>
2:07 am - Thursday December 9, 2021

አማራ ክልል ምን እየሆነ ነው? (ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን)

 አማራ ክልል ምን እየሆነ ነው?

ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከወደ አማራ ክልል ያልተለመደ ዓይነት አሰቃቂ ዜና እየተሰማ ነው። 

  ❶
ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን፤ ጠገዴ ወረዳ፣ ማይዳራ በሚባል ወንዝ አካባቢ ከብት በመጠበቅ ላይ የነበሩ እድሜያቸው ከ10-16 የሚሆኑ ስምንት ታዳጊዎች፤ ለቀናት ታግተው አጋቾቻቸው የጠየቁት ገንዘብ ሳይከፈል በመቅረቱ 6ቱ በጥይት ተገድለዋል። ሰባተኛው ልጅ ወደህክምና ከተወሰደ በኋላ በቀናት ልዩነት ሕይወቱ አልፏል።
 ❷
ይህንን አፈና እና ግድያ በተመለከተ የተጠየቁት የጠገዴ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ተወካይ ኃላፊ ኢንስፔክተር እሸቴ ገ/ማሪያም ከግድያው ጋር በተያያዘ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንና ፍለጋው ተጠናክሮ መቀጠሉን ለቢቢሲ አማርኛ ገልፀው ነበር።
ይሁን እንጂ “ማንነታቸው ያልታወቁ” የተባሉት አፋኞች እና ገዳዮች አሁንም እገታቸውን ቀጥለዋል። ባለፉት 2 ቀናትፐብቻ አርማጭሆ ውስጥ 6 ህፃናት እና 5 ገበሬዎች ተጠልፈው ተወስደዋል። ከነዚህ ውስጥ እስካሁን የተለቀቀው አንድ ህፃን ብቻ ነው። የቀሩትን ሰዎች ለማስለቀቅ በሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ እየተነገረ ነው።
 ❹
የተለቀቀው ሕፃን ከአርማጭሆ በደዌ ከተማ የተጠለፈው ትናንትና ነበር። ዛሬ “በቤተሰብ ድርድር” ለመለቀቅ መብቃቱን መረጃ ደርሶኛል።
 ❺
“በቤተሰብ ድርድር” ምን ማለት ነው?
በስፍራው የሚገኙና የሆነውን በቅርብ የሚያውቁ ሰዎችን በስልክ አነጋግራያቸው ነበር። ከበደዌ ከተማ የታገተው ሕፃን ወገኖች፣  “የአጋቹን እናትና ወንድም አሰሩ፤ ተደራደሩ፤ እና ሕፃኑን አስለቀቁ” ብለውኛል። ጥያቄዬን ቀጠልኩ፦
“ይህ ማለት ሕፃናቶቹንና ሌሎቹን ሰዎች አጋቾቹ ይታወቃሉ ማለት ነው?”
“በደንብ ይታወቃሉ። አጋቾቹ መንግስታዊ መዋቅር ውስጥ በደንብ ተንሰራፍተው እንዳሉ እናውቃለን” ብለውኛል።
አማራ ክልል ምን እየሆነ ነው? በውስጡ የተሰገሰጉ ወንጀለኞቾን እንዴት መመንጠር አቃተው? የአማራ ክልል አክቲቪስቶችስ በዚህ ፀያፍ ወንጀል ላይ አፋቸው የተሸበበው ለምንድነው?!! መልስ የሚሻ ጥያቄ ነው።
Filed in: Amharic