>
11:05 am - Thursday August 18, 2022

ከንቲባው የሰጠውን ካርታ ክፍለከተማው  አመከነው!!  (ዘመድኩን በቀለ )

ከንቲባው የሰጠውን ካርታ ክፍለ ከተማው  አመከነው!! 

 

ዘመድኩን በቀለ 

* …በቄሮ ደም ስልጣን ይዞ ጭራሽ የኦሮሞን መሬት ማን ሰጪ አደረገው..!!!!
የአለቃና የሎሌው ድንበር በግልጽ  ተንዷል። የታከለም ጉልበት አቅመቢስ መሆኑ ታይቷል። ስውሩ ቄሮ ከግልጹ ታከለ በላይ ጉልበት እንዳለው አሳይቷል። ብቻ መጨረሻውን ማየት ነው። 
•••
ከ10 ቀን በፊት በመላው አዲስ አበባ ፈንጠዚያ ነበር። አብያተ ክርስቲያናቱ የራሳቸውን መሬት ሕጋዊ ካርታ ሰጥተናቸዋል ስለተባለ ቅዳሴም ውዳሴም ላይ ጮቤ ተረገጠ። በየክፍለ ከተማው ያሉና በመሬት አስተዳደር ውስጥ ያሉ ታከለ ራሱ የአዲስ አበባ መታወቂያ ሰጥቶ የሾማቸው ከኦሮሚያ ክልሎች አዲስ አበባ የተሾሙ ሃይማኖታቸው ኦርቶዶክስን እንዲጠሉ የሚያደርጋቸው ግለሰቦች ቅር አላቸው። ዛቱም። ዛቱናም አልቀረ ይኸው ታከለ ምን አገባው ብለው ካርታው በተሰጠ በአሥረኛው ቀን የእኛዎቹ ጨፍረው ሳያበቁ ወሽመጥ ቆራጭ ደብዳቤ ልከው እንደፈንጂ ካርታውን አምክነዋል ብለው ጻፉላቸው።
፩፥ ጀሞ ፫ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
፪፥ፉሪ ቅዱስ ኡራኤል እና እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን
፫፥ ፉሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፥ ካርታችሁ መክኗል የተባሉቱ ናቸው።
የእኛዎቹ
•••
በቅዱስ ሲኖዶሱ ፊት ለራሳቸው ለቅዱስ ፓትሪያርኩ በእጃው እኮ ነው በሚድያ ፊት ምክትል ከንቲባው ኢንጅነር ታከለ ኡማ ካርታውን ዓለም ሁሉ እያየው ለአብያተ ክርስቲያናቱ ሁሉ በክብር የሰጠን ብለው ካህናቱ የባህረ ጥምቀቱን ማክበሪያ ስፍራ የያዘውን ሕጋዊ ካርታ ይዘው የተሰጠውን ካርታ አምክኜዋለሁ የሚል ደብዳቤ የሰጣቸውን የክፍለ ከተማውን የመሬት አስተዳደር ኃላፊዎችን በጨዋ ደንብ ያናግራሉ።
እነሱ
•••
በኦሮሞ መሬት ታከለ ምን አገባው፣ የራሱ ጉዳይ ሂዱ ጥፉ አላሏቸውም። ህዝቡ ምንድነው የታሰበው ብለው የክፍለ ከተማውን አስተዳደር ኃላፊዎች ደግመው ማነጋገር ይሞክራሉ። ምን አልባት ተሳስተው ሊሆን ይችላል ብለው ማለት ነው። ኧረ እነሱ እቴ በቄሮ ደም ስልጣን ይዞ ጭራሽ የኦሮሞን መሬት ማን ሰጪ አደረገው ብለው ቀወጡት አሉ።  እንዲያውም የበዓለ ጥምቀቱን ማክበሪያ ሥፍራ በግሬደር እርስ አደረጉት።
እኔ፥
•••
ቆይ በዓለ ልደት በሰላም ይለፍና የሚሆነውን አብረን እናያለን ብዬ ጫ ብዬ ተቀምጫለሁ።
•••
እስከአሁን
•••
ፕሮቴስታንቶቹ ፥ በደቡብ ሆሣዕናና በጋሙጎፋ በመሎለሃ በግልጽ የመስቀል ደመራና የበዓለ ጥመቀት ማክበሪያ ስፍራችንን በጉልበት ቀምተው ምን አባታችሁ ታመጣላችሁ ብለዋል። ይኸው በአዲስ አበባም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ የሚገኘው የመሬት አስተዳደር የአለቃውን የከተማውን ከንቲባ ትእዛዝ፣ የምክርቤቱን ውሳኔ ጥሰው የኖረ ሕጋዊ ካርታ ጸድቆ በአደባባይ የተረከብነውን የበዓለ ጥምቀት ማክበሪያ ስፍራውን ካርታ በገዛ ሥልጣናቸው አምክነውት ለአድባራቱ ደብዳቤ ጽፈዋል። አከተመ።
•••
ጃንሜዳን መቼ ይሆን የሚወስዱት? እየጠየቅኩ ነው?
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ታህሳስ 27/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic