>

ቤተክርስትያንን በመክዳት የተጀመረው የ "አቡነ" ሳዊሮስ ጉዞ አገር ወደመክዳት አድጓል!!! (መምህር ታሪኩ አበራ)

ቤተክርስትያንን በመክዳት የተጀመረው የ “አቡነ” ሳዊሮስ ጉዞ አገር ወደመክዳት አድጓል!!!

መምህር ታሪኩ አበራ
ቅዱስ ሲኖዶስ የ”አቡነ” ሳዊሮስን ጵጵስና በአስቸኳይ  ሊይዝ ይገባል!!†
** አፈንጋጩ “አባ” ሳዊሮስ ከሊቀ ጳጳስነት ወደ ሊቀ ባንዳነት በመለወጥ  ከግብፅ ጋር የጀመሩት  ድብቅ  ምስጢር ተጋለጠ!!!
 
* አባ ሳዊሮስ  ጀዋር መሐመድ ከግብፅ ጋር የጠበቀ ግኑኝነት እንዳለውና ከግብፅ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር ድርድር ላይ እንደሆኑም ተናገሩ ።*
በትግራይም ሌላ ተገንጣይ ቤተክህነት እናቋቁማለን የሚሉ አማጽያን በቤተክርስቲያን ላይ መነሳታቸውንም እየሰማን ነው!
ግብፅ ለአንድ ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት ያህል ጳጳሳትን እየሾመች ለኢትዮጵያ ትልክ የነበረው በርካታ ወርቅ፣ብር፣የከበሩ ማዕድናትና የዝሆን ጥርስ እያስገበረችን ነበር፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ የዓብይን ግደብ ለማስጀመር  ለመጀመሪያ ጊዜ ሲነሱ ግብጽ ጳጳስ አልክላችሁም ብላ ስታስፈራራ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ የራሷን ሲኖዶስ አቋቁማ የመጀመሪያውን ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስን ፓትርያርክ አድርጋ ሾማለች።
ዛሬ ላይ ግብጽ በጎን ለኤርትራ ፓትርያርክ በመሾም ኢትዮጵያን ለመበቀል እንደምትወራጭ ሁሉ ባንዳው “አቡነ” ሳዊሮስን የኦሮሚያ ፓትርያርክ ብላ ሹም ሀገር ለመከፋፈል ሴራ መጎንጎኗን ቀጥላለች።
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ አሳፋሪ ሊባል በሚችል መልኩ ከቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ አባላት ጋር ቁጭ ብለው የእነ ቄስ በላይ ሥልጣነ ክህነት እንዲያዝ የወሰኑትን ውሳኔ በማግስቱ ዓይናቸውን በጨው አጥበው ቅጥፈትና ውሸት በተሞላበት ንግግር የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ የተሳሳተና ተቀባይነት የሌለው በጥቂት ሰዎች ግፊት የተወሰነ ነው በማለት በOMN ቲቪ ላይ ቀርበው
እግዚአብሔርን ሳይፈሩ ሰውንም ሳያፍሩ ሲደሰኩሩ ነበር ።
የዕለቱ አሳፋሪ ንግግር ማንነታቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳየና ከጸጋ መንፈስ ቅዱስ ተገፈው እርቃናቸውን ካስቀራቸው መግለጫ ውስጥ የቅዱስ ሲኖዶስን
ውሳኔ “የትግራይ ጳጳሳት አልደገፉትም” የምትለዋ  ንግግራቸውና ስለ ቀድሞው የውጭ ሲኖዶስ ታሪክ ሲናገሩ “አራት ሆነው ከሀገር ወጥተው ሃያ አራት” ሆነው ተመለሱ የምትለዋ ንግግራቸው የሚሰመርበት ነው ።
ከOMN መግለጫ በኋላ የእነ አባ ሳዊሮስ አሰላለፍ ተቀይሯል ከአሳፋሪውና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ከጣሰው መግለጫ በኋላ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ በቋሚ ሲኖዶስ እንዲሁም በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንም ዓይነት ጥያቄ
አልቀረበባቸውም ዝም ጭጭ ነው የተባሉት። እዚህ ላይ ሁላችን የምንጠረጥረውና  ደግሞም  የምንጠይቀው ወሳኝ ነጥብ አለ።
የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ኃላፊዎችና የፓትርያርኩ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እነማን ናቸው?
መልሱን አፈንጋጩና አማጺው አባ ሳዊሮስ በመግለጫቸው ላይ የትግራይ ጳጳሳት ከኛ ጋር ናቸው ካሉት ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው። ከዛ በተዋህዶ ላይ እየተሴረ ያለውን ሴራና ከውስብስቡ የቤተ ክርስቲያን ፈተና በስተጀርባ ያሉትን ስውር እጆች እነማን እንደሆኑ አስላውና ድረስበት።
በጣም የሚገርመው ነገር የእነ አባ ሳዊሮስ መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስን ምልዓተ ጉባዔ ውሳኔ የሻረና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ ከቅዱስ ሲኖዶስ
አባልነት እስከ ማሰረዝ የሚደርስ ከባድ ክህደትና ጥፋት ሆኖ ሳለ በየትኛውም ደረጃ ያለ የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ጠርቶ ማብራሪያ የጠየቃቸው አካል የለም። እነ አባ ሳዊሮስ ግን ጭራሽ ከሰሞኑ ሌሎች ዘጠኝ የትግራይ ጳጳሳትን
ይዘን መግለጫ እንሰጣለን እያሉ እየፎከሩ ነው።በትግራይም ሌላ ተገንጣይ ቤተክህነት እናቋቁማለን የሚሉ አማጽያን በቤተክርስቲያን ላይ መነሳታቸውንም እየሰማን ነው።
ምን ይሄ ብቻ አባ ሳዊሮስ የባጥ የቆጡን ሲቀባጥሩ ከባድ ምስጢር አምልጧቸዋል ይሄውም ግብፆች የጀዋር መሐመድ የቅርብ ወዳጅ እንደሆኑና
በጀዋር መሐመድ አመቻችነት አባ ሳዊሮስን የሚያግዙ በጎጥና በዘረኝነት መንፈስ የተለከፉ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የካዱ ለሆዳቸው ያደሩ ህሊናቸውን የሸጡ መነኮሳት ግብፅ ድረስ ይዘው ሄደው ጵጵስና እደሚያሾማቸውና ከግብፅ
ጵጵስና ተሹመው የሚመጡና ሀገር ቤት ካሉ ሰቃልያነ ቤተ ክርስቲያን ጋር ተሰባስበው የራሳቸው ፓትርያርክ እንደሚሾሙ እየቃዡ ነው።
ኢትዮጵያዊ ሁሉ ልብ በል!!  ለረጅም ጊዜ እነ ጀዋር የግብፅ ተላላኪ ናቸው ሲባሉና በወሬ ሲታሙ እንሰማ ነበር አሁን ግን እድሜ ለአባ ሳዊሮስ ሃሜቱና ግምቱ እውነት መሆኑና እንደ ጋሪ ፈረስ እየጋለባቸው ያለው ጀዋር መሐመድ ከግብፅ መንግስት ጋር
ተነጋግሮ ጳጳሳት ሊያሾምላቸው መሆኑኑን እግዚአብሔር ልባቸውን ነስቶ፣አንደበታቸውን ከፍቶ፣ ፊታቸውን ፀፍቶ አናግሯቸዋል ።
አንባቢ ሆይ!!  ይህን መረጃ እንደተራ ነገር የምታይ ከሆነ አንተ ጀዋርንም ግብፅንም አታውቃቸውም ማለት ነው ወዳጄ ግብፆች በዓባይ የመጣ በሕይወታቸው የመጣ እንደሆ እዚህ ጋር ልብ ልንል ይገባል ምንም ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አይሉም ።
ያውም የህልውና ጉዳይ ነው ኢትዮጵያን ለመከፋፈልና የሁከትና የብጥብጥ ማዕከል እንድትሆን ከማድረግ ወደኋላ አይሉም።
ግብፅ ለአንድ ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት ያህል ጳጳሳትን እየሾመች ለኢትዮጵያ ትልክ የነበረው በርካታ ወርቅ፣ብር፣የከበሩ ማዕድናትና የዝሆን ጥርስ እያስገበረችን ነበር፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ የዓብይን ግደብ ለማስጀመር  ለመጀመሪያ ጊዜ ሲነሱ ግብጽ ጳጳስ አልክላችሁም ብላ ስታስፈራራ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ የራሷን ሲኖዶስ አቋቁማ የመጀመሪያውን ፓትርያርክ አቡነ ባስልዮስን ፓትርያርክ አድርጋ ሾማለች።
ዛሬ ላይ ግብጽ በጎን ለኤርትራ ፓትርያርክ በመሾም ኢትዮጵያን ለመበቀል እንደምትወራጭ ሁሉ ባንዳው “አቡነ” ሳዊሮስን የኦሮሚያ ፓትርያርክ ብላ ሹም ሀገር ለመከፋፈል ሴራ መጎንጎኗን ቀጥላለች።
እናም አባ ሳዊሮስ በዓይናችን እያየን በጆሮአችን እየሰማን ከሊቀ ጳጳስነት ወደ ሊቀ ባንዳነት የቁልቁለት ጉዞውን ተያይዘውታል።
ያደቆነ…… እንዲል ብሂሉ እነ አባ ሳዊሮስ የለከፋቸው በሽታ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በመካድ ጀምሮ እነሆ አሁን ሀገርን ወደ መክዳት ተመነድጓል ።
ህሊና ባዶ ሲሆንና ፀጋ እግዚአብሔር ሲለይ እንደዚህ ለማይረባ አዕምሮ ተላልፎ ይሰጣል። የሚያሳዝነው ነገር ይሄ ሁሉ ክህደትና ቅሌት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን
ለመከፋፈል ነው።
በመጨረሻም ጥያቄ ለአንባብያን
 
1,የአባ ሳዊሮስ ወአቶ በላይ መኮነን ግሩፕ + የትግራይ ጳጳሳትና የቤ ክህነቱ ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት + ጀዋር መሐመድና መሰሎቹ + ግብፅ የእነዚህ ጥምረትና ሴራ የት ድረስ ያስኬዳቸዋል?
በቀደመው በአባቶቻችን ዘመን ለግራኝ አህመድ፣ ለዮዲት ጉዲት ፣ ለፋሺስት፣ ለሐሳውያንና ለቀሳጥያን  ያልተንበረከከች ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ዛሬስ የእነዚህን ባንዳዎች ሴራ እንዴት ታልፈው ይሆን?
ይቆየን
ዲ/ን አብርሃም ወርቁ
ለሌሎችም ሼር አድርጉት።
Filed in: Amharic