>

ስለ ጀኔራል አበበ ተ/ሀይማኖት ያልተነገሩን ....!!! (ናትናኤል አስመላሽ)

ስለ ጀኔራል አበበ ተ/ሀይማኖት ያልተነገሩን ….!!!
ናትናኤል አስመላሽ
 
ጋዜጠኛ ደረጀ ሃይሌ ክባዶ ሽዱሽተ(06) ነብሰ ገዳዩ ጀነራል አበበ ጋር ያደረገው ቃለመጠይ!!!
.—-
ጋዜጠኛ ደረጀ ሃይሌ፣ ከጀነራል አበበ ጋር ያደረገው ቃለ መጠይቅ አየሁት፣ ጋዜጠኛ ደረጀ ሃይሌ ተራ ጋዜጠኛ አይደለም፣ መፅሃፎችን ከነገፃቸው እየጠቀሰ ይጠይቃል፣ ይከራከራል፣ ከታሪክ ሰሪዎች እኩል በሜዳው የነበረ እስኪመስል ድረስ ደስ በሚል ጥያቄ እና መልስ ዝግጅቱን ጀምሮ ይጨርሳል። በቃለመጠይቁ  ግን ደረጀ ሃይሌ ብዙም ያልሄደባቸው ወይንም ደግሞ እንግዳው ማክበር እና ፍርዱን ለሰሚ የተወ ይመስል ለተሰጡት መልሶች መስቀላዊ ጥያቄ የሚያቀርብበት በመፅሃፍ የተሰነደ ሃቅ እያለ አውቆም ይሁን ሆን ብሎ ሲያልፈው አይቻለሁ። እኛም ካነበብነው እየጠቀስን ህወሓት ውስጥ ገዳዮች ከነበሩት ማለትም የባዶ ስድስት(06) ነብሰ ገዳዮች ከነበሩት አንዱ ጀነራል አበበ መናገር ያልፈለገውን ለመናገር እና ለመፃፍ ወስነናልhttps://www.youtube.com/watch?v=JpoppbCrqr0&fbclid=IwAR1okboPTUXxWKVowSTbCxR2bHuDHGOH4U2qYxtEdnP-All_VD___uAbPW4
.
ጥያቄው ሲጀመር ጀነራል አበበ እንዴት ብሎ ከተራ ወታደር እስከ ማእከላይ ኮሚቴ እንደደረሰ ቆራርጦ ነግሮናል፣ በህወሓት ቤት ወንጀል ሳይሰሩ ወደ ከፍተኛ ስልጣን መምጣት ሃጥያት ነው። ስለሆነም ጀነራል አበበ በደደቢት ከጀነራል ፃድቃን እኩል ወንጀል ሰርቶ ጀነራል የሆነ ሰው ነው። ጀነራል አበበ በህወሓት ሰራዊት ውስጥ በጭቃኔው ከሚታወቁ ታጋዮች አንዱ ነበረ። ጀነራል አበበ ከክንፈ ገብረመድህ ጋር የሰራው ወንጀል የፀጉራችን ብዛት ያክላል። የህወሓቱ ሰላይ እና የደህነነት አባል የነበረው አቶ ብስራት አማረ፣ በትግሉ ጊዜ በነ ጌታቸው አሰፋ ይሁን በህወሓት እንደ ፓርቲ የተፈፀሙትን ወንጀሎች ፅፎ ለታሪክ እንደሚያስቀምጥ ቃል ገብቶልን ነበር፣ መፅሃፍ የት እንደደረሰ ባላውቅም፣አቶ ብስራት አማረ መፅሃፉን ከፃፈው ግን፣ እድሜ የሰጣቸው የትግራይ እናቶች ምን እንደሚውጣቸው አላቅም። አሁን ህወሓት ወይ ሞት የሚሉ የትግራይ አክቲቪስቶች ወላጆቻቸው በህወሓት እንደተረሸኑ ሲያነቡ ምን እንደሚሉም አላውቅም፣ አሁን ሰይጣን የሚሉት አብርሃ ደስታ፣ ትክክለኛው የህወሓት ታሪክ ሲያውቁ አብርሃ ደስታን መልአክ እንደሚሉት እርግጠኛ ነኝ።
ወደ ዋናው ነጥቤ ልመለስ፣ ጀነራል አበበ የባታልዮን ኮሚሳር ለመሆን የፈጀበት አመት አራት አመት እንካን አይሞላም። ሕንፍሽፍሽ በሚል ትግርኛ ስንቶቹ እንደተገደሉ እና እንደታሰሩ ማንም ያውቃል፣ ያኔ ጀነራል አበበ ዋና ተዋናይ ነበር። አቶ አስገደ ገበረስላሴ ጋህዲ ሁለት በተባለ መፅሃፋቸው ገፅ 150-151 ላይ እንዲህ ይላሉ። “ለወታደራዊ ባይቶ የተመለመሉ አብዛኛዎቹ  በዝምድና እና በሰፈር ልጅ ነበር የተመደቡት፣ ከነዚህ ውስጥ አበበ ጆቤ ከህወሓት ማእከላቅይ ኮሚቴ በነበረባቸው ቅርበት ለመመልመል ችለዋል” ይላል። ጋህዲ ሁለት በተባለ የአቶ አስገደ ገብረስላሴ መፅፋህ ላይ እንዲሂ ይላል። “ህወሓት 69 አ/ም ክፍሎቹ እንደ አዲስ ሲያቋቅም የባዶ ስድስት(06) እስርቤት ሃላፊ የነበሩት በስብሓት ነጋ ቀጥተኛ ትእዛዝ የሚመሩ” ብሎ ካስቀመጣቸው ውስጥ።
1.  ሙልጌታ አለምሰገድ
2. አበበ ተኽለሃይማኖት (ጆቤ)
3. ክንፈ ገብረመድህን ወዘተ
አቶ አስገደ ገበረስላሴ  ጋህዲ ሁለት ገፅ 152-153
.
ባዶ ሽዱሽተ (06) ማለት ለመላው ኢትዮጲያ ህዝብ የተደበቀ ወይንም አዲስ ስም አይደለም፣ ህወሓት አዲስ አበባ ማእከላዊ ውስጥ ሲፈፀሙ የነበሩ ወንጀሎች ከመፈፀምዋ በፊት ደደቢት ውስጥ በዳ ሹዱሽተ (06) ብዙ ወንጀሎች ፈፅማለች፣ ለምሳሌ ያክል፣ የህወሓት አመራሮችን ይቃወማሉ የተባሉ ታጋዮች በቁማቸው በቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ተረሽነዋል፣ ከነዚህ ገዳዮች ውስጥ አንዱ ጀነራል አበበ ነው።
ጀነራል አበበ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ጨቃኝ ገዳይ ናቸው ሲሉም ይናገራሉ፣ ጀነራል አበበ በትግራይ ደደቢት በረሃዎች ውስጥ በርስዎ በክንፈ ገብረመድህ፣ በሓሰን ሽፋ በጭቃኔ የተገደሉ የትግራይ ወጣቶችስ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሰያስ በጭቃኔ ገድሎዋቸው ይሆን? የኤርትራው ፕሬዝዳንት በደም ከተጨማለቁ እርስዎስ በደም አልተጨማለቁም? ጋዜጠኛ ደረጀ ሃይሌ በአቶ አስገደ ገብረስላሴ የተፃፉት መፅሃፍቶች ስላላነበበ እንጂ የእርስዎ የበረሃ ጉዞ እና ጭካኔ በደምብ ይገለጥለት ነበር፣ ከህወሓት መስራቾች አንዱ የሆኑት አቶ ካሕሳይ በረሄ የፃፉት መፅሃፍ( Ethiopia : democratization and unity ; the role of the Tigray People’s Liberation Front) ላነበበ ኢትዮጲያዊ የእርስዎ (ጀነራል አበበ) እና የህወሓት አመራሮች ጭካኔ ይገለፅለት ነበር። የፕሬዝዳንት ኢሰያስ እና የጠ/ሚ ዶር አብይ ፍቅርም ያሳስቦታል? አዎ ልክ ነው፣ ወልደስላሴም በጌታቸው አሰፋ ሲታሰር ማእከላዊ ውስጥ ሆኖ ህወሓት ስለ መውደቅዋ ያሳስበው ነበር፣ ያለ ምንም ጥፋቱ አምስ አመት በመለስ እና በስብሓት ነጋ ትእዛዝ የታሰረው ቢተው በላይም፣ የአሳርዋ ህወሓት መውደቅ አሳስቦት፣ እስካሁን ድረስ ከአሳሪው ስብሓት ነጋ እግር ውስጥ አልጠፋም። እናማ አያሳስብዎት
 .
ሌላው እጅግ የሚገርም የጀነራል አበበ መልስ፣ እሳቸው በሁለት መስመር በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ ከመከላከያ ሲባረሩ፣ የእርስዎ ባለቤት አልተባረረችም ብሎ ጋዜጠኛ ደረጀ ሲጠይቅዎት የሰጡት መልስ እጅግ የሚገርም ነው። እሳቸው እንዳሉት ባለቤቴ ያልተባረረችበት ምክንያት ብለው የገለፁት፣ “መከላከያ በተቛም ደረጃ ይመራ ስለነበር ማንም እንደ ፈለገ ሊያባርርሽ ስለማይችል እዛው ቆይ አልኩዋት፣ አልተባረረችም” አሉ፣ የሚገርም ነው፣ እሳቸውስ በየትኛው አሰራር ነው የተባረሩት? ቢያንስ ቃለምልልስዎ የሚሰማ የሰባት አመት ልጅ እኮ አይደለም!!!
1.  መከላከያ በተቛም ደረጃ ሲመራ የነበረ ሳይሆን በህወሓት ሲመራ የነበረ ተቛም ነበር፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ፣ ከመለስ ሞት ቦሃላም ቢሆን፣ የህወሓት የበላይነት አለ ለማለት አቦይ ስብሓት ለህወሓት ጀነራሎች የሰጡትን እድገት እናውቃለን፣ እሳቸውም ያውቃሉ።
2. ጋዜጠና ደረጀ ፍርድ ለሰሚው ብሎ ተዎው እንጂ የአቶ ገብሩ አስራት መፅሓፍ ገፅ 397 ብቻ አነበበልዎት እንጂ ገፅ 398 አላነበበልዎትም፣ ይህም ያደረገው እርስዎ ጀነራል አበበ ውሸታው መሆንዎን ከፍትዎ ላይ እያነበበ ስለ ነበር ነው። ለማንኛው የ አቶ ገብሩ አስራት መፅሃፍ ገፅ 398 እንዲህ ይላል። .
.
“የመለስን ሃሳብ ይቃወማሉ ከሚባሉት የጦር መኮንኖች ውስጥ
1.  ኮሎኔል እሌኒ መለስ
2. ሌተናንት ኮሎኔል አረጋዊ(ጎልያድ)
3.  ሻለቃ ወልደስላሴ አብርሃ
4. ሌተናንት ኮሎኔል ኩሕለን ገሰሰ ወዘተ
ከነዚህ ውስጥ ለእስር ከተዳረጉት አንዳዋ ኮሎኔል እሌኒ መለስ; የመለስን አቋም የተቃወሙ የሰለሞን ተስፋይ(ጢሞ)ባለቤት ስትሆን፣ በወቅቱ የሁለት ህፃናት እናት ነበረች፣ ኮሎኔል እሌኒ  የታሰረችው ስውር በሆነ  የግል ቤት ውስጥ ነበር። ለእስር የተዳረገችውም የመለስን አቋም ስለተቃመወች ብቻ ነው። የጦር ሃይሉ አቃቢ ህግም ከሶ ለፍርዴብት ሊያቀርባት አልቻለም፣ ከዘጠኝ ወራት እስርቤት ቦሃላ ከቤተሰቦችዋ ጋር ተቀላቀለች። በመጨርሻም የቦርድ ፎርም ሰጥተው ፎርሙን ሙይው እና ከሰራዊቱ ተሰናበቺ ሲልዋት፣ ይህ ፎርም የሚሞላ የአካል ወይንም የአእምሮ ችግር ላለበት ነው እኔ አልሞላም ብላ ወረቀቱን ሳትሞላው ቀረች” ይላል (ሉዓላዊነት እና ዴሞክራሲ በኢትዮጲያ አቶ ገብሩ አስራት ገፅ 398-399)
.
ጀነራል አበበ በእርሶ አባባል መከላለያ ተቋም ቢሆን ኖሮ፣ እነ ኮሎኔል እሌኒ እና ሌሎቹ ለምን ለእስር ተዳረጉ? የእርስዎ ባለቤት ስላልተባረረች ወይንም ደግሞ እርሶ ልጆችዋን ማሳደግ ስለሚፈልፉጉ ባለቤትዎ መለስን እንዳትቃወም ነግረዋት ከሆኑ አሁንም ይንገሩን? መከላከያ ግን ከህወሓት የበላይነት ወይንም ደግሞ ከፖለቲካ ነፃ ነበር አይበሉን በዚህ እድሜዎ ዉሸት አያምርቦትም!.
.
 “መለስ ለራሱ ስልጣን ብሎ ጦር ሃይሎች ሞኮንኖች ክበብ ውስጥ ለሰራዊቱ አመራሮች ስብሰባ ሲያደርግ የተቃወመው ቢኖር ጀነራል ታደሰ በርሀ ብቻ ነበር፣ እርስዎ እንካን አልተቃወሙትም፣ ጀነራል ታደሰ በርሀ መለስ ህገመንግስቱን እየጣሰ እንደሆነ ሲነግረው፣ ስብሰባው መደረግ አለበት ብሎ ስብሰባው ሲያደርግ፣ ጀነራል ታደሰ በረሀ መልቀቅያ አስገብቶ መከላከያን ተሰናበት ይለናል (የአቶ  ገብሩ አስራት  መፅሃፍ ገፅ  395-396”)
.
እኔ ምለው ጀነራል አበበ፣ ስየ ከነ ቤተሰቡ ሲታሰር፣ የአቶ ገብሩ አስራት ባለቤት ከስራ ስትባረር፣ የሰለሞን ተስፋይ(ጢሞ)ባለቤት ኮሎኔል እሌኒ በስውር እስርቤት ስትታሰር;  የእርስዎ ባለቤት እንደት እስከ ብርጋዴል ጀነራልነት ማእርግ ደረሰች? ምናልባት እርስዎ ባዶ ስድስት(06) ውስጥ ስብሓት ነጋን ለማስደሰት ብዙ የህውሓት ታጋዮች ስለ ረሸኑ ይሆን? በባዶ ስድት(06) የተፈፀሙት ወንጀሎች በጥቂቱ ተፅፎ በቅርቡ ለገበያ ስለሚዉል ስምዎን ከሰሩት ወንጀል ጋር እዛው ያገኙታል።
.
ጀነራል አበበ እርስዎ ኢህ አዴግ በሙስና ይከሱታል; የእርስዎ እህት የኦሮምያ ገበሬዎች መሬት በየካ  ክፍለከተማ ውስጥ ዋና ቸርቻሪ እንደነበርችስ ረስተውት ይሆን? የትግራዩ ተወላጅ በዛን ጊዜ የባለ አደራ ምክርቤት የነበረው አቶ አምባሳደር ሓለፎም; ሙስና አልሰራም በማለቱ ብቻ ከዛም በእህትዎ ምክንያት የታሰረውስ ረስተውት ይሆን?
ለመረጃ ያክል አቶ አምባሳደር ሓለፎም ከ OMN ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ ካልሰሙት እንዲሰሙት እዚህ አስቀምጨዋለሁኝ ያድምጡት!!! ሙሰኛው ህወሓት ብቻ ሳይሆን የእርስዎም ቤተሰብም ጭምር ነው፣ እስኪ እንደ ጀነራል ገዛኢ ታሪክ ይስሩ፣ በችግር ላይ ላሉት የህወሓት የሰማእታት ወላጆችን ይርዱ። በተረፈ ግን የሸፋፈኑት ታሪክ በጥቂቱ  ይህ ይመስላል፣ መፅሃፉ ታትሞ እስኪወጣ ድረስ ለሁላችን እድሜ ይስጠን፣ አንድ ነገር ግን ልንገርዎት፣ ደደቢት ውስጥ የተፈፀመው ወንጀል፣ ደደቢት ውስጥ የረሸንዋቸው የትግራይ ወጣቶች ታሪኩን መች ይሆን ለትግራይ ህዝብ እና ለትግራይ ወጣት በተለይ አዲሱን ትውልድ የሚነግሩት? እባክዎትን ንስሃ ይግቡ፣ እኛም ታሪኩ አውቀን ይቅር እንላቸዋለን፣ በተረፈ መልካሙን ሁሉ እየተመኘሁ፣ አሁንም ቢሆን ግን የእውነት እንቅልፍ እንዲወስድዎት በደደቢት የተፈፀሙት ወንጀሎች ግድያዎች ሳይሸፋፍኑ ይንገሩን!!!https://www.facebook.com/OromiaMedia/videos/2081380872074769/
.
ጀነራል አበበ እርሶ እና ጀነራል ፃድቃድን አልተሳካልዎትም እንጂ፣ አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ከሞተ  ቦሃላ እኮ፣ ስልጣን ፈልገው አቦይ ስብሓትን ለማስደሰት ብለው፣ በአቶ ገብሩ አስራት የተፃፈው መፅሃፍ እኮ ውሸት ቀላቅለው ተችተውታል፣ አቦይ ስብሓት ነጋ ግን ማን; መች; ምን መጠቀም እንዳለብዎት ስለሚያውቁ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ከጨዋታ ውጭ አድርገዋቸዋል፣ አሁን እርስዎ አቦይ ስብሓት ስልጣን እንደማያካፍልዎት ሲያውቁ፣ አቦይ ስብሓት እና ስዩም መስፍንን “መቆዴናውያን” ብለው በሚዲያ ተሳድበዋል። መርህ አልባ ሰው ማለት እንደ እርስዎ ነው።
.
N B. ጋዜጠኛ ደረጀ መፅሓፍቶችን አገላብጠህ መጠየቅ ህ ጡሩ ነው፣ ነገር ግን ለጀነራል አበበ ስለ ኮሌኔል ኢለኒ መታሰር መጠየቅ ነበረብህ፣ እዛው አንድ መፅሃፍ ላይ እያለ ለምን እንዳለፍከው አልገባኝም፣ ለማንኛው በርታ ጋዜጠኛ ማለት እንዳንተ አምባቢ ማለት ነው በርታ።
Filed in: Amharic