>

ዛሬ የጃዋርን መግለጫ ከተዋሱ ነገ የሱን ሜንጫ እንደማያነሱ በምን እንመን? (አሌክስ አብርሃም)

ዛሬ የጃዋርን መግለጫ ከተዋሱ ነገ የሱን ሜንጫ እንደማያነሱ በምን እንመን?
አሌክስ አብርሃም
ጠ/ሚንስትር ዓብይ አህመድ አገር ለማረጋጋት ያደረጉትን ጥረት ባደንቅም ያቀረቡትን ሪፖርት ግን ፈፅሞ አላምንበትም ! በአሁኑ ሰዓት ኦሮሚያ ውስጥ እንኳን ቄሮ የጨፈጨፈውን ህዝብ ብሔር ለማጣራት ይቅርና ህዝቡ ጋር ለመነጋገርም ከባድ መሆኑን ማንም አይስተውም ! እንዴ… የገደላችሁን እናጣራ ብሎ የሚሄድ አጣሪ ይቅርና ዶ/ር ዓብይ ራሳቸው ጃዋርን ዝንብ እንኳን እንደማያርፍበት ምለው ተገዝተው ለመናገር በሄዱበት አንቦ ላይ ቤተክርስቲያን እንደገባ ውሻ እንዴት አካልበው እንዳባረሯቸው አይተናልኮ ! ((መልዓኩ ነጭ ሄሊኮፕተር ተመስሎ ነው ያዳናቸው እንጅ እስካሁን የተገደሉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ቁጥር 51 ይሆን ነበር !))
ለማንኛውም ይሄን የዶ/ር ዓብይን መግለጫ ከዚህ በፊት የት ነው የሰማሁት ብየ ሳስብ ለካስ ጃዋር ከዓመት በፊት ያወጣው መግለጫ ራሱ ነው !! ትዝ ይላችኋል? በአዲስ አበባ ዙሪያ በርካታ ህፃናት ሴቶችን ጨምሮ በቄሮ ሲጨፈጨፉና ንብረታቸው ሲዘረፍና ሲወድም ከፍተኛ ተቃውሞ ተነሳ …በወቅቱ በፎቶ በቪዲዮና በዓይን ምስክሮች ጭምር የተረጋገጠው ይህ ጭፍጨፋ ከፍተኛ ተቃውሞ በማስነሳቱ ጃዋር ብቅ ብሎ ምናለ ?….‹‹ለምንድነው የኛ ብቻ የሚጋነነው ? ለሰላም ብለን ትተነው እንጅ አዲስ አበባ ሳሪስ ላይ ከሰባ በላይ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ተገድለውብናል ››አለ ! ከገደሉት ቁጥር በላይ እኛም ሙቶብናል የሚል ማስተባበያ የመስጠት የተለመደ እቃቃ ጨዋታ!
የሳሪስ ዙሪያ ፖሊስ አዛዥ ታዲያ <<እርሰዎ በሚቆጣጠሩት ክልል ሰባ ሰው ተገድሏል ይባላል የታለ ሬሳው ?>> ሲባሉ ግርም ብሏቸው <<እኛ እንኳን ሰባ …..አንድ የተገደለ ኦሮሞ አላየንም>> ብለው የጃዋርን አይን ያወጣ ውሸት አሰጡት !! ከዛ በኋላ ጃዋር ይሁን የኦሮሞ ብሔርተኞች ሰብዓዊ መብት አጣሪ ኮሚሽን ይሁን መንግስት ተገደሉ ስለተባሉት 70 የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ትንፍሽ ያለ የለም !! በሚኒሊክ ዘመን ምንጅላታችን እንቅፋት መታው ብለው ሃዘን የሚቀመጡ ሰዎች ያውም ሳሪስ ላይ 70 ሰው ሙቶባቸው ዝም ሲሉ አስባችሁታል ????? የጠ/ሚ ዓብይም ሆነ የጃዋር ማስተባባያዎች መንፈሳቸው አንድ አይነት ነው …ልዩነቱ ተናጋሪዎቹ ሁለት ሰዎች መሆናቸው ላይ ብቻ ነው !
የሆነ ሁኖ ያሉትን እንቀበል ብንል እንኳን
50 ኦሮሞ፣
20 አማራ፣
8 ጋሞ፣
2 ስልጤ፣
1 ጉራጌ፣
2 ሀዲያ እና አንድ አርጎባ
የአንዱ ሟች ብሄር ያልታወቀ
የእነዚህ ንፁኃን ዜጎች ደም እንዲፈስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያነሳሳው፣ በሚመራው ሚዲያ የቀሰቀሰው ፣ቄሮ የሚባለውን ቡድን ያልሆነውን ነህ ብሎ በማጀገን በመላው የሰው ዘር ላይ ጥላቻ እንዲያድርበት ያደረገው አቶ ጃዋር መሃመድ መሆኑን ምንም አይነት ማስተባበያ ሊሸፍነው አይችልም …አሁን ሰውየው ከህግም ከመንግስትም በላይ ነው … ወይ መንግስት አልያም ህዝብ የተሻለ አቅም ሲኖረው ይህን ሰው ተገቢው የተከሳሽ ሳጥን ውስጥ ማየታችን አይቀርም !! ለጊዜው ግን የዶ/ር ዓብይን አጣብቂኝ በማየት እርሰዎም እንደኛው ነብስዎትን ለማዳን እየጣሩ ነው ብለን ከማለፍ ውጭ አማራጭ የለንም !! ስለነገ እናውራ ከተባለ ግን ጃዋር ባለበት አገር ሰላም ህልም ነው!! ነገ በሌላ የእልቂትና የብጥብት አጀንዳ ይከሰታልና !!
Filed in: Amharic