>
5:13 pm - Saturday April 18, 0589

ፖለቲካ፤ ፖለቲከኛ እና ሃይማኖት!!! (ቅዱስ ማህሉ)

ፖለቲካ፤ ፖለቲከኛ እና ሃይማኖት!!!

ቅዱስ ማህሉ

አብይ አሳምነው እስኪታሰር ቸኩሎ ነበር! 

ፍትህ መጽሄት

* ለአሳምነው እኔ የዋልኩለትን ውለታ የእናቱ ልጅ አልዋለለትም…. እኔ አልገደልኩትም

ዶ/ር አብይ
* ….መንጋው እባክህ ለከርስህ እና ለጥቂት ጥቅማ ጥቅም ብለህ በህይወት በሌለ ሰው ላይ አታጨብጭብ! ቤተክስርቲያንን ካዋረደ እና እያዋረደ ካለ እቡይ ጋር  ድራማ አትስራ። ድራማው ነገ ልጅህን እና ሃይማኖትህን እንዲሁም ራስህንም ጭምር እሳት ሆኖ ይበልሃል…
የመስከረም 4ቱ ሰልፍ እንዲቀር ያደረጉት ኮሚቴዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ልባቸው ከአብይ ጋር ያልቆረጠ ኦርቶዶክሳዊታን “የእንታገስ” ጥሪ ግፊትም ጭምር ነው። የኋለኞቹ ግፊት ለኮሚቴዎቹ ድጋፍ ነበር። እነዚያ ሰዎች የራሳቸውን ረስተው ኮሚቴውን ሲወቅሱ ነበር። የሰሩት ስህተት ከኮሚቴው የሚለየው የመንግስት ጫና በቀጥታ ያላረፈባቸው መሆኑ ብቻ ነው። ትናንት ኮሚቴውን ሲወቅሱ የነበሩት እነዚሁ ሰዎች ከኦርቶዶክ ጥቃት በላይ የአብይ ስም መቆሸሽ የሚያሳስባቸው መሆኑ ደግሞ “ዱባይ ቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታ አስፈቀደልን።” እያሉ አሁንም ቤተክርስቲያንን ደፍቀው አብይን ሊያነሱት ሲፍጨረጨሩ ማየት ይበቃል። ሃይማኖት እና ፖለቲካ እኩል ለድጋፍ የሚቆም አምድ የለውም። የፖለቲካ አምድ ተለዋዋጭ ነው። ፖለቲካ ሃይማኖት አይደለም። ስለዚህ ኦርቶዶክስ ዛሬ እንደትናንቱ እየተጠቃች ነው። ትናንት ሃይማኖትን አጥቂ የነበረው ፖለቲከኛ ዛሬ ለሃይማኖት ወገንኩ ሲል ደስ ካለን የተሳሳትነው እኛ ነን። የሱን ወገናዊነት እና ድጋፍ ሳይሆን እጁን እንዲያነሳ ብቻ መጠየቅ ነው። ይህን ተከትለን እንዲህ እንዲያ እያልን ሰውየውን ለማንቆለጳጰስ ከሞከርን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በቤተክርስቲያን ላይ እየቆመርን ያለነው እራሳችን ነን።
 ፖለቲከኛን እንደ ፖለቲካ ፍልስፍናችን እና ውስጣችን ስለሰውየው በተረዳው መጠን አካሄዱ ከጣመን መደገፍ በራሳችን ሚዛን ትክክል የሚመስለንን መንገድ ሲስት ወይም ወደ ትክክለኛ መንገድ የማይወስድ ጎዳና ሲከተል ደግሞ መደገፍ እና መተቸት ትክክለኛ አካሄድ ነው። እኔ ለማንኛውም ፖለቲከኛ ቋሚ ድጋፍ ኖሮኝ አያውቅም፤አይኖረኝምም። ይህ ግን የሚሰራው እንደኔ የፖለቲካ ድርጅት አባል ላልሆነ ሰው ነው። አባል አለመሆን በፓርቲው ፖሊሲ እና አስተዳደር ላይ በነጻነት መተቸት እንዲሁም የምትወደውን የመደገፍ እድል ይሰጣል። አባል ከሆንክ ግን ሃሳብህን እንዳሻህ ለማንሸራሸር ቢያንስ የፓርቲህን ህገደንብ የማክበር ግዴታ ይኖርብሃል። እናም የምወደውን ሃሳብ የሚያራምድ ፖለቲከኛን በተለይ ፓርቲን በተለያየ መንገድ መደገፌን እቀጥላለሁ። በጣም መስመር የሳተ ሲመስለኝ ደግሞ በተለይ ትኩረት ሰጥቼው የነበረ ከሆነ ማንም ቢሆን እነቅፈዋለሁ። እናም ትናንት ቤተክርስቲያን አፈረሰ ያላችሁትን ሰው ስልጣን እና ሃላፊነት በሌለበት ስፍራ ላይ የሌለ ነገር ሰጠን ብላችሁ ምንም የፖለቲካ ትርፍ አታገኙም። ቤተክርስቲያኒቷ ላይ ፊትለፊት የማይታይ የጥፋት ክንዳችሁን ከማሳረፍ በቀር!!
አብይ አሳምነው እስኪታሰር ቸኩሎ ነበር! 
አብይ አህመድ በአማርኛ ተናግሮ እስካሁን ያልዋሸው ምንም ነገር የለም። ዛሬ ስለ ጀነራል አሳምነው ጽጌ የተናገረውም ነጭ ውሽት ነው። እሱ እንዳለው ሚስቴ እና ልጆቼ አሜሪካ ለስደት የተዳረጉት ጄነራል አሳምነው ጽጌ እንዳይታሰር ጥረት በማድረጌ ምክንያት ነው ይላል። ስብሰባው ላይ የተሳተፈው መንጋም አጨበጨበ። መንጋውን ከየት እና እንዴት እንደተሰባሰበ አይታወቅም። ተመስገን ደሳለኝ ከትቂት ቀራት በፊት በፍትህ መጽሄት ያስነበብን ግን ተቃራኒውን ነው። አብይ አህመድ ጀነራል አሳምነው ጽጌ ሊታሰር አንድ ቀን ሲቀረውግ አሳምነው ይኖርበት የነበረውን የመንግስት ቤት ሂዶ እንደጎበኘ እና በማግስቱ ሲታሰር ቤቱ ውስጥ እንደገባበት ነው። እንግዲህ ይህ ቲያትረኛ አሳምነው እስኪታሰር ድረስ ምን ያህል እንደቸኮለ እና ጓጉቶ እንደነበር ከዚህ በላይ ማስረጃ ከየት ይመጣል። መንጋው እባክህ ለከርስህ እና ለጥቂት ጥቅማ ጥቅም ብለህ በህይወት በሌለ ሰው ላይ አታጨብጭብ! ቤተክስርቲያንን ካዋረደ እና እያዋረደ ካለ እቡይ ጋር  ድራማ አትስራ። ድራማው ነገ ልጅህን እና ሃይማኖትህን እንዲሁም ራስህንም ጭምር እሳት ሆኖ ይበልሃል። ፖለቲካ መደግፍ እና አለመደገፍም ይቻላል። ከደገፉ ግን ሃይማኖትህን ከሚነካ ጋር ዛሬ ቀይ መብራት ነገ አረንጓዴ እያበራህ አትደንስ። ዥዋዥዌ በፖለቲካ የተፈቀደ እና በመድረኩ ላይ የጤናማነት ምልክት ነው። የምትደግፈው ፓርቲ እና ፖለቲከኛ ሲቆም ወይም ከምትደግፍበት መሰረት ሲንሸራተት አብረህ የመቆም ግዴታ የለብህም። ወይ እንዲስተካከል ትተቸዋለህ።ካልሆነም ጥለህው ትሄዳለህ። ይህ ግን ሃይማኖትህን ከነካ እና ካወረደ ጋር የምታድርገው አይደለም። በዚያ ጨዋታ ከጀመርክ ዛሬ ልታቆመው የምትችለውን ጥቃት ነገ ብዙ ዋጋ ትከፍልበታለህ። ዝም ብለህ ለገዳዩም፣ለአዋራጁም እንዲሁ አታጨብጭብ። በነገራችን ላይ ዛሬ አብይ ስለ ጀነራል አሳምነው ጽጌ  ያወራውን በኦሮምኛ ቢያወራው አምነው ነበር። ስለዚያ ቢያወራ በትክክለኛው አገላለጽ  “አማራን እና መሪዎቹ ሰብረናቸዋል። ” እንደሚል አልጠራጠም።
ከታች ያለው ምስል የነገዋ ፍትህ መጽሄት ሽፋን ነው።ሰውየው እየሰመጠ እንኳ እውነት ጋር መታረቅ የማይችል የውሸት ሱስ የተጣባው መሆኑን ስለሚያመላክት ተጠቀምኩ።
Filed in: Amharic