>

‹‹የሰበሩንን ሰባብረናቸዋል!!›› - የበሻሻው ጠፈርተኛ (አሰፋ ሃይሉ)

‹‹የሰበሩንን ሰባብረናቸዋል!!›› ( የበሻሻው ጠፈርተኛ)

 

አሰፋ ሃይሉ
 
• የሆነ ቅዠትማ ተወግተዋል በሆነ ነገራቸው ላይ፡፡ የምር የሆነ ሾጥ የሚያደርጋቸውማ የሆነ ሰባብረናቸዋል እያለ የሚያስለፈልፋቸው የሆነ አቴቴ ተፀናውቷቸዋል፡፡ 
• ሰዎቹ ግን ምን ነክቷቸዋል???? የበሻሻው ጠፈርተኛ በስተመጨረሻ የኦሮሞን ጠላት ሰባብሮ ሰባብሮ… ከጠፈር ሳተላይቱ ወርዶ ወርዶ… ዘቅጦ….ዘቅጦ …. በመጨረሻ ወዳደገበት የዘረኝነት የጠፈር አልጋው ላይ ተምዘግዝጎ ተፈጠፈጠና አረፈው??????
“በኦሮሚያ እምብርት ላይ (በፊንፊኔ ላይ) የሰበሩንን ሰብረን አባረናቸዋል! እኛ ካልፈቀድን ተመልሰው እንዳይመጡ አድርገን ሸኝተናቸዋል! ብልፅግና የኦሮሞ ጠላቶችን ከቤተመንግሥት ለማባረር የተፈጠረ ነው!”
(- ዶክተር ኮሎኔል አብይ አህመድ አሊ ለባሌ ኦሮሞ ተከታዮቹ ያደረገው ንግግር፡፡ አብይ አህመድ ደገመው የሽመልስ አብዲሳን፡- “በዚህ በፊንፊኔ ላይ ድል አድርገናቸዋል! የሰበሩንን አከርካሪያቸውን ሰብረናቸዋል!” ንግግር!!!)
እውነት እውነት… እኔን ግን እጅግ የሚገርመኝ ነገር… የትኛውን እና ማንን በየትስ ቦታ ነው ግን አከርካሪውን በአዲሳባ ላይ የሰባበሩት እነዚህ ሰዎች?? ወይስ ኦሮሞ ሰብሰብ ሲል የሆነ ስለ አከርካሪ ስለ አጥንት መሰባበር ምናምን የሚያስለፈልፋቸው የሆነ የቄራ ልክፍት አጠናግሯቸዋል?? ወይስ ምን ዓይነት ቅዠት ውስጥ ነው ያሉት?? ማን ነው ማንን የሰባበረው?? የት ቦታ ላይ?? መቼ?? እንዴ??!! የጤና ነው ግን??
ቆይ ግን የበሻሻው አብይ አህመድ አሊ – የኢህአዴግ ጆሮ ጠቢዎች (የኢንሳ) ዋና ዳይሬክተር፣ ሚኒስትር ሆኖ፣ ከነመለስ ጋር፣ ከነደመቀ፣ ከነኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ከነደብረፅዮን ጋር ሲያሸረግድ የኖረ ዋናው የሰባቂዎች አውራ አልነበረም ወይ?? የኦሮሞ ህዝብ፣ የትግራይ ሕዝብ፣ የአማራ ሕዝብ፣ የደቡብ ሕዝብ… የኢትዮጵያ ሕዝብ በጭንቅና በመከራ ተይዞ ኑሮው አልሞላ ብሎት ያቺኑ የመከራ ኑሮውን ሲገፋ… የበሻሻው አብይ አህመድ… ከገጠር.. ከውትድርና… ከተራ ካድሬ ተላላኪነት…. በኢህአዴግ ታቅፎና ተደግፎ ወደ አዲስ አበባ የተጠራው…. ከግል ኮሌጅ እስከ ሚኒስትርነት የተመነጠቀው… የጆሮ ጠቢዎች አለቃ ሆኖ… ቤተሰቡን እንደ ጌታቸው አሰፋ ቤተሰቦች አሜሪካ ልኮ እያኖረ፣ ልጆቹን አሜሪካ እያስተማረ፣ አሜሪካ እየተመላለሰ ተምነሽንሾ ተንቀባሮ በፊንፊኔ ላይ የኖረው…. በኢህአዴጎቹ የስልጣን ዘመን አይደለም ወይ????
እንዴ?!!!!! እና… ማን ነው እና ነው እሱ ራሱ?? የትኛው ቅድስናውና የትኛው አርበኝነቱ የትኛው ጀግንነቱ ነው እሱን ሰባሪ… ሌላውን ተሰባሪ ያደረገው???? የትኛውንስ የኦሮሞ ጦር አዝምቶ ነው…?? በየት ቦታ…?? እንዴትስ አድርጎ…. የየትኛውን ህዝብ ወይ የኦሮሞ ጠላት የሆነ አካል የሰባበረው???????? (ሀሀሀሀሀሀ….!!!! እንዴ????!!!!)
በእውነት ግን እነዚህ ሰዎች… የሆነማ አብሾ… ወይ የሆነ ቅዠትማ ተወግተዋል በሆነ ነገራቸው ላይ፡፡ የምር የሆነ ሾጥ የሚያደርጋቸውማ የሆነ ሰባብረናቸዋል እያለ የሚያስለፈልፋቸው የሆነ አቴቴ ተፀናውቷቸዋል፡፡ ሰዎቹ ግን ምን ነክቷቸዋል???? የበሻሻው ጠፈርተኛ በስተመጨረሻ የኦሮሞን ጠላት ሰባብሮ ሰባብሮ… ከጠፈር ሳተላይቱ ወርዶ ወርዶ… በመጨረሻ ወዳደገበት የዘረኝነት የጠፈር አልጋው ላይ ጭልጥ ብሎ ተፈጠፈጠና አረፈው??????
እሆሆሆ….!! ጉድ እኮ ነው ባካችሁ????!!  አልበዛም እንዴ አሁንስ????? ኤ…………..ጭጭ!!!  ‹‹ሲያልቅ አያምር!›› አለ ያገራችን ሰው??!!! ቅ ዠ ታ ሞ ች  ! ! ! !
Filed in: Amharic