>

የዶር. ዓቢይ ሽልማት!!! (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም)

የዶር. ዓቢይ ሽልማት!!!

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

አጼ ኃይለ ሥላሴ ከነግርማ ሞገሳቸው ከዙፋናቸው ከወረዱ በኋላ የኢትዮጵያ ስም እንዲህ በገናናነት ተሰምቶ አይታወቅም፤ የኢትዮጵያውያን ልብ በኩራት አበጥ ብሎ አያውቅም፤ ኢትዮጵያዊነት ቀና ብሎ አያውቅም፤ አሁን ሳየው ትልቁ ቁም ነገር ዓቢይ ሽልማቱን መቀበሉ አልነበረም፤ ሽልማቱ ትልቅ ነገር ነው፤ ከዓቢይ ስም ጋር ተቆራኝቶ እንደሚቀርም እርግጥ ነው፤ ለእኔ ዋና ቁም-ነገር ሆኖ ያገኘሁት ሽልማቱ ምክንያት የሆነለት የዓቢይ ንግግር ነው፤ የዓቢይ ንግግር በእንግሊዝኛ ከመሆኑ ሌላ ድንቅ፣ ልብን የሚነካና ኢትዮጵያዊ ሰውነትን የሚያጎላ ነበር፤ ዓቢይ በተናገረው ኢትዮጵያዊ ሰውነትን ተላብሰው ‹‹እኛም ኢትዮጵያውያን ነን፤›› አሰኛቸው፤ የኢትዮጵያን ሰብአዊነት፣ የኢትዮጵያን የመንፈስ ልዕልና፣ የኢትዮጵያውያንን የማስተዋል ቅርስ፣ የኢትዮጵያውያንን የአእምሮም ሆነ የመንፈስ ችሎታና ብቃት በሚገባ ለዓለም በሙሉ አሳይቷል፤ ንግግሩን ያላዳመጡት የዓቢይን ሰውነትና የአእምሮ ችሎታ መገንዘብ ያቅታቸዋል፡፡
ዶር. ዓቢይ እግዚአብሔር ይባርክህ! መንገድህን ያቃናልህ!
Filed in: Amharic