>

ውሀ አልባ ግድብ ታቅፋ እንድትቀር የተፈረደባት ሀገር! (ሚልዮን አየለ)

ውሀ አልባ ግድብ ታቅፋ እንድትቀር የተፈረደባት ሀገር!!!

ሚልዮን አየለ
በአባይ ጉዳይ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት እስከምን ድረስ…
የአሜሪካዊው ባለስልጣን ኸርማን ኮኸን   ከመለስ ዜናዊ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጉ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ ሲቀጥል ባራክ ሁሴን ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ በመጣ ጊዜ ከአቶ ሀይለማርያም ጋር ሆነው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ኢትዮጵያ ያደረገችው ምርጫ ፍፁም ዲሞክራሲያዊ መሆኑን አይኑን ሳያሽ ነግሮናል፡፡ ምንም እንኳ ኢትዮጵያውያንም የአልም ህዝብም የተሳለቁበት ቢሆንም ፡፡
ዛሬ ላይ ደግሞ በአባይ ግድብ ላይ ከሩቅ ታዛቢነት ወደ መሀል አጫዋችነት ገብታ የግብፅን ኢንትረስት ለማስጠበቅ ደፋ ቀና እያለች ይመስላል፡፡  ምንም እንኳ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ገዱ አንዳርጋቸው አሜሪካ ከመታዘብ ውጪ ምንም የምትፈይደው አልያም ጣልቃ የምትገባው ነገር የለም ቢሉንም፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ላይ የተፋሰሱ ሀገራት ባደረጉት ስብሰባ ግብጽ ስምምነት እንዳሳየች እና ኢትዮጵያን በማይጎዳ መልኩ በአባይ ጉዳይ ላይ እንደምትስማማ የገለፀችበትን ቃል ጥቂት ቀናት እንኳ ሳይቆጠር በካይሮ በተደረገው ስብሰባ መልሳ ኢትዮጵያ በግብጽ የመጣውን ሀሳብ እንድትቀበል ለማድረግ እየሞከሩ ነው፡፡
በአጠቃላይ ለስምንት አመታት እየታኘከ ያለው የአባይ ጉዳይ ግብፅ በኢትዮጵያ ሀሳብ የምትስማማ እንዳልሆነ የመሚወጡት መረጃዎች እየጠቆሞ ናቸው አሜሪካ ደግሞ በአባይጉዳይ ላይ የግብፅ ኢንትረስት እንዲሟላ ለኢትዮጵያ መንግስትም ከፍ ያለ ገንዘብ ለመደለያነት ሊያቀርብ መሆኑንም ጭምጭምታዎች ያሳያሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በዚህ እንደማይደለሉ ተስፋ አደርጋለሁ ግብፅ እንደምትፍልገው በየአመቱ 40ቢሊየን ሜተሪክ ኪዩብ ውሃ እንድትለቅላት የሚደረግን ስምምነት በላዩም የግብፅ አስዋን ግድብ 165 ሜትር በታች ከሆነ ኢትዮጵያ ከግድቧ ላይ እንድትለቅ እንድትስማማ በአሜሪካ በኩል ጫና ለማድረግ እየሞከረች ነው፡፡ የዘርፉ ምሁራን እንደሚገልፁት ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ ውስጥ በቂ ውሃ ለማጠራቀም ምእት አመታትን ይፈጅባታል ያ ደግሞ ያ ደግሞ የአባይ ግድብ ውሃ አልባ ኮንክሪት ይሆናል፡
Filed in: Amharic