>
4:31 pm - Friday August 19, 2022

የቀበሮ ባህታዊ  (ከሲናጋ ብቅአለ)

የቀበሮ ባህታዊ

 

 

ከሲናጋ ብቅአለ

 

          ልጃችን፤ ወንድማችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዓሊ ሥራቸውን ከጀመሩ ዛሬ እውነተኝ ገጽታቸውን ለህዝብ ገለጡ፡፡ በወልመል የግድብ ፕሮጄክት ምራቃ ላይ ተገኝተው በኦሮምኛ የተናገሩትን ወደ አማርኛ የመለሱት ዶክተር አብርሃም ዓለሙ የተባሉ የአገር ተቆርቁዋሪ ግለሰብ እንዳስቀመጡት እንደነዶክተር ብርሃኑ ነጋ ያሉ የተማሩና ለነጻነት ትልቅ መስዋዕትነት የከፈሉ አሳፋሪም አነጋገር ቢሆን “ከኔ በላይ ኢትዮጵያዊ ናቸው” ብለው እንዳልመሰከሩላቸው ሁሉ ስለፍቅር ፤ ስለሠላም ፤ስለእርቅ እንዳልሰበኩ ሁሉ፤ ሕዝብ ካልፈለገኝ በ24 ሰዓት ውሰጥ ሥራቸውን እንደሚለቁ በይፋ እንዳልተናገሩ ሁሉ እነሆ ዛሬ   “ማን አባቱ ነው( የኔ) ከእንግዲህ ሥልጣን ከኦሮሞ ላይ የሚነጥቀው” አይኖርም አሉ፡፡በምንም መልኩ እንዲወስድ አንሻም” ብለው ሲፎክሩ ተሰምተዋል፡፡

          ኣረ በጉዴ ወጣሁ አሉ እማት ተላላ ትሁነኝ ፡፡ ለዐቢይ ተንበርክኮ ያልጸለየ ፤በዐቢይ ንግግር ያልተመሰጠ አለ ቢባል አገሩን የሚጠላ ብቻ ነበር የሚባለው፡፡ ጉድና ጅራት ከበስተሁዋላ ነው እንዲሉ ዐቢይ የጭቃ ጅራፋቸውን አወናጨፉት፡፡

           በአክራሪ ጽንፈኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ዘንድ እንደ “ዲቃላ” ተቆጥረው አይወክሉንም የሚል አመለካከት ጠንክሮ በመከሰቱ፤ ዐቢይ ደግሞ ከምንም በላይ ለሥልጣናቸው ሙት በመሆናቸው የኦሮሞውን ሕዝብ በጉያቸው ለማድረግ የተደበቀውን ዓላማቸውን እውን ሊያደርጉና ተቃዋሚዎቻቸውን ለማማለል የወሰዱት እርምጃ እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ ስለሆነም የመጨረሻ ካርዳቸውን የዘረገፉት የአክራሪ ኦሮሞችን የነጃዋር መሓመድን፤ የነበቀለ ገርባን የነመራራ ጉዲናን የነሽመልስ አብዲሳን ጽንፈኛ አመለካከት ሌላውን ህዝብ “ምን ትሆኑ” ብለው ዘርግፈውልናል፡፡ ግድየላችሁም እኝህ ሰውዬ ከአባታቸው የወረሱት ሓይማኖት በልባቸው ተቀርጾ የተቀመጠ ይመስለኛል፡፡ ስለሼክ ዑመር ዋሻ ቅዱስነት ከማንም የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ በላይ የምሥክር ቃላቸውን ሲሰጥ የሰማነው ዛሬ ነው፡፡ ኣረ ለምን እስከዛሬ ለምን ተሸፈነ፡፡ ለነገሩ እንጂ የትኛውንም ሃይማኖት የመከተል መብቱ የሳቸውም የኔም የየአንዳንዱም ኢትዮጵያዊ መብት መሆኑን እንደምቀበል ለማስረገጥ እወዳለሁ፡፡

      ዐቢይ  በንግግር መቁዋጫ ላይ ምንጊዜም ፈጣሪን ማክበራቸውን ይናገራሉ፡፡ ባለፉት 50 ዓመታት የፈጣሪን ስም አንስቶ የሚናገር ባለሥልጣን ባለመኖሩ  ዛሬ እንዲህ ዓይነት ሰው ካስተዳደረን ፈጣሪ ፊቱን ወደኛ አዙሩዋል በማለት ደስ ያላለው አልነበረም፡፡ ዐቢያ አምላካቸው መድሐኔ ዓለም ይሁን ወይም አላህ መሆኑን አጣርተው ግን ለህዝብ ጀባ ይሉበት ቀን አላስታውስም፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉ በሁለቱ ሀይማነቶች መካከል ያለው ልዩነት ከሰማይን ከምድር በላይ የተራራቁ ናቸው፡፡ ክርስቲያኑ አየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወልዶ የሰውን ልጅ ከፍዳ ለማውጣት የመጣ ፈጣሪ ነው ሲል እስላሙ አምላክ አይወለድም አይወልድም ብሎ ይደመድማል፡፡ ስለዚህ በብዙ ሥነ ምግባር የሚያመሳስላቸው ቢኖርም አምልኮቻቸው የተለያዩ ናቸው፡፡ ይህ ለሁሉም ግልጥ ሊሆን ይገባል፡፡ የሚያዋጣውን ሀይማኖት የመከተልና ሁሉም የየራሱን ይዞ በመከባበር መዝለቁ ተገቢ ነው፡፡ ዐቢይ ፈጣሪ ፈጣሪ የሚሉት ግን ፖለቲካው ወደ ሚያመዝነው ዘንበል ለማለት እንጂ እሳቸው አሁንም ከላይ ለማለት እንደሞከርኩት የአባታቸው መንፈሳው አቁዋም እላያቸው ላይ ሠፍሮ የተቀመጠ ይመስለኛል፡፡ ይቅርታ ይደረግልኝና ሼክ ዑመር በስማቸው የሚጠራው ዋሻ ውስጥ ምን እንደሠሩ ባለውቅም ዋሻው በተፈጥሮ የተገኘ  ዋሻ መሆኑን ማንም አይክደውም፡፡ የእግዚአብሔር እጅ የማይዳስሰው አይኖርምና እዚያ ከእግዚአብሄር በተፈቀደ መልኩ የተፈጸሙ ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ እቀበላለሁ፡፡ የእግዚአብሔር መገለጫው ብዙ ነውና፡፡ 

      የዶክተር ዐቢይ ፕሮፓጋንዲስቶች እንደሚነገሩን ከሆነ ዐቢይ ከተመረጡ ወዳጆቻቸው ጋር በመሆን በቤት መንግሥቱ ውስጥ በወር የተወሰኑ ቀናት ተገናኝተው በደረታቸው መሬት ላይ ተደፍተው ክርስቲያናዊ ጸሎት እንባቸውን እየዘሩ ለአገራቸው ይማጸናሉ የሚል ወሬ ሽው ብሎኛል፡፡ በሰመሁም ጊዜ ተደንቄያለሁ፡፡ መንፈሱን ለእግዚአብሔር ተገዢ ያደረገ ዞሮ ዞሮ ከክፉ ሥራ ይሠወራል በሚል እሳቤ፡፡

      በወልመል የግድቡ ምረቃ ሰዓት “……  ትናንት ንቆን፤ሰብሮን ፤ዘርፎን፤ ኦሮሚያ ውስጥ ያለውን ሁሉ ግጦ የወሰደን፤ ልጆቻችሁ ታግለው፤ ሰባባረው፤ ከኦሮሚያ እምብርት አባረው ካስወጡት ጋር ከመቆም ሞት ይሻለናል፡፡” “ትላንት ያዋረደንን አዋርደነዋል፤ ትናንት የሰበረንን ሰባብረነዋል፡፡” ሲሉ መናገራቸውን በጆሮዋችን ሰማን፡፡

      “ ጠላቶቻችን ከዚህ በሁዋላ ከኛ ጋር ቁጭ ብለው በሀገሪቱ ላይ መወሰን እንደይችሉ ለማደረግ የተፈጠረ” ድርጂት ብልጽግና መሆኑን ያበስራሉ፡፡ ኣረ ማነው ጠላቱ ? ኣረ ማንን የሰባበሩት? ኣረ ማነው የኦሮሚያን ሀብት ግጦ የወሰደው?

        “ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን እንመራለን፡፡” …. እንዴት በዚህ ንቀት ለወንድም አፍሪካዊያን ይነገራል፤ አፍሪካዊያንስ ምን ይሉናል አይባልም እንዴ፡፡ በየትኛው አቅም ነው በዓለም የእድገት ሰንጠረጅ ከውራዎቹ አንዱዋ ሆና የተፈረጀችው አገር አፍሪካን እመራለሁ ብላ የምትመኘው፡፡

        “በዱአችሁ አትርሱን፤ በዱአ እናምናለን” ብለው የቦረኖችን የእስልምና እምነት ተከታዮች ኦሮሞች ለማማመለል ሞክረዋል፡፡ ለአገር የአንድነትን መዝሙር መዘመሩ አይበጅም እንዴ? ለሥልጣን ሲዳል በአገር መቀለድ ተገቢ ነው እንዴ?

         “ኦሮሞ እስኪነቃ ነው እንጂ ሲነሳ ሚዳቁዋ አትበላንም፤ እኛ ዝሆኖች ነን፤ እንሰብራለን፤ እንበላለን፤ እንገዛለን” አሉዋ ዶክተር ዐቢይ፡፡

        “ይኸ ዘመን የእኛ ስለሆነ ……… አሳልፈን ሰጥተን ዳግም ወደ ባርነት ለመመለስ አንፈልግም…..፡፡”  በዚህ አነጋገር እጅግ የተዘመረለት ድሞክራሲ ፍትሃዊ ምርጫ አከተመለት፡፡ በምንም መልኩ ሥልጣን አሳልፈን አንሰጥም ብለው ወስነዋላ፡፡ ሲያልቅ አያምር ይላል ያገሬ ሰው፡፡

        ከላይ በጥቅስ የቀረቡት ሁሉ የተነገሩት የሠላም አባት ስለፍቅር ስለአብሮነት ጡዋትና ማታ ሲሰብኩ የቆዩት ስለሠላም የተገበሩትን በመገንዘብ የኖቤል የሠላም መዳሊያ የተሸለሙት የተከበሩት ሊቁ ዶክተር አብይ አህመድ ዓሊ ናቸው፡፡

         ዐቢይ የኛ ዴሞክራት፤ ዴሞክራት በሥልጣን ኮርቻ ላይ ለመቀመጥ የሕዝብን ፈቃድ በሕዝብ ድምጽ ባረጋገጠ  ጽንሰ ሃሳብ ብቻ መሆኑ ተሽቀንጥሮ ተጣለ፡፡ ከእንግዲህ ሥለጣን ከኦሮሞ እጅ አይወጣም ብሎ መደንፋት ለያዙት ሥልጣን የሚመጥን ንግግር  ይሆን ? ይህን ህዝብ ይፍረድ፡፡

     ኣረ ለመሆኑ የአገሪቱ የበላይ ባለሥልጣን የሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር በባህል ለተወረሰና በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ የበላይነቱን ላላረጋገጠለት   “አባ ገዳዎች” ተንበርክከው እጅ የሚነሱት ሥልጣን ለአባገዳዎች ለማስረከብ ታስቦ ይሆን እንዴ ? ያስጠረጥራል ! ኢትዮጵያን ከመከራ ይሰውራት፡፡

       “ይህ የባላገር ልጅ በቅሎ ያላወቀ፤”

       “ርካቡን ሳይረግጥ ሲወጣ ወደቀ” ሲል ነው መሰለኝ ሰውዬ  የተቀኘው፡፡

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡

       

Filed in: Amharic