>
5:13 pm - Thursday April 20, 1539

"…ጨቋኝ መደብ እንጂ ጨቋኝ ብሔር የለም!!!" (ታዬ ደንደአ)

“…ጨቋኝ መደብ እንጂ ጨቋኝ ብሔር የለም!!!”
ታዬ ደንደአ
 
* “…ኦሮሞ ተበድሏል ብለን የምናወራውን ያህል አማራ፣ ትግሬ፣ ወላይታ ወዘተ ተበድሏል!”
 
 * “… አማራ በድሎናል ያልነውን ያህል ወንጀለኞች ከኦሮሞም ከትግሬም ይኖራሉ!”
ትናንት ወልዲያ ላይ ሁሉት የሰው ልጆች የአዳም ዘር ሞቱ። ዘለን የተፈናጠጥነው ብሔር ላይ ነው።
ናይጄሪያውያን ወይም ደቡብ ሱዳናውያን ቢሆኑስ? በማክስ 37 የሞቱት ወገኖችስ በሰው ልጅነታቸው እንጂ ማን ብሔራቸውን አነሳ?
የሕዝብ ማመላለሻ ተገልብጦ ሰዎች ሲሞቱ የሟቾች ማንነት፣ የሹፌሩና የመኪናው ባለቤት ብሔር አንስተን ተወቃቅሰናል?
ዛሬ ሁሉም ነፃ አውጪ ግንባር በሆኑበት ዘመን ነፃነት የነፈገችው ሀገሬ ናፈቀችኝ። ኢትዮጵያ ሀገሬ።
በተለይ ኦሮሚያን የብሶት መንደር የሚያደርጉ ዳያስፖራዎች ይገርሙኛል። በታሪክ ኦሮሞ ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀስ ያገኘውን ዘር ሳይመርጥ እያገባ ተዋህዶ ኢትዮጵያን መገንባቱስ? እስቲ ንፁህ ኦሮሞ ጥሩልኝ?
የኢትዮጵያ ቋንቋ ኢትዮጵያኛ እንጂ አማርኛ አይባልም ያሉት ምሁር መማር ለዚህ ነውን? የአሜሪካ ብሔራዊ ቋንቋ አሜሪካኛ ነውን? እናንተ ውጭ ሁኑና እሳት ለኩሱ። እኛን አቃጥሉን።
ማንም ምንም ቢያወራ ቀለማችን ቢለያይም ስፍራ ቢለያየንም በልዩነት ውበታችን አንድ ነበርን። አንድም ነን። ማንም በምናብ አይለያየንም። ምክንያቱም እኛ ነን።
እኛ ኩሩ ኢትዮጵያውያን።
Filed in: Amharic