>

ወሬው፡– እውነት ነው? ወይስ ውሸት? (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም)

ወሬው፡– እውነት ነው? ወይስ ውሸት?

 

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

 

 

በጂጂጋ፣ በጂማና በአጋሮ፣ በቦረና … ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብ የድጋፍ ሰልፎች ተደርገዋል ይባላል፤ በአንጻሩ ሌሎች የፖሊቲካ ቡድኖች ስብሰባ እንዳያደርጉ ተከልክለዋል፤ የሞከሩም ታስረዋል ይባላል፤ የሕዝብ ነጻነት በታወጀበት አገር ሀሳብን መግለጽ መሠረታዊ መብት ነው፤ አንዳንድ ያነጋገርኋቸው ወዳጆቼ ከልካዩ መንግሥት አይደለም ይላሉ፤ እንደማምነው መልሱ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በታወጀበት አገር ማንም ቢሆን የዜግነት መብት ያለው ሕዝብ በሕግ ያልተከለከለ ሀሳቡን እንዳይገልጽ የሚያደርግ እርምጃ ለመውሰድ ሥልጣን የለውም፤ እንግዲህ የለመድነው አምባገነንነት እየተተከለ ነው ወይ? ብሎ ለመጠየቅና መልሱን በሕግ አስገድዶ ማግኘት የሕዝቡ መብት ይመስለኛል፤እንግዲህ ወሬው ትክክል ከሆነ ማለትም አገሩ ለአንዳንዶች ክፍት፣ ለአንዳንዶች ደግሞ ዝግ ከሆነ ዓቃቤ ሕጉ የያዘው የሕግ ሚዛን ተሰብሯል ማለት ነው፤ እንዲህ ከሆነ ይቺ ባቄላ ያደረች እንደሆን አትቆረጠምም ልንል ነው!

Filed in: Amharic