>

የቦሌ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ከቄሮ ጥቃት የተከላከሉ 3 ወጣቶች በፖሊስ ጥይት ተመቱ!!!  (ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምንአለ )

የቦሌ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ከቄሮ ጥቃት የተከላከሉ 3 ወጣቶች በፖሊስ ጥይት ተመቱ!!!
 ጋዜጠኛ ሀብታሙ ምንአለ
” ቄሮ ነን!” ባዮች መጥተው ቤተክርስቲያን ሲያውኩ ከተከላከሉት መካከል  ሙስሊም_ወንድሞች ነበሩ !!!
   በቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ምን ተፈጸመ ?!
      አራት የሰ/ት/ቤት አባላት የሆኑ ልጆች ለኅደር ሚካኤል ክብረ በዓል ቤ/ክ በር ላይ የተሰቀለውን ባንዲራ በማውረድ ላይ ሳሉ ሁለት “ቄሮ ነን!” ባዮች መጥተው ለፀብ ሲጋበዙ የሰ/ት/ቤት አባላቱ ነገሩን ቀለል አድርገው “ተዉ!” በማለት ሲያግባቡት፣ አንደኛው “ማን እንደሆንኩ አውቃችኃል? ማንነቴን አሳያችኃለሁ!” ብሎ ፎክሮ ይሄዳል።
     ልጆቹም የልጁን ንግግር ከቁብ ሳይቆጥሩ ሥራቸውን መስራት ቀጥለው ከተወሰነ ደቂቃ በኃላ ብዛት ያላቸው ኦሮምኛ ተናጋሪ የሆኑ ቄሮዎች ባንዲራ በማውረድ ላይ የነበሩ ልጆች ላይ ጥቃት ማድረስ ይጀምራሉ።
    ይሄን ሲያረጉ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የሰፈሩ ወጣት በብዛት ሲመጣባቸው እግሬ አውጪኝ ብለው ይሸሻሉ። ከእነሱ መካከል አብድረዛቅ ሙሐመድ የሚባል ከጅማ የመጣ ልጅን አሯርጠው ይይዙታል። በቀጥታም ይዘውት ሰ/ት/ቤት ቢሮ አምጥተው ለኃላፊዎቹ ያስረክባሉ። የሰ/ት/ቤት አመራሮችም ለወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ለሆኑት ኢ/ር አዲስ ደውለው ሁኔታውን በማሳወቅ ልጁን ሊደርስበት ከሚችለው አካላዊ ጥቃት በመከላከል ቢሮ ውስጥ ያስቀምጣሉ።
    የተደወለላቸው ፖሊሶች መጥተው ልጁን በመረከብ፣ በቄሮ ጉዳት የደረሰባቸውን ልጆች በማነጋገር ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየወሰዱ እያለ ብዛት ያላቸው ቄሮዎች ወደ ቤ/ክ በር ሲጠጉ ልጁን ይዘው ከመጡ ከአካባቢው ወጣቶች ጋር ቤ/ክ በር ላይ ፊት ለፊት ይገጣጠማሉ። ፀብም ይጀመራል።
     የአዲስ አበባ ፖሊስ ከአቅሙ በላይ ሲሆን ወደ ነዋሪው ፊቱን ያዞራል። በዚያው አጋጣሚ ልጁም አምልጦ ሊሄድ ሲል በእውር ድንበር ወደ ቤ/ክ ግቢ ሲገባ በሰ/ት/ቤት አባላት በድጋሚ ይያዛል። የፌዴራል ፖሊስ አባላት መሳሪያ ቢይዙም ፀቡን ከመቆጣጠር ይልቅ ሸሽተው ቤ/ክ ግቢ ውስጥ ይገባሉ። ጥቃት የደረሰባቸውም ፖሊሶችም አሉ። ልጁንም ፀቡ ከተረጋጋ በኃላ እስከነ ንብረቱ ለፖሊስ ያስረክባሉ። የተይዘው ልጅ ስም አብድረዛቅ መሐመድ ይባላል። “ማንነቴን አሳይሃለሁ!” ሲል የነበረው፣ ሌሎችን ሰብስቦ የመጣውና በፀቡ መኃል የሸሸው አድና የሚባል ልጅ እግር ነው። ይሄንም ከተያዘው ልጅ አንደበት አድምጠናል።
    የተፈጠረውን ነገር የሰማ የአካባቢው ነዋሪ ከቅርብም ከሩቅም ተጠራርቶ ወደ ቤ/ክ ይመጣል። በዚህ ወቅት ተጨማሪ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት መጡ። በተለይ አንደኛው የመሳሪያ አፈ ሙዝ ወደ ነዋሪው በመወደር ለመተኮስ ሲዘጋጅ ድጋሚ ፀቡ በፖሊስና በህዝብ መካከል ሆነ። የተወሰነ ሰው ነገሩን ለማረጋጋት በሞከረበት ወቅት ቄሮዎቹ አሁንም ለፀብ እየተሰባሰቡ፣ ዱላም ጭምር በመያዝ መዘጋጀታቸውን ፖሊስና የነበረው ህዝቡ ይሰማል።
   ወዲያው። ፀቡ በአዲስ መልክ አገረሸ። ፖሊስ የአካባቢውን ወጣቶች ለመበተን ሲሞክር ነዋሪው ላይ እርምጃ ሲወስድ ቄሮዎች እነሱን ተገን አድርገው ጥቃታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። በዚህ ወቅት የሰፈሩ ነዋሪ የኾኑት ዳኛቸው አስማረ (ያኪኒ)፣ ወንድማማቾቹ ዳግም ዮሐንስና ሲራክ ዮሐንስ በጥይት ተመተው በቅድሚያ ወደ ዋሽንግተን ሆስፒታል በመቀጠል ወደ ምኒሊክና የካቲት ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል። ሁለቱ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ውዳሴ ሆስፒታል ሲላኩ ፣ አንደኛው ግን እዛው ቀዶ ጥገና እየተደረገለት ነው።
√ በዚህ ወቅት የአካባቢው ነዋሪዎች በፖሊስ እምነት የለንም በማለት ቤ/ክ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
√ ይሄ ሁሉ ችግር ሲፈጠር ፖሊስ ቄሮዎችን “ግቡ” ብቻ ከማለት ከዘለለ ምንም አይነት ነገር አላረደረጉም።
√ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባልደረባ በ97 ዓ.ም ወጣቱን ሲያስለቅም የነበረ፣ የህወሃት ቀንደኛ ታዛዥ ኮማንደር ብርሃኑ መብሬ የሚባል የአካባቢው ወጣቶችን:- “ችግር ፈጣሪ እናንት ናቸሁ!” አንላቀቅም በሚል አኳኃን ሲዝት ነበር። እኔ ላይም ሲፎክር ነበር። የሚሰማው የለም እንጂ።
√ ኢንስፔክተር አዲስ ለማረጋጋት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ነበር። እንደ እነ ብርሃኑ መብሬ ቆስቋሾች ጋሬጣ ሆኑበት እንጂ በጣም ጥሯል። ኢ/ር አዲስ ሊመሰገን ይገባል።
√ የተጎዱትንና በጥይት የተመቱትን ለማሳከም ከነገ ጀምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር ታውቋል።
√ በዚህ አጋጣሚ ቤ/ክ በመገኘት ቄሮን ሲፋለሙ የነበሩ #ሙስሊም_ወንድሞች ነበሩ። ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው እኩል ችግሩን ተጋፍጠዋል። – ፀቡ የእምነት እንዳልሆነ ይሄ ትልቅ ማረጋገጫ ነው።
ነገስ ምን እንሰማ ይኾን? <ፎቶውን የለጠፍኩት የተያዘው ልጅ አብድረዛቅ መሐመድ ።
Filed in: Amharic