>

"ለጠፋው የ67 ንጹሃን ወገኖች ህይወትና ለተጎዱ 218 ሰዎች ተጠያቂው ጀዋር ነው" (ታዬ ደንደአ)

“ለጠፋው የ67 ንጹሃን ወገኖች ህይወትና ለተጎዱ 218 ሰዎች ተጠያቂው ጀዋር ነው”
ታዬ ደንደአ
 
….የክልሉ ፕሬዚዳንት ኤታማዦር ሹሙ፤ ኮሚሽነሮቹን ጨምሮ ጓደኞቹ ናቸው ” ድረሱልኝ” ብሎ ህዝቡን ከሚጠራ ለምን ለነዚህ ሰዎች አልደወለም?!?
ማነው ያበደው?
       “በብዙ እብዶች መካከል ጤነኛ ያብዳል” ይባላል ይህን እውነታ ኡመር ሱሌማን ነው ከ18 አመት በፊት የተናገረው። ብዙ ሰዎች የወደዱት እምቢ ካለ ወይም እነሱ የጠሉትን ከወደደ “እብድ፣” ወይም “ከሃዲ መባሉ አይቀርም። በዚህ ውስጥ አልፈን ነው የመጣነው እኔ ጤንነቴን በደንብ አውቀዋለሁ የሰውም ማረጋገጫ አልፈልግም ለሰውም እንደዛው ትልቅና አስቀያሚ በሽታ ነው ያለው።
    ይህን ለማከምና ለማስተካከል መታገል ትክክል ነው ግን ደግሞ ትግሉ አገር በሚያፈርስ መልኩ መሆን የለበትም። የፈለገ ችግር ቢኖር ከየመን ከሊቢያና ከሶሪያ ኢትዮጵያ ትሻላለች! የመንን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት እንጂክአመሰግናለሁ  ኢትዮጵያን ወደ የመን መውሰድ ጤንነት አይደለም። ሩዋንዳን የዘነጋ ሰው በራሱ በሽታ ነው። ተቀምጠው የሰቀሉትን ቆመው ማውረድ ይቸግር ይሆናል ያጣነውን ብቻ ሳይሆን ያለንንም ማስታወስ ተገቢ ነው የተሰቀለውን ለማውረድ ስትል ብብት ስር የያዝከን እንዳታጣ
————-
    ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ፓርላማ ላይ እውነት ተናገሩ ሚዲያዎች ጥላቻና ብጥብጥን ከመስበክ እንዲቆጠቡ ሲሉ ማስጠንቀቂያ ሰጡ ጀዋር እንደሰማ ” እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምሰናል” በማለት ጉድጓድ መቆፈሩን ነገረን። በእለቱ ጀዋር ቤት ስብሰባ ነበር የሆነ ሰበብም ፈጥሮ እምቢተኝነትን ተቃውሞን ለማነሳሳት ከስምምነት ላይ ተደረሰ። በዚያኑ እለት ከለሊቱ 7:30 ላይ የጀዋር ጠባቂዎች እንደሚቀየሩ መደወሉ ተሰማ። ይህ የስልክ ውይይት ደግሞ በአማረ ሁኔታ ተቀድቶ ወድያውኑ ጀዋር አየር ላይ አዋላት።
ይህ ሁሉ ድንገት የተፈጠረ ነው?
.
በሌላ መንገድ እንየው!!
*
      ጀዋር የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ጓደኛ ነው ጀነራል ብርሃኑ ኮሚሽነር መላኩ ኮሚሽነር ከፋለውና ኮሚሽነር ደመላሽም ጋር በጣም ይቀራረባሉ ይተዋወቃሉ! ታዲያ ጀዋር ይህ ችግር ሲገጥመው ለምን ለሰዎቹ ደውሎ እርዳታ አልጠየቀም? በእጃቸው ምንም የሌለ ምንም የማያውቁ የአዳማና የሰበታን ነዋሪ መጥራቱ ነው እዛው ያለውን ጀነራል ብርሃኑን ሃይል መጠየቅ ይቀላል? አሳምነው ጽጌ ሰው የፈጀ እለት የጀዋርን ህይወት ለመታደግ ጀነራል ብርሃኑ ሃይል እንደላከለት ይታወቃል
*
      ደግሞ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እያወቀ እሮብ ጠዋት ነገሩን ለማቀዝቀዝ አልሞከረም? ጠዋት ካቃተው ማታ መግለጫ ሰጥቶ ሃሙስ የተፈጠረውን ጥፋት አስቀረውም?
እኔ ለነጻነት እንጂ ለባርነት አልታገልኩም ትላንት ጠመንጃ ፊትለፊት ቆሜ ለህዝብ መብት ተናገርኩ የማያውቁኝ ሰዎች በስድብ አፌን መዝጋት ይፈልጋሉ! የማይሆን ነገር ነው።!!! ሁሉም ይወቀው!!! ለጫወታ መስዋእትነትን አልከፈልኩም እስገገባኝ ድረስ ኦሮሞን ከሰቆቃና ከስቃይ ውስጥ ለማውጣት ነው ዋጋ የከፈልኩት ስቃይና በደል ደግሞ ዘመድና ጠላት የለውም።
.
     እኔ ኑሮዬን ያጣሁለት ኦሮሞ! የልጆቹን ደምና አጥንት ስውር እዚህ የደረሰ ኦሮሞ በባይሆን ግዜና በማይሆን ምክንያት ደሙ በከንቱ ማፍሰስ የማይሆን ነገር ነው። ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል። ለጠፋው ህይወት ለተጎዳው ለቆሰለው ወገን ለጠፋው ንብረት ተጠያቂው ጀዋር ነው። የጠፋው የ67 ንጹሃን ወገኖች ህይወትና የተጎዶ 218 ባለቤት ሊያገኝ ይገባዋል። በስንት መስዋእትነት የተገነባን የኦሮሞን ህዝብ አንድነት በአንድ ቀን ያፈረሰ ማነው? ለብዙ ሰዎች ይህን ለማመን ያስቸግር ይሆናል ነገ ግን ይገባቸዋል!
.
ይህ የእኔ አቋም ነው ድርጅትንም ሆነ መንግስትን አይመለከትም!
ያበደውን ደግሞ አድረን ማወቃችን አይቀርም
©ትርጉም Hebre Zema
Filed in: Amharic