>
4:53 pm - Sunday May 25, 3524

የጃዋር የዜግነት መመለስ ጥያቄ ማሥረጃ በማቅረብ እንጂ በንንዝንዝ አይመልስም!!! (ዳንኤል በቀለ)

የጃዋር የዜግነት መመለስ ጥያቄ ማሥረጃ በማቅረብ እንጂ በንንዝንዝ አይመልስም!!!

ዳንኤል በቀለ
ጃዋር የአሜሪካ ዜግነቱን ለመመለስ በአሜሪካ የኢሚግሬሽን ጽ/ቤት በአካል ቀርቦ፥  ወይም ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆነ ደሞ የአሜሪካ ኤምባሲ በአካል ቀርቦ የአሜሪካ ዜግነቱን እንደማይፈልግ revoke እንዳደረገ ቃለ መሃላ መፈጸም አለበት። ጃዋር ይሄን አሜሪካዊነቱን ሪቮክ ያረገበት ቃለ መሃላ የፈጸመበትን ማሥረጃ ለምርጫ ቦርድ አቅርቧል ወይ?
 ይህ ጥያቄ የቀረበለት የአሜሪካ መንግሥት ጃዋር በግብር፥ በእዳ፥ በወንጀልና በወታደራዊ አገልግሎት ግዴታ እንደማይፈለግ አጣርቶ፥ ጥያቄውን ከተቀበለ በሁዋላ አሜሪካዊ ሳለ ላጠፋቸው ጥፋቶች (ካሉ)፥ ወደፊትም ከሚሰራቸው ወንጀሎች በአሜሪካ መንግሥት ከተጠያቂነት እንደማይድን አስረግጦ፥ የአሜሪካ ዜግነት ማጣቱን የሚገልጽ ማስረጃ ሰነድ ይሰጠዋል። ጃዋር እንዲህ አይነት የአሜሪካ ዜግነቱን እንዳጣ የሚያሳይ ሰነድ ለምርጫ ቦርድ አቅርቧል ወይ?
የኢትዮጵያ ዜግነትን ከነሙሉ ክብሩና ግዴታው እነዚህ ማሰረጃዎች ከቀረበ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ከሚመለከተው ባለሥልጣን መሥርያ ቤት ያገኘዋል። ከጃዋር የሚጠበቅበት ማሥረጃውን ይዞ ማመልከት ብቻ ነው።
ስለዚህ ንዝንዙን ወደ ጎን አርጉና ጃዋር ዜግነቱን ለመመለሱ ያቀረበው ማሥረጃ የትኛው እንደሆነ ንገሩን።
የቢቢሲ ዘገባ ከዚህ በታች

ጃዋር መሐመድ ኢትዮጵያዊ ነው” ኦፌኮ

ቢቢሲ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በቅርቡ በአባልነት የመዘገበው ጃ?ዋር መሐመድ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ ነው ሲል ፓርቲው ተናገረ።
በአገሪቱ ሕግ መሰረት ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌላቸው ግለሰቦች በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ ስለማይችሉ ከዚህ ቀደም የአሜሪካ ዜግነት እንዳላቸው የተነገረው አቶ ጃዋር የፓርቲው አባል መሆናቸውን ተከትሎ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ከአንድም ሁለት ጊዜ ግለሰቡ ኢትዮጵያዊ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እንዲቀርብ ለፓርቲው በደብዳቤ ጠይቋል።
ይህንንም ያረጋገጡት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ፤ “ጃዋር መሐመድ ኢትዮጵያዊ እንዳይሆን ገደብ የሚጥልበት ሕግ የለም፤ ስለዚህም ኢትዮጵያዊ ነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ለረጅም ዓመታት የአሜሪካ ዜጋ እንደሆኑ የሚታወቁት አቶ ጃዋር መሐመድ በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባል ሆነው በቅርቡ ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቀስቃሴ ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል።
በአገሪቱ ሕግ መሠረ አንድ የውጪ አገር ዜጋ የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብት እንደሌለው ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም አቶ ጃዋር መሐመድ አሜሪካዊ ዜግነታቸውን መመለሳቸውን እና ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ማረጋጋጫ እንዲሰጥ ለኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በደብዳቤ ጠይቋል።
አቶ ጥሩነህ ገምታ “መጀመሪያም ሆነ ለሁለተኛ ጊዜ የተላከው የድብዳቤ ይዘት አንድ አይነት ነው። የአቶ ጃዋር መሐመድን የዜግነት ሁኔታን ነው የጠየቁን። የዚህን አገር ዜግነት አግኝቷል ወይስ አላገኝም የሚለው ነው። ቦርዱ በዜግነት ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ሰው በምርጫ መሳተፍ እንማይችል ጠቀሶ ነው ጥያቄውን ያቀረበው” ይላሉ።
አቶ ጥሩነህ አክለውም ከምርጫ ቦርድ ይህ ጥያቄ እንደቀረበላቸው ጃዋር መሐመድ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ በጽሁፍ መጠየቃቸውን ተናገረው፤ ጃዋርም ለምርጫ ቦርድ ምላሽ የሚሆን መልስ “የዜግነት አዋጅ ቁጥር 378/1996” ጠቅሶ ለፓርቲው መስጠቱን አመልክተዋል።
“ጃዋር ምላሽ እንዲሰጥ በጽሑፍ አሳወቅነው። እሱም ምላሽ ሰጥቶናል። ይህንንም ለቦርዱ ለመስጠት ዝግጅት ላይ ነው ያለነው። እስከ ጥር 29 ነው ምላሽ ስጡ ያሉን፤ እኛም አዋጅ 378/1996 አንቀጽ 22 ጠቅሰን ከዚያ በፊት ምላሽ እንሰጣቸዋለን” ብለዋል አቶ ጥሩነህ ገምታ።
የኢትዮጵያ የዜግነት አዋጅ ቁጥር 378/1996 አንቀጽ 22 የኢትዮጵያን ዜግነት መልሶ ስለማግኘት ያትታል።
አስቀድሞ ኢትዮጵያዊ የነበረና በሕግ የሌላ አገር ዜግነት ያገኘ ሰው፤
ሀ/ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በመምጣት መደበኛ መኖሪያው በኢትዮጵያ ከመሠረተ
ለ/ ይዞት የነበረው የሌላ አገር ዜግነት ከተወ እና
ሐ/ ዜግነቱ እንዲመለስለት ለባለስልጣኑ ካመለከት የኢትዮጰያ ዜግነቱን መልሶ ያገኛል ይላል።
“አንደኛ ወደ አገር ተመልሶ እየኖረ ነው። ሁለተኛ ዜግነቱን ለአሜሪካ መልሷል። ሦስተኛ ደግሞ ለሚመለከተው አካል ዜግነቱን እንዲመለስለት አመልክቷል። ከዚህ ውጪ ሕግ የሚጠይቀው ነገር የለም። ስለዚህ ጃዋር መሐመድ የኢትዮጵያ ዜጋ ነው” ይላሉ።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጃዋር መሐመድ ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ፤ በምርጫው ላይ ለመሳተፍ የአሜሪካ ፓስፖርቱን የመመለስ ሂደቱ ከምን እንዳደረሰ ተጠይቆ የሰጠው ምላሽ፤ “ፓስፖርቴን መልሼያለሁ። በእኔ በኩል የሚጠበቀውን ጨርሻያለሁ። ምንም የሚያግደን ነገር የለም” ብሎ ነበር።
Filed in: Amharic