>

"በእጃችን የገባውን ሥልጣን ለማንም አሳልፈን አንሰጥም!!!" ( ጠ/ሚ  ዶ/ር አብይ መሀመድ በኦሮምኛ ያደረጉት ንግግር - ትርጉም በዶ/ር አብርሃም አለሙ) 

 “በእጃችን የገባውን ሥልጣን ለማንም አሳልፈን አንሰጥም!!!” 

*  “ዘመኑ የኦሮሞ ነው ኦሮሞ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ገና አፍሪካን እንገዛለን!” 

* “እኛ ኦሮሞዎች አሽሙር አንናገርም!”

 * “ኦሮሞ እስኪነሣ ነው እንጅ ሚዳቋዋን እንሰብራታለን ቀረጣጥፈንም እንበላታለን!”

 

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ መሀመድ በወልመል የግድብ ፕሮጀክት ምረቃ ላይ   በኦሮምኛ ያደረጉት ንግግር፤ 

ትርጉም :- በዶ/ር አብርሃም አለሙ 

“የተከበራችሁ የባሌ ሽማግሌዎች፣ የኦሮሞ ወጣቶች፦ የነገ ተስፋዎች፤
እኔ በየቀኑ የባሌን ሶፍ ኡመር ዋሻን ቀዬ ውስጥ ስለማየው፣ ውሎዬም፣ አዳሬም ሶፍ ኡመር ውስጥ፣ ባሌ ውስጥ ስለሆነ፤ ባሌ የኦሮሞ ታሪክ የተጀመረበት፣ ባሌ የኦሮሞ ታጋዮች ቁጭ ብለው፣ ተረጋግተው ጠላቶቻቸው እንዴት መፍረስ እንዳለባቸው አጥንተው፣ አዲስ ፍልስፍና ፈጥረው፣ ከዚህ ጀምረው ኦሮሞንና ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣትና ለመግዛት ስለሚችሉ፣ ሶፍ ኡመር . . . የሶፍ ኡመርን ዋሻ ቀዬያችን ውስጥ ስንሰራ ታሪክ እንዲያስታውሰውና ለማስታወስ፣ ለማሳወቅ፣ ዓለም ይሄ ምንድን ነው ቢለን፣ “የሶፍ ኡመር ዋሻ ይባላል፤ ትግላችን የጀመረበት፣ ማንነታችን የተጀመረበት ነው፤” ብለን ልንነግራቸው ነው። የሶፍ ኡመር ዋሻን ቀዬያችን ውስጥ የሚያዩ ሰዎች ምን እንደሆነና ለምን እንደሰራነው መገንዘብ ያዳግታቸዋል፡፡ ባሌ ግን ይህን መገንዘብ እይቸገርም፤ መጥታችሁ እዩት።
ኦሮሞነት በስራ ይገለጻል፤ ኦሮሞነት በልማት ይገለጻል፤ ኦሮሞነት በፍቅር ይገለጻል። በልዩ ባህል፣ ወግና ስነምግባር ያደግን ስለሆን፣ ስድብ አናውቅም፤ ፍቅር ግን እናውቃለን። ኦሮሞ ስለሆን እራስን መካብ፣ በአሽሙር መናገር አንችልም፤ ሰርተን ማሳየት፣ ጽፈን፣ ጽፈን ዓለም ሊማርበት የሚችልበትን ሃሳብ ማፍለቅ ብንችልም በአሽሙር መናገርን ግን ኦሮሞነታችን ስላላስተማረን አንችልበትም።
ኦሮሞ፦ ትናንት ንቆን፣ ሰብሮን፣ ዘርፎን፣ ኦሮሚያ ውስጥ ያለውን ሁሉ ግጦ የወሰደን፣ ልጆቻችሁ ታግለው፣ ሰባብረው፣ ከኦሮሚያ እንብርት አባረው ካስወጡት ጋር ከመቆም ሞት ይሻላል። ትናንትና ያዋረደንን፣ አዋርደነዋል፤ ትናንት የሰበረንን ሰብረነዋል። ትናንትና አትወጡም አትገቡም ብሎ አጥር ያጠረብን ዛሬ ወጥቶ መግባት አይችልም፣ ከእኛ ፈቃድ ውጪ።
ኦሮሞ ስለሆን መግደልን አልመረጥንም፤ ኦሮሞ ስለሆን እግር መቁረጥን አልመረጥንም። ባህልና ታሪካችን እንዲህ ያለውን ነገር ስለማይፈቅድልን። እነዚያት እጅሬዎች ጋር፤ አዋርዳን፣ ግጣን፣ እንደዚህ የሚያምርን መሬት ማልማት ስንችል፣ ሃብታችንን ዘርፋ ከመሬቷ ጋር ልትቀላቅል ከሞከርች ቡድን ጋር ዳግም አብረን እንቆምም።
አንዳንድ ሰዎች ብልጽግና ለምን ተፈጠረ? የማን ነው? ብለው ይጠይቁናል። ብልጽግና የኦሮሞ ነው፤ ብልጽግና፣ ብልጽግና የኦሮሞን ጠላቶች ከስልጣን፣ ከቤተመንግስት ለማባረር የተፈጠረ ነው። ብልጽግና ጠላቶቻችን ከዚህ በኋላ ከኛ ጋር ቁጭ ብለው በሀገሪቱ ላይ መወሰን እንዳይችሉ የተፈጠረ ነው። “ኦሮሞ የራሱን ድርጅት ገንብቶ ሀገር መምራት አይችልም፤ ሀገር መምራት የለበትም፤” የሚሉት ብልጽግናን ይሰድባሉ። ኦሮሞ ግን የብልጽግና አባት፣ የአዲስ ሃሳብ አእምሮ ባለቤት ስለሆነ የራሱን አያሳንስም፤ የራሱን አይገፋም፤ የራሱን አይጠላም። ይሁን እንጂ በሱ (ብልጽግና) ተጠቅሞ ባሌን ያለማል።
ሕዝቤ ሆይ፤
ብልጽግና የናንተ ባይሆን ኑሮ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በሰላሳ ዓመታት ውስጥ እዚህ ቦታ ተገኝቶ ክህዝቡ ጋር መቆም ያልቻለው ለምድን ነው? ባሌ አዲስ ሆኖ ነው? ባሌ አዲስ ሆኖ ነው? ወይስ ይሄ ወንዝ አዲስ ሆኖ ነው? ወይስ የሶፍ ኡመር ዋሻ አዲስ ሆኖ ነው? ወይስ የሼህከና ሁሴን ሜዳ አዲስ ሆኖ ነው ወይ? ባሌ ባሌ ነው የነበረው፤ የራሱ ሰው ስላልነበረው ነው ችላ የተባለው። አሁን ደግሞ ልጃችሁ እናንተን ይዞ፣ እስከዛሬ ያወረዱንን አዋርዶ፣ ወደ ሀገራቸው መልሶ፣ ሀገሪቱን ባዲስ መልክ፣ በፍቅር፣ በአንድነት ወደ ከፍታ ለማሻገር እየሰራ ስለሆነ፣ እንደዛሬው በችኮላ ሳይሆን፣ የምረቃ ጊዜ ወስዶ፣ ውስጡ ውለን፣ ውስጡ አድረን፣ ገንፎ በልተን፣ ዱአችሁን ሰምተን አሚን ብለን፣ በፍቅር መሄድ ነገና ከነገ ወዲያ ይሆናል።
ቤተመንግስታችንን መጥታችሁ ለማየት እድል ያላገኛችሁ ሰዎች፣ ከፕሬዚደንታችሁ ጋር ተመካከሩና፣ ከገዳ አባቶች ጋር ተመካከሩና መጥታችሁ እዩት፤ ቤተመንግስታችን ባሌን ይመስላል፤ ባሌ ቤተመንግስታችንን ይመስላል። ስለ ቤተመንግስታችን ማውራት የማልፈልገው፣ ኦሮሞ ሰርቶ ያሳያል፤ ማውራት አዲስ ጠባይ ስለሆነ፣ ይህን አዲስ ጠባይ ወደ ትውልድ ማስተላለፍ ስለማንፈልግ ሰርተን ማሳየት እንፈልጋለን። አሁን ደግሞ ጊዜ የለንም፤ ወሬ ይበቃናል፤ መከፋፈል ይበቃናል፤ መባላት ይበቃናል። እንደ ባሌ አንድ ሆነን ይህን ቆላማ ቦታ ገነት አድርገን፣ ለዚህ የታገሉትን. . . ቅድም መደወላቡ ላይ ተናግሬዋለሁ፤ ባሌን መለወጥ መሬት ላይ ብቻ ሳይሆን ገነት ውስጥም ሰማእቶቻችሁን የሚያስደስት ስለሆነ፣ ይህን መሬት እንለውጣለን። ይህን መሬት እንለውጣለን፤ ይህን መሬት እንለውጣለን፤ ቆላችን ገነት ይሆናል፤ ቄሮአችን ባለ ስራ ይሆናል፤ ድህነት ታሪክ ይሆናል፤ አንድነታችን ይጠናከራል፤ አንዳችን ላንዳችን ጉልበት ሆነን ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን እንመራለን።
ስለዚህ እግዝያብሄር የሰጠንን አእምሮ፤ እግዚያብሄር የሰጠንን አእምሮ ተጠቅመን በተግባር በሚታይ ስራ ሀገር ቀይረን የኦሮሞን ህዝብ ለማኩራት በልዩ ቆራጥነት ሌት ተቀን እየስራን ያለን በመሆኑ፣ በዱአችሁ አትርሱን፤ እኛ እግዚያብሄር የለም ብለን በራሳችን አለመጠን የምንኩራራም አይደለንም፤ እግዚያብሄርን እናምናለን፤ በህዝብ እናምናለን፤ በዱአ እናምናለን። ከህዝባችን ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን ሀገራችንን እንለውጣለን። ባለፈው ዓመት ጊኒር ውስጥ ስንዴ አይተናል፤ ለመጪው ዓመት ደግሞ ይህን ስራ እናያለን፤ እንመጣለን፤ እንጠያየቃለን፤ እናሸንፋለን፤ እንሻገራለን፤ እናሻግራለን። ሊያቆመን የሚችል ማንም አይኖርም።
ዛሬ እንደ ሚዳቋ ወዲህና ወዲያ እየሮጠ የሚወራጨውን ይቅርና ሃያ ሰባት ዓመት የበላችንን ወያኔ እንኳን በልተን አባረናታል። ኦሮሞ እስኪነቃ ነው እንጂ፣ እስኪነሳ ነው እንጂ ሲነሳ ሚዳቋ አትበላንም፤ እኛ ዝሆን ነን፤ እንሰብራለን፤ እንበላለን፤ እንገዛለን። ሃሳብ አለን፤ ድርጅት አለን፤ ከአለም ጋር ግንኙነት አለን፤ ህዝባችን በስራ ያውቀናል፤ እኛም ህዝባችንን እናውቃለን፤ ሽማግሌዎቻችንን እናውቃለን፤ ተያይዘን መላውን አፍሪካን ለመለወጥ፣ ይሄ ዘመን የእኛ ስለሆነ፣ ይህን ዘመን የሰጠን እግዝያብሄር በመሆኑ አሳልፈን ሰጥተን ዳግም ወደ ባርነት ለመመለስ አንፈልግም፤ ያ ደግሞ ተመልሶ አይመጣም። እጃችሁ የገባውን ነገር ጠብቁ፤ ቆጥቡ፤ አጠንክሩ፤ ጉድለት (ስህተት) ካለ ምከሩ።
ያለበለዚያ ይህን ከጅ ካወጣን አጥር ውስጥ ተቀምጠው እንደሚያለቅሱት ዓይነት ለቅሶ ስለሚሆን፣ ከዚህ በኋላ ለኦሮሞ ለቅሶ የማይሆንለት ስለሆነ፣ ያገኘነውን ይዘን፣ የቀረውን ሞልተን፣ ወደ ፊት መሄድ እንድንችል አንድነታችንን እንጠብቅ። ፍቅር ይብዛላችሁ፤ ሰላም ይብዛላችሁ፤ ብልጽግና ለናንተ ይሁንላችሁ። ተያይዘን ወደ አዲስ ለውጥ ተሻግረን እናሻግር። ክቡር ሁኑ፤ ኑሩልኝ፤ ታላቅ ፍቅርና ክብር ነው ለናንተ ያለኝ። መጪው ዘመን ለባሌ፣ ለኦሮሚያ፣ ለኢትዮጵያ፣ ለአፍሪካ የብልጽግና ዘመን ነው። ከለቅሶ ውስጥ ወጥተናል፤ ተያይዘን ወደ ልማት እንሄዳለን፤ ክቡር ሁኑልኝ።”
Filed in: Amharic