>

"ውሻ ነከሰኝ ተብሎ ጅብ ጋር አቤቱታ አይኬድም!!!" (ሀብታሙ አያሌው)

“ውሻ ነከሰኝ ተብሎ ጅብ ጋር አቤቱታ አይኬድም!!!”
ሀብታሙ አያሌው
የፌደራል ዐቃቤ ህግ ኃለፊው የኦሮሞ ዴሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ብርሃኑ ፀጋዬ ሞቴን ባህርዳር ያድርገው የሰኔ 15 ግድያን በተመለከተ ሪፖርት ሳላቀርብ አልተኛም ይልሃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ 78 ሰው አርደው የበሉ (በላዔ ሰቦች)  እነማን እንደሆኑ እያወቀ፤ በአደባባይ ቪዲዮ እየቀረፁ ሲያርዱ፤ የእምነት ተቋማትን ሲያነዱ ተመልክቶ፤ በይፋ አማራ እና ጋሞን አግልል፤ አስወግድ ተብሎ መግለጫ እየተሰጠ አይኑን በጨው አጥቦ ይዋሽሃል።
በእጅጉ የሚገርመው የገዳይ መንጋው መሪዎች ከጃዋር እስከ አፍሮው ቀኝ እጃቸው ሆነው አብርው እየሰሩ ለሞቱ ሰዎች የብሔር ኮታ ሰጥቶ እመኑኝ ሊል አደባባይ ይመጣል። ይህም አልበቃውም የሚደርስላቸው አጥተው ኤሎሄ እያሉ ለታረዱት ነፍሳት ሳይራራ የአራጆችን ወንጀል ለመሰወር የእርስ በእርስ ፀብ ነበረ ይልሃል።
የመከላከያ ኢንዶክትሬሽን ህዝብግንኙነት ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል መሐመድ ተሰማ ያለውን ደግሞ እናስታውስ…”ቄሮ መንገድ ሲዘጋ ለምን ትዘጋለህ ብለው እንዳይዘጋ ለማድረግ የሞከሩ አካላት የፈጠሩት ፀብ ነው”  አየህ የአብይ አስተዳደር ይህ ነው።  በሪፎርም ስም መከላከያን በአንድ ብሔረሰብ  ጉያ ስር ሸጉጦ አገሪቷን ወደ አዘቅት እየነዳት ነው ያልኩህ ለዚህ ነው።
ሰኔ 15 ባህርዳር እነ ዶክተር አምባቸው፤ አዲስ አበባ እነ ጀነራል ሰዓረ ሲገደሉ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ አንድ ሻለቃ ጦር ልኮ  ጃዋርን ሲያስጠብቅ እንደነበረ በቅርቡ ታዬ ደንደአም አምኖ አረጋግጧል።  በዚያው ወቅት  በሜጀር  ጀነራል ጌታቸው ጉዲና የሚመራው የሰሜን እዝ ባህርዳር ነበር።
ወንጀለኛቸውን በጉያቸው ይዘው ለጃዋር ምንጣፍ እየጎተቱ፤ ይህው ፎቶው እንደሚያሳየው ገዳይ ምልምሎቻቸውን እየተንከባከቡ ስለ ፍትህ የማውራት ምን ሞራል አላቸው ? በነገራችን ላይ ይህ በፎቶ ላይ የምናየው አፍሮ በቅርቡ ጀዋር ድረሱልኝ ሲል ቄሮን መርቶ የመጣ እና መኖሪያ ቤቱን ከብቦ ሲጠብቅ ያደረ ነው።
ከደህንነት መስሪያ ቤቱ እና ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመሆን የአዲስ አበባውን የኢሬቻ በአል በቄሮ ሲያስጠብቅ ነበር።  በቅርቡ ደግሞ በአርሲ ዶዶላ የሜንጫ አዋጅ ሲታወጅ ሜንጫውን ይዞ በይፋ ዘመቻውን መርቷል።
ፌደሬል ፖሊስ፣ አቃቤ ህግ፣ ደህንነት፣ መከላከያ  የባህርዳር ሪፖርት ዝግጅት ስላለባቸው የነሱን ስራ ቄር እየሰራላቸው ነው።
እነዚህ ነውረኞች የሚያቀርቡት ሪፖርት ምንም ይሁን ምን አላማው ግልፅ ነው።  የሴራ አጀንዳቸውን ትተህ አንድነትህን አጠናክር።  ቀን ሲመጣ ለፍርድ መቅረብ ያለበት ለፍርድ ይቀርባል።  ውሻ ነከሰኝ ብለህ ጅብ ጋር አቤቱታ እንዳትሄድ ተጠንቀቅ።
Filed in: Amharic