>

የኮሮናን ስርጭት... ሳውዲ በሰዓት እላፊ፣  ኩዌት በቅጣት ፣ፑቲን በአንበሳ፣ ጣልያን በምስል...!!!  (ነቢዩ ሲራክ)

የማለዳ ወግ…

 

የኮሮናን ስርጭት… ሳውዲ በሰዓት እላፊ፣  ኩዌት በቅጣት ፣ፑቲን በአንበሳ፣ ጣልያን በምስል…!!! 

 

ነቢዩ ሲራክ 
* ሳውዲና ኩዌት የሰአት እላፊ ደነገጉ  ! 
* የኩዌት 10,000 ዲናር ቅጣት!
* የሩሲያው ፑቲን አንበሳ ማሰማራት !
* ጣሊያን ተማጽኖዋን በምስል አቀረበች..!!!
 
   በመላው አለም በአስገራሚ ፍጥነት እየተሰራጨ ያለውን የኮሮና ተዋስዕ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት በመጨመር ላይ ይገኛል። ስርጭቱን ወደ መራሄ መንግስታት ከፍ እያለ አለምን ሲያምሳት መራሄ መንግስታትም ስርጭቱን ለመግታት ጠበቅና መረር ያሉ እርጃዎች መውሰድ መጀመራቸው ይጠቀሳል።
 ሳውዲ
 በኮሮና ጥቃት ስጋት ላይ የወደቁት  ሳውዲ አረቢያ እና ኩዌት የኮሮናን ስርጭት ለመከላከል የሰአት እላፊ ደንግገዋል። ከዛሬ መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓም ተግባራዊ የሚደረገው የሰዓት እላፊ ገደብ  ለ21 ቀናት የሚቆይ መሆኑ ተጠቅሷል።  የሰዓት እላፊው የሚጀምረው ከምሽቱ 1 ሰአት ወይም 7 pm እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ወይም 6 am ይሆናል። በሌላ አገላለጽ ጀምሽት እስከ ማለዳ ወይም ከመቅሪብ  እስከ ፈጅር ጸሎት ባለው ሰዓት መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን ከሳውዲው ንጉሱ ሰልማን ቢን አብድልአዚዝ የተላለፈው ትዕዛዝ ያስረዳል።
የኩዌት ቅጣት … 
ሀገረ ኩዌት በበኩሏ የኮሮናን ስርጭት ለመከላከል ተመሳሳይ የሰአት እላፊ እገዳ አውጃለች። የኩዌት መንግስት በትናንትናው  እለት ባሰራጨው መረጃ መሰረት የሰአት እላፊውን ተላልፎ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ 10,000 ከኩዌት ዲናር እስከ ሶስት አመት የሚደርስ ከባድ የእስራት ይጠብቃቸዋል።
ጣሊያን  በምስል..!!!
ቀደም ሲል የጣልያኑ ጠ/ሚ/ር ጁሴፔ ኮንቴ  “ወረርሽኙን መቆጣጠር አቃተን፤ በአካልም ሞትን፤ በአዕምሮ ዝለትም ሞትን፤ ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም፤ በምድር ላይ ያሉ መፍትሄዎችን ሁሉ ተጠቅመን ጨረስን፤ አሁን ያለን መፍትሄ ሊመጣ የሚችለው ከሰማይ ብቻ ነው።” የሚል ልብ የሚነካ ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል፤አሁን በጣልያን ያንኑ ንግግራቸውን ገቢራዊ ያደረገ የተማጽኑ ምስል በጣሊያኑ አርቲስት ተቀርጿል፡፡
🟢
ይህ የኮሮና ቫይረስን በምስል ያስቀመጠው ጣሊያናዊ ሰአሊ በሀገሪቱ ቫይረሱ ከቁጥጥር ውጭ በመሆኑ መፍትሄውን ፈጣሪ ያመጣው ዘንድ የሚማፀን ነው ተብሏል።አምላካችን ሆይ ❗አቤቱ እንደቸርነትህ ጎብኛቸው የመከራው ዶፍ ይብቃ ማዳንህ በሁላችላይ ይሁን…በፊትህ የሚቆም ፅኑ ልብ ስጠን…!!!
የሩሲያ አንበሳ… 
በሌላኛው የእስያ የአለም ክፍል ሀገረ ሩስያ የሰማነው የሰዓት እላፊና ቅጣቱ ደግሞ ያስገርማል። የሩሲያው የበላይ ፕሬዚደንት ፑቲን የሰአት እላፊ ደንግገው ከተማዋን የሚጠብቁ ከ500 የሚደርሱ ባለ ግርማ አንበሶች ማሰማራታቸውን ሰምተን እግዚ ኦ ብለን በአግራሞት አልፈነዋል።
   የሩሲያው አምበሳ ስምሪት ቢያስፈራ ቢያስፈነግም የኩዌት መንግስት ያስተላለፈው የ 10,000 የኩዌት ዲናር መቀጮው  አንበሳና ነብር በከተማው ፈትቶ ከማሰማራት የተናነሰ የሚገባን ምንዛሬውን ያሰላነው እንደሆነ ነው።
የጀርመን ቻንስለር …
የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ ሜርክል የግል ሐኪሟ በኮሮና ቫይረስ በመጠቃቱ ራሷን በመኖሪያ ቤቷ ለይታ ተቀምጣለች። ምክንያቱም ከሐኪሟ ጋር ከቀናት በፊት ኮንታክት ስለነበራት ነው። ስለዚህ በሂደት ራሷን በምርመራ እስክታውቀው ድረስ “በቫይረሱ ተይዛለች” የሚለው የአንዳንዶቻችን ድምዳሜ ስህተት ይሆናል።
ህግ እናክብር !
   ኮሮናን ለመከላከል የሚወሰዱ ቅጣቶች ጠበቅና መረር ያሉ መሆናቸው ሀገራት ስርጭቱን ለማሳየት የሞት ሽረት እርምጃ መጀመራቸውን ነው። ወገኖቸ ወደድንም ጠላንም ፈራንም አልፈራንም ስርጭቱን ለመከላከል በየሀገራቱ መንግስት የሚተላለፉትን መመሪያና ህጎች ማክበር ጠቃሚና ተገቢ ነው እላለሁ ።የተደነገገውን ሰዓት እላፊውን አክብሩ ፣ ህግ አናክብር  !
ቸር ጊዜን ይመጣ ዘንድ በጸሎት እንጽና  ! 
Filed in: Amharic