>

መጪው ምርጫ ቅርጫ እንዳይሆን...! (ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)

መጪው ምርጫ ቅርጫ እንዳይሆን…!

ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
እኔ የብልጽግና ፓርቲ (የለውጡ) ደጋፊ ነኝ፤ ሰፊ ተቀባይነት እንዲያገኝ፣ በምርጫ እንዲያሸንፍ እፈልጋለሁ፡፡ ብቻውን ጋልቦ እንዲቀድም፣ ብቻውን ተወዳድሮ እንዲመረጥ ግን አልፈልግም፤ አልፈቅድምም፡፡ ይህ ስቃወመው የኖርኩት የዴሞክራሲ ሾተላይ ነውና አሁንም ልደግፈው አልችልም!!!
 
 
“ሰሞኑን ደምቆ እንደምንመለከተው ለዶ/ር አብይ/የብልጽግና ፓርቲ በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች (ትግራይን አይጨምርም) የድጋፍ ሰልፍ እየተደረገ ነው። የሚያስፈራው የብልጽግና ፓርቲ ተቀባይነት ማግኘት አይደለም፤ በእነዚህ ቦታዎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ማድረግ እንኳን መቸገራቸው ነው፡፡
.
እኔ የብልጽግና ፓርቲ (የለውጡ) ደጋፊ ነኝ፤ ሰፊ ተቀባይነት እንዲያገኝ፣ በምርጫ እንዲያሸንፍ እፈልጋለሁ፡፡ ብቻውን ጋልቦ እንዲቀድም፣ ብቻውን ተወዳድሮ እንዲመረጥ ግን አልፈልግም፤ አልፈቅድምም፡፡ ይህ ስቃወመው የኖርኩት የዴሞክራሲ ሾተላይ ነውና አሁንም ልደግፈው አልችልም፡፡
.
ዜግነትን መሰረት አድርገው የተደራጁ ፓርቲዎች ብሄርን መሰረት አድርገው በተደራጁ ፓርቲዎች ክልል ቢሮ መክፈት፣ ስብሰባ ጠርቶ ዜጎችን ማወያየት አልቻሉም፡፡ በኦሮምያም ቢሆን መሰብሰብና መሰለፍ የውሀ መንገድ እየሆነ ያለው ለብልጽግና ነው፡፡
ይህ በዚሁ ከቀጠለ መጪው ምርጫ በየክልሉ እና ዞኑ አብላጫ ቁጥር ያላቸውን ብሄረሰቦች የሚወክሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሀገሪቱን በምርጫ ስም የሚቃረጡበት እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ ከምርጫው የሚጠበቀውን ሰላምና ዲሞክራሲም አያመጣም፡፡
በመሆኑም ፓርቲዎች በመላው ሀገሪቱ ተንቀሳቅሰው፣ ዜጎችን የማወያየትና ፕሮግራማቸውን የማስተዋወቅ ፖለቲካዊ መብታቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ምርጫን ማካሄድ ትርጉም አይኖረውም፡፡”
Filed in: Amharic