>
5:13 pm - Monday April 19, 9655

ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች እውነት ሀገር  ደፍረዋል? (አብዱላሂ ሁሴን)

ስዊድናውያኑ ጋዜጠኞች እውነት ሀገር  ደፍረዋል???

 

 

አብዱላሂ ሁሴን
 
•  አብዱላሂ ሁሴን የሚለውን ስም  በርካቶቻችን ከአቶ መለስ ዜናዊ፣ ከቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ኢሌ እና በሶማሌ  ክልል  ከአሸባሪዎች ጋ ተያዙ ከተባሉ ሲውዲናውያን  ጋዜጠኞች  ጋ እናስታውሰዋለን።
 
አቶ መለስ በፓርላማ ቀርበው  ሴት የደፈሩ በሌላው አለም በህግ ይጠየቃሉ እነዚህ ጋዜጠኞች ግን ሴት ሳይሆን ሀገር ነው የደፈሩት በሚል  የገለፁትን   በተለየ ሁኔታ በወቅቱ ተሰርቷል ያለውን ደባ እና አሻጥር  እንዲሁም የአብዲ ኢሌን የግፍ እና የጭካኔ ተግባራት በሚስጥር በመቅረፅ ለአለም ያሳወቀው አብዱላሂ ዛሬ ማምሻውን በገፁ  ይህንን ብሏል።
“ከሰባት ዓመታት በኋላ የተሳካ የተስፋ እና የቡና ቀጠሮ!”
የዛሬ ሰባት ዓመታት ህይወቴ አደጋ ላይ ወድቆ በነበረበት ወቅት፤ ከኋላ የሚከተለኝንም ሆነ ከፊት የሚጥበቅኝን ሳላውቅ አገሬን ለቅቄ በወጣሁበት በዚያ የህይወቴ ከባድ ወቅት፤ በእጄ የነበሩትን መረጃዎች ለትክክለኛው ዓላማ ተጠቅሞ የያኔዎቹን አምባገነኖች ማጋለጥ እንድችል ከረዳኝ Johan Ripås ጋር ክልላችንም  ሆነ ኢትዮጵያችን ሰላም ሆነው በአዲስ አበባ እና በጅግጅጋ ጎዳናዎች ላይ በነጻነት መንቀሳቀስ በጣም ያስደስታል፡፡
ከሰባት ዓመታት በፊት  እኔና Johan Ripås ኢትዮጵያ ሰላም ሆና ኢትዮጵያ ላይ ቡና ለመጠጣት የያዝነው ቀጠሮ የፈጣሪ ፈቃድ ሆኖ ተሳክቷል፤ በአዲስ አበባ እና በጅግጅጋ የአገሬን ትኩስ ቡና ጋብዠዋለሁ … Johan Ripåsም የኢትዮጵያን ለውጥ በዘጋቢ ፊለሙ ውስጥ ለማሳየት የተጠቀመው ይህንን ታሪክ ነው፡፡
ይህ የ15 ደቂቅዎች ርዝመት ያለው ቪድዮ ዋና መቀመጫውን በስዊድን ያደረገው SVT (Sveriges Television)  የስዊድን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ የሆነው Johan Ripås ከባልደረቦቹ ጋር አዲስ አበባ እና ጅግጅጋ በመገኘት ያዘጋጀው እና ለ አየር የበቃ ዶክመንተሪ ነው፡፡
ይህ ዶክመንተሪ ዋና ትኩረቱን ያደረገው በዓለም የሰላም ሎሬት ዶ/ር ዐብይ አህመድ የሰላም ሽልማት እና በአገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ነው፡፡
 እኔና Johan Ripås በ 2012 እ.ኤ.አ በኬንያ ናይሮቢ ከሰባት ዓመታት በፊት በተዋወቅንበት ጊዜ እኔን አገሬን ጥዬ እንድሰደድ ምክንያት የሆነው የያኔው የአገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታ በመጠኑ ይዳስሳል፡፡
 ከዚያን ጊዜ አንስቶ በያኔው ፖለቲካ ግፊት ከአገር የወጣን እና በየፊናችን ለዴሞክራሲ እና ሰላም ስንታገል ቆይተን ወደ አገራችን መመለስ እንድንችል እና ለአገራችን ሰላም እና እድገት የበኩላችንን እንድናበረክት ያደረገን ለውጥ እስከሚምጣ ድረስ በአገራችን የነበረውንም ሁኔታ በመጠኑ ያስቃኛል፡፡
እኔ ከአገር ከመውጣቴ ቀድሞ በስራ ላይ ሳሉ ታስረው፣ የወቅቱ መሪዎች የጠሉትን እና የጠረጥሩትን ሁሉ ለማጥቃት ከሚለጥፏችው ስሞች አንዱ በሆነው ‘አሸባሪነት’ ተከሰው 438 ቀናትን ዘብጥያ ወርደው ስለነበሩት ሁለት ስዊድናውያን ጋዜጠኞችም ( Johan Persson & Martin Schibbye) ጉዳይ በዚህ ዘጋቢ ፊልም ተካቷል፡፡
ምን አልባት በ2012 እ.ኤ.አ ከአገር ስወጣ ሲያሳድዱኝ የነበሩ ሰዎች ተሳክቶላችው ቢሆን ኖሮ እጣ፟ፈንታዬ ይሆን የነበረው እና ከለውጡ በኋላ የተዘጋው ‘ጄል ኦጋዴን’ም በዚህ ዶክመንተሪ ተጎብኝቷል፡፡
ለውጡን ተከትሎ ጠ/ሚንስቴር ሆነው በርካታ አበረታች እና ተስፋ ሰጪ እርምጃዎችን በመውሰዳቸው  ትልቁን የሰላም ሽልማትን መቀዳጀት ስለቻሉት ዶ/ር ዐብይ ያትታል፡፡
 በአዲስ አበባ እና ጅግጅጋ የሚገኙ ወጣቶችም ስለ ዶ/ር ዐብይ ሃሳባቸውን ያጋሩበታል፤ የእኔም ቃለ-መጠይቅም ተካቶበታል፤  ተመልከቱት፡፡
Filed in: Amharic