጃዋር ወይ በእንቅልፍ ልቡ ሲያቃዠእ ወይ ደግሞ ከዐቢይ ለማ ጋር ተማክሮ እኩለ ሌሊት ላይ በእንቅልፍ ልቡ በሞነጫጨረውና ቄሮ ድረስልኝ ባለው መሠረት መንጋው ጨርቄን ማቄን ሳይል ሌሊቱኑ እየተመመ መጥቶ ከደጁ ተኮልኩሎ መዋሉ ይታወቃል።
 አዲስ አበባ መምጣት ያልቻሉትም በያሉበት በለመዱት የትግል ስልት ድንጋይ ተሸክመው መንገድ ሲዘጉ ውለዋል። ለአምላካቸውም ጎማ እያቃጠሉ ሲለማመኑ ውለዋል። ዋቃ ጉራቻው የደም ግብርም የለመደ ነውና የተመረጡ የተዋሕዶ ልጆች ከየ አካባቢ ተመርጠው ሲታረዱለት ውሏል። አጋንንቱ ከጴንጤው ዐቢይ የተጣላ መስሎ የፈረደባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሲያቃጥላት ውሏል።
•••
በዚሁ መሠረት ዛሬ አጋንንቱ ሁከት ማስነሳት ከፈለገበት ስፍራ አንዱ በሻሸመኔ እና አካባቢዋ ሲሆን በተለይ ደግሞ ከሻሸመኔ 23ኪሜ ርቀት በምትገኘው የአርሲ ነጌሌ ከተማ ላይ አጋንንቱ የከረመ ቂሙን ይዞ ነበር የተከሰተው። እንዲህም ሆነ። አጅሬ የኦሮሞ የወሃቢያ አአክራሪ እስላም የግርግር አጋጣሚውን አገኘሁ ብሎ እንደለመደው አላሁ ወአክበር እያለ በእውነተኞቹ የኢትዮጵያ እስላሞች ኃይማኖት እየቀለደ የኦርቶዶክሳውያኑን የመስቀል ደመራ እና ጥምቀት በሚከበርበትን ቦታ የተተከለ ቀይ መስቀል ነቅለው ይጥላሉ። የከተማዋ ኦርቶዶክሳውያን ግን ታገሱ።
•••
ከዚህ ቀደምም የከተማው የወሃቢይ እስላም አስተዳደር ከተደራጁ ቄሮ ከሚባሉት ልቡሳነ ሥጋ አጋንንቶች ጋር በመሆን መስቀላችሁን ከቦታው አንሱ በማለት በተደጋጋሚ ደብዳቤ በመጻፍ የቤተ ክርስቲያኒቱን ይዞታ ለመንጠቅ ሞክሮ የነበረ ሲሆን እኔም ራሴ ከጀርመን በወቅቱ ለነበረ ለከንቲባ ደውዬ ዘግቤ እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይ በክልሉ መንግሥት ጉዳዪ እየታየ ያለና የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስም እየተከታተሉት ያለ ቦታም ነው።
የአጋንንት መንጋዎቹ ግን የለማ መገርሳ መከላከያና የሽመልስ አብዲሳ ፖሊስና ልዩ ኃይል ከእነሱ ጋር ስላለ ወበራ። የክርስቲያኑ ዝምታን እንደ ፍርሃት ቆጠረው። መንጋው የልብ ልብ እያገኘ።መጥቶ የክርስቲያኖችን ሱቅና መኖሪያ ለማቃጠል በድንጋይ እየወገረ መንቀሳቀስ ጀመረ። አሁንም የተዋሕዶ ልጆች ታገሱ። ወሃቢ ሆዬ የበለጠ ወበራ።
•••
ፌደራል ፖሊስ ከነ ጭስ ቦንቡ መጣ። የተዋሕዶ ልጆች ደስ አላቸው። ቢያንስ ይሄኛው ከሽመልስ አብዲሳ ሠራዊት ከተሻለ ብለውም ተስፋ አደረጉ። ተበተኑ አለ ፌደራል እንደ ደረሰ ህዝበ ክርስቲያኑን። አንበተንም አሉ የተዋሕዶ ልጆች። ወሃቢ አይሸሽም። አይደነግጥም። ፌደራል ለምን አለ ህዝበ ክርስቲያኑን። መስቀላችን ተነቅሎ ወደ ቤታችን አንገባም። እስከ አሁን ወንድ ሴት ህፃን አዋቂ ሳንል በመንጋው በድንጋይ ተወግረናል እናም አንሄድም አሉ።
•••
የክልሉ አድማ በታኝም የመስቀሉን ደራዊት ለመበተን ሁለት ጊዜ የጭስ ቦንብ በመተኮስ ለመበተን ቢሞክርም ህዝቡ ግን እግርህን ብላ። በጅምላ ጨርሰን እንጂ በሃይማኖት ቀልድ የለም በማለት የቀረውም ከቤቱ ነቅሎ ወጣ።
•••
ቄሮ ወሀቢ እስላም ብቻ የሚመስለው ገልቱ ሁላ ተሸወደ። የኦሮሞ ቄሮ ፣ የኦሮሞ የተዋሕዶ ልጆች ከወሃቢው ኦሮሞ ጋር ይከታከቱ ጀመር። ወሃቢይና ፖሊስ አንድ ላይ፣ የኦሮሞና የዐማራ፣ የጉራጌ፣ የደቡብ የተዋሕዶ ልጆች በአንድ ላይ ሆነው ፈጠሙ። ፖሊስም ሸሸ። ወሃቢይም ፈረጠጠ።
•••
የተዋሕዶ የኦሮሞ ቄሮዎች አሸነፉ። ተነቅሎ የተጣለውን መስቀልም በታላቅ ክብር አንስተው በቦታቸው ላይ ተከሉ። ወሃቢይም ፈርጥጦ የት እንደገባ መድኃኔዓለም ይወቅ። እኔም እላለሁ። በሃይማኖት ቀልድ የለም። ዝም ብሎ መታረድ በግነት ነው። አረ በግም ሲታረድ ይወራጫል። እናም የኦሮሞ ኦርቶዶክሳውያን ከጃዋር አሽከርነት ውጡ። OMN የአክራሪ የኦሮሞ እስላሞች ቤት ነው። ዛሬ አብረህ የምታሽቃብጥ የኦሮሞ ክርስቲያን ወጣት እነ ጃዋር ነገ የሚያርዱህ መጀመሪያ አንተን ነው። እውነቱ ይሄው ነው። እናም እንደ አርሲ ነገሌው አስብበት።
•••
የጃል መሮው ወለጋ ዛሬ ጮጋ ብሎ ነው የዋለው። ወለጋ ጃዋር መሐመድን ካስጠነቀቀው ቆይቷል። ወለጋዎች የጎጃሞች ጎረቤቶች ናቸው። ትንሽም ፊደል የቆጠረ ይበዛበታል። በዚህ ላይ ይሄን የአሩሲና የባሌውን የሐረሩን አክራሪ የወሃቢይ እስላም ሴራ በሚገባ ነው የሚያውቁት። እናም ይጠየፉአቸዋል። አምርረው ይጠየፏአቸዋል። እነ ጃዋርም ለዚህ ነው ወለጋዎችን  “ ኢጆሌ ሚሺኖታ ” እያሉ የሚሰድቧቸው። ለማንኛውም ወለጋ ዛሬ ከመንጋው ጋር አልተባበረም።
•••
በአርሲ ነገሌ የኦሮሞ ክርስቲያን ቄሮ የወሃቢይ የኦሮሞ ቄሮን ድባቅ መትቶታል። ነገ እነ ጴንጤዎቹ ዐቢይ አህመድ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ አዲሱ አረጋ ቂጤሳ፣ ለማ መገርሳ ተመካክረው የሚወስዱት እርምጃ ባይታወቅም ዛሬ ግን የኦሮሞ የተዋሕዶ ልጆች አሸንፈዋል። የተነቀለውን መስቀል በቦታው መልሰው ተክለዋል።
★ እኔ የማውቀው ኦሮሞ ይሄ ነው። አከተመ።
•••
ሻሎም  !   ሰላም  !  
ጥቅምት 12/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic