>
5:13 pm - Friday April 19, 8250

እነ  "አሻግሬ" እና " ሱሴ" መሪዎቻችን በሐረርጌ ሰይፍ/ካራ ተሸልመዋል (ዘመድኩን በቀለ)

እነ  “አሻግሬ” እና ” ሱሴ” መሪዎቻችን
በሐረርጌ ሰይፍ/ካራ ተሸልመዋል !!
ዘመድኩን በቀለ
 ★ ይሄ ወደፊት ሊመጣ ላለው ምልክት ይሁነን። ሰይፍ!! 
   ★ የሚመሯቸው 80 ያህል ዜጎች የሞቱባቸው እንኳን በጭራሽ አይመስሉም!!!
•••
• ሐረር ማለት ባሳለፍነው ሳምንት ብዙዎች በዚሁ ካራና ሜንጫ ተቆራርጠው የተገደሉበት ሥፍራ ነው።
• በሐረር አቶ መስፍን ዓለማየሁ በዚሁ ካራ ተቆራርጦ፣ በድንጋይ ተወግሮ ቱቦ ውስጥ ተጥሎ የተገደለበትና እስከአሁን ሐዘኑ ትኩስ ሆኖ የሚለቀስበት ከተማ ነው።
• ሐረርጌ ማለት ከአንድ ቤተሰብ ባልና ሚስት፣ የባል ወንድም በአሰቃቂ ሁኔታ ታርደው የተገደሉበት ክልል ነው። በዚህ ካራም እያስፈራሩ በግድ ያሰለሙበትም ክልል ነው።
• በሐረርጌዋ በሮዳ ከተማ ውስጥ አሁን ዐቢይ እና ለማ በተሸለሙት ካራ አቶ ደረጀ ኃይሉ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ፖሊስ ይዞ ለባለ ካራዎቹ ሰጣቸው። በፖሊስ ጣቢያወ ውስጥ በመጀመሪያ በቁሙ በህይወት እያለ ዓይኑን ያወጡበት፣ ምላሱንም የቆረጡበት፣ ከዚያም በመጨረሻ ብልቱን ቆርጠው በአፉ ከከተቱበት በኋላ በሜንጫ፣ በድንጋይ፣ በገጀራ ጨፍጭፈው የገደሉበት ነው።
•••
እንግዲህ እነዚህ ናቸው አሁን ሀገር የሚመሩት። ሲበዛ ውሸታም፣ የሃሰት አባቶች፣ ፈሪዎች ነገር ግን ጨካኞች ኘም አሻግሬም ሆነ ሱሴ ምንም ዓይነት የኃዘን ምልክት አይታይባቸውም። ከሟቾች ይልቅ ለገዳዮች ጥብቅና ቆመው ሲከራከሩ ውለዋል።
•••
ሊመጣ ያለው እና እየመጣ ያለው መከራ ምክንያት ይፈልጋል። አሁን ከበቂ በላይ ምክንያቶች እየተፈጠሩ ነው። በዳር ሀገር ያሉ ክርስቲያኖች በሰማዕትነት ያልፋሉ፣ የእርስ በእርስ ጦርነቱ ብዙ ሰው ያልቅበታል። ክፉ የረሃብ ዘመን አለ። ማታ የታመመ ጠዋት፣ ጠዋት የታመመ ማታ የሚሞትበት ቀሳፊ ደዌ ከፊታችን ይጠብቀናል። ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን ከመጠበቅ በቀር ሌላ አማራጭ የለም። በሰላም ማስከበር ሰበብ በኢትዮጵያ ምድር እሳት የሚያዘንቡ የዓረብ ሀገራት በበአሰብ፣ በጅቡቲ፣ በምጽዋ ዝግጁ ናቸው። ሱዳን ግብፅ ሶማሊያም እንዳሰፈሰፉ ነው። መከራ አለ፣ ነገር ግን ኢትዮጵያ ታሸንፋለች። ከድቅድቁ ዋሻ ጫፍ የሚደንቅ ብርሃን አለ ይላሉ በረኸኞቹ።
•••
የሚገርመው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትንና የጦር ኃይሉን የሚመሩት እሊህ ሁለቱ ግለሰቦች ናቸው። መከላከያ አልረዳንም አትበል። መከላከያ እንዴት ነው የሚረዳህ። ወታደር በትእዛዝ ነው የሚንቀሳቀሰው። እናም እርዱአቸው ሳይባል ሊረዳችሁ አይችልም። ይኸው ነው።
•••
ሻሎም !    ሰላም !  
ጥቅምት 12/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic