>

ሼህ ሆጀሌ አልሀሰን ሲታወሱ!!! (መስፍን ሚካኤል)

ሼህ ሆጀሌ አልሀሰን ሲታወሱ!!!

መስፍን ሚካኤል
ሼህ ሆጀሌ በአጼ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በአድዋ ጦርነት ላይ 5000 ወታደርና ፈረሰኛ በማሳተፍ ለድሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ
የነበራቸው ሲሆን በቀጣይ በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመንም የኢጣሊያ ጦር ዳግም ሀገራቸንን ሲወር ወደ ጦርነቱ ዘምተው በ1931
ዓ.ም. በጥይት ተመተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል!!!
ሼህ ሆጀሌ የቤንሻንጉል ገዢ ከነበሩት ከአባታቸው ሼህ አልሀሰን መሐመድ እና ከእናታቸው ወይዘሮ ፈዳይል በ1817 ዓ.ም
በቤንሻንጉል በአሶሳ ከተማ ተወለዱ፡፡
.
እድሜያቸውም ለትምህርት ሲደርስ ‘የኸላዋ’ ትምህርት እየተከታተሉ አደጉ፡፡ ሼህ ሆጀሌ በትምህርት ከማደጋቸውም ባሸገር በአደን
ብቃታቸውና በጀግንነታቸው ስማቸው እየገነነ በመምጣቱ አባታቸው የጦር መሪ አረጓቸው፤ ከዚያም በኋላ ብዙም ሳይቆዩ
ከደርቡሾች ጋር በተደረገ ጦርነት አባታቸውን በማጣታቸው ጦራቸውን አጠናክረው በአካባቢው የነበረውን የደርቡሽ ጦር በመውጋት
የአባታቸው ወንበር ላይ በመቀመጥ የቤንሻንጉል ገዢ ሆኑ።
.
በቀጣይም አጼ ምኒልክ ከ1889 እስከ 1890 ዓ.ም. ባለው ጊዜ በየክልሉ ራስቸው እየዘመቱም ሆኑ መኳንንቶቻቸውን እያዘመቱ
ገዢዎችን በማስገበር በማዕከላዊ መንግሥት የምትተዳደር አንዲት ኢትዮጵያን በሚፈጥሩ ጊዜ ሼህ ሆጀሌ በሠላማዊ መንገድ
ለአጼ ምኒልክ ለመገበር ተስማሙ።
.
አጼ ምኒልክም ሼህ ሆጀሌን ሸልመው የራስነት ማዕረግ ሰጥተው በቤንሻንጉል ላይ ሹመታቸውን አጸደቁላቸው፡፡
.
ሼህ ሆጀሌም የራስነት ማዕረጉ ይቅርብኝ “ሼህ” ራሱ ማዕረግ ነውና በእሱ መጠራትን እመርጣለሁ በማለታቸው እስከ ሕይወታቸው
ፍጻሜ በዚያው ስም ሲጠሩ ኖሩ፡፡
.
ሼህ ሆጀሌ በኃላ ላይ ከታወቁ የጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪዎች አንዱ ለመሆን በመቻላቸው ከአሶሳ ሲመጡ የሚያርፉበትና
ቤተሰቦቻቸውንም ለማኖር የሚያስችላቸው ሰፊ የከተማ ቦታ አዲስ አበባ ውስጥ በአጼ ምኒሊክ ተሰጣቸው፡፡
.
በዚሁ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ሩፋኤል አካባቢ በሚገኘው ይዞታቸው በ1880 አካባቢ ያሰሩት መኖሪያ ቤታቸው ይገኛል፡፡ ቤቱ
የህንድ የምንድህስና ኪነጥበብ ይታይበታል፡፡ ዛሬም በከፊል የቀበሌ ነዋሪዎች እና በከፊል ወራሾች ይኖሩበታል፡፡
.
ሼህ ሆጀሌ በአጼ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት በአድዋ ጦርነት ላይ 5000 ወታደርና ፈረሰኛ በማሳተፍ ለድሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ
የነበራቸው ሲሆን በቀጣይ በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመንም የኢጣሊያ ጦር ዳግም ሀገራቸንን ሲወር ወደ ጦርነቱ ዘምተው በ1931
ዓ.ም. በጥይት ተመተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
.
ከአምስት ዓመቱ የኢጣሊያ ወራራ በኋላም በአዲስ አበባ ከተማ ከቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን አጠገብ አንስቶ እስከ አርበኞች
መንገድ የሚደርሰው “የሼኽ ሆጄሌ መንገድ ” ተብሎ ተሰይሞ ነበር።በዚያው አካባቢም ራሳቸው ያሰሩት ቤት በመኖሩ ሰፈሩ ራሱ
እስከአሁን( ሸጎሌ) ተብሎ ይጠራል፡፡
Filed in: Amharic