>

ህወሓት የኮረና ወረርሽኝንም በፉከራና በፕሮፓጋንዳ ልታጠፋው ቆርጣለች¡¡¡  (አሰግድ ገብረ ሥላሴ)

ህወሓት የኮረና ወረርሽኝንም በፉከራና በፕሮፓጋንዳ ልታጠፋው ቆርጣለች¡¡¡ 

አሰግድ ገብረ ሥላሴ

“አሁንም እንደድሮው ታሪክ እንሰራለን!!!

ዶ/ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል 
  * የካቲት 11 ለማክበር እኮ የዘመናችን ካድሬዎች እነ ስብሀት ነጋ ፣ስዩም መስፍን ፣ኣባይ ጸሀዬ ፣ ጸጋይ በርሀ ኣባዲ ዞሞ እስከ ገጠር ቀበሌዎች ወርደው እንደ ተራ የቀበሌ ካድሬ  ቀስቅሰዋል ።ታድያ በዝህች ቀውጥ ጊዜ ለምን ድምጻቸው ከውሀ እንደጠለቀች አይጥ  ጠፋች ? ምናልባች የኮረና ቫይረስ አዛውንት እየመረጠ ነው የሚቀጥፍ ስለተባለ ሰግተው በፕላኔት ሆቴል  የመከላከያ ከሚካል ረጭተው ለብቻቸው እድሚ ለማስቀጠል ተደብቀው ተዘግተው ይሆን ?ስልጣንና ገንዘብ ክፉ  ታድያ ህዝብ ከሌለ ከማን ሊኖሩ  ያስቡ ይሆን ? 
—-
ዶክተር ደብረጽዮን  በሽታው ለመከላከል ታሪክ ንሰራለን ብለህ ሞፎከር ማሰማትህ መልካም ምኞች ነው ። ግን አደጋው ይቅርና በኛ ደረጃ በነዛ አለምን የሚያንጥቅጡ የበለጸጉ ሀያላን  አገሮች  ለመከላከል እያደረጉት ያሉ ዝግጅት  ተመልከት ፤ የሀገራቸው መርከቦች ፣ሆቴሎች መዝናናዎች ፣ስተዴሞች ፣በሁሉም  ደረጃ  ያሉ ት /ቤቶች ፣መሰብሰብያ አዳራሾች ።የመንግስት፣የግል ድርጅት ምስራቤቶች  ወ  ዘ ተ በኮረና ቫይረስ የተለከፉ ተኝተው ሊታከሙበት፣  ሊያጋጉሙበት  ለሚችሉ  ዝግጅት በማድረግ  ሌት ተቀን እየተረባረቡ ይገኛሉ  ። በተጨማሪ  ሁሉም እንድትሪያቸው በሙሉ የቫይረሱ መከላከያ ቁሳቁስ ማምረቻ ፣መድሀኒት ፋብሪካ በማድረግ ለከፋ አደጋ ለመከላከል በሙሉ አቅማቸው ይዘጋጃሉ ።ለመከላከሉ  የሚጠቅሙ እንደውሀ ሌሎችም መሰረተልማት ይሰራሉ ።  የሀገሮች መሪዎች ዋጋው በትርሊዮን የሚገመት ባጀት በፓርላማዎቻቸው ሊያጸድቁ  እየጠየቁ  ይታያሉ ።በሀገራችንስ ምን እየተሰራ ነው ።በገጠር ህዝባችን በአንድ የገጠር ገበያ በየሳምንቱ  ያሉ ገበያዎች  በኣንድ ቅዳሜ (ሰኞ )  ብቻ በአስር ሽ የሚቆጠር ህዝብ ይሰበሰባል ።በኣከባቢው ውሀ የሚባል የለም  ።በገበያ የተሰበሰበ ህዝብ ጠላ ስለሚጠጣ  በአንድ ኩባያ ሳይታጠብ በአስር የሚቆጠሩ ሰዎች ስለሚጠጡበት ለወረርሽን  ማስፋፋት ተጠቃሽ ነው ።በአሁኑ ጊዜ ከገጠር እስከ ከተማ ውሀ የለም ።የምንነሩባት መቐለ ከተማ እእኳን  ከግማሽ ምሌን በላይ ህዝብ  የተሰበሰበባት  ውሀ  የለንም  ሸታለች ። ፣ቡዙ ህዝብ የሚሰበሰብባቸው ትላልቅ ከተሞች በሽረ ፣ሕሞራ ፣አክሱም ፣ዓዲ ግራት ፣ በውቅሮ ፣በውቅሮ ፣ ተንቤን ዓብይ ዓዲ ፣አለማጣ ፣ተመሳሳይ ሁኔታ ነው ያለው ። ሀሰት የምትሉ ከሆነ ሆቴሎች ፣ቁርስ ቤቶች ፣መስራቤቶች ዝራችሁ ፈትሹ ፣በህዝብ መኖሪያ ቤትም ወሀ ከእለታት አንድ ቀን ውሀ ስለሚያገኙ አብዛኛው ህዝብ ቤቱ ሸታል ። በሁሉም ከተሞች ያለ ድሀ ማህበረሰብ በውሀ እጦት ተሸግራል ።ቤት አካራዮች ለተካራዮችን ውሀ ያግዱዋቸዋል እነዚህም ምክር ያስፈልጋቸዋል ።
 በክልላችን ያሉ የውሀ ሀፍት ቢሮ የትግራይ እርዳታ ማህበር ተከዜ ውሀ ቁፋሮ  ፣የኤፈርት ትልቁ የቁፈራ ኩባንያ  ኢዛና ፣ሌሎች የግል ድርጅቶች የክልል መንግስት ወደ ውሀ ቁፋሮ ሊያሳማሩዋቸው እየቻለ ሲንቀሳቀሱ  አናይም ። በትግራይ ወረዳዎች  የሚገኙ የተቆፈሩ ጉድጓዶች ጽገና ተደርጎላቸው ለአገልግሎት ሲደርሱ አይታዩም ። በየሚዲያው መስኮት እየወጣችሁ  ፣ውሀ ታጠቡ ጓንት ተጠቀሙ ፣ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ አትገኙ ብላችሁ ስትናገሩ  የተዛጋጀ ነገር በእጃችሁ የተጨበጠ ነገር እንዳላችሁ  ትመስላላችሁ ። ታድያ ዶ /ደብረጽዮን አሁንም እንድድሮው ታሪክ እንሰራለን ብለህ በሚዲያ ስትቀርብ ምን ተይዞ ነው ያልኩህ ዝግጅታችሁ ባዶ ዲስኩር ሆኖ ስላየሁት ነው ።
ዶ/ ደብረጽዮን  ትላንትና በክፍል 2 ጽሁፌ ጠቁሜ እንዳለፍኩት አሁንም የዚሁ አመት የልማት ባጀት ካለ ፣የኤፈርት ተቀማጭ ገንዘብ ስላላቹ ባለፈው ስብሰባችሁ ከ15 ቢሌን  በላይ ገንዘብ አለን እንዳላችሁም  ፣እርዳታ ድርጅት እህል ፣ የመንግስት የመጠባባበቂያ እል ወጭ ተደርጎ ሰው በቤቱ ተዘግቶ ቆሎና ንፍሮው ይብላ ፣ውሀ በሚመለከተም የመንግስትም ፣የግለሰዎችም ቦቴዎች በፍላጎታቸው ወይ በግዳጅ በየቤቱ ይቅረብለት ። የሚል አስተያየት አለኝ ።
ሌላስ በወረርሽኝ የተለከፉ ተገለው የሚታከሙበት ( ማቆያ )  በመቐለ 03 ቀበሌ በሚገኜው የመለስ አካዳሚ  ግቢ አዛጋጅተናል ብለችሁ እንደትልቅ ነገር ስትናገሩ ሰምተናል ።ግን እች ቦታ ለስንት ሰው ነው እምታጠልለው ? ለምን ሁሉም የግል ሆስፒታሎች ሁሉም ደረጃ ያላቸው ሆቴሎች ፣ዩንቨርሲቲዎች ፣ የ1ኘና 2ኛ  ደረጃ  ት / ቤቶች ፣የስብሰባ አዳራሾች ፣ ትላልቅ የመንግስት ህንጻዎች ፣የእድር ድንኳኖች  በሆስፒታል  (ጊዚያዊ መጋገምያ ) መልክ ለምን አይዛጋጅም ? እኔ እንደ ሚመስለኝ  በተለብዥን መስኮት ብቅ እያላቹሁ የምትናገሩት ለፖለቲካ ትርፋማነት ነው እንጅ በተግባር ስንመለከታቹሁ ከልብ የመነጨ የስነ አእምሮ ዝግጅት የላችሁ  ኣትመስሉም  ።
  ምናልባት በህዝብ ሽብር ሊፈጠር ይችላል ብላችሁ ታስቡ ይሆናል ።በእኔ እምነት ምናልባት አምለክ ይምረን ይሆናል ።ሁላችን በየእምነታችን ጸሎት እናድርግ ። ነገር ግን  እኔ እንደ በለጸጉ አገሮች ሁሉም ገንዘብና ቁሳቁስ ፣ በቂ የሰው ሀይል  አለን ማለት እና  አእንዛጋጅ አላልኩም ።  እኔ እያልኩት ያለሁ ባለን የገንዘብ ፣የቁሳቁስ አቅም እንዛጋጅ ነው እምጠይቀው  ያለሁ ? ኣሁን እኮ ባለን ገንዘብ ፣ቁሳቁስ ፣የሰው ሃል 10 % አልተሰራም ። በመሆኑም ለከፋ አደጋ ለመከላከል እንዘጋጅ ነው እያልኩ ያለሁ  ።
ፈደራል መንግስትም ቢሆን  ለቫይረሱ  ለመከላከል 5 ቢሌን  ብር ባጀት መድቤ አለሁ ብሏል  ።5 ቢሊዮን ብር ምንድናት  ስልጣን ከያዘበት ጀምሮ  የልማት ፕሮጆክቶች  ማስፈፀምያ  የተመደበ ገንዘብ የት አውሎታል ። ለዚሁ ቫይረስ ለማጥፋት እንደመጨነቅ ፈንታ ለብልጽግና ማንነት ለማስታዋቅና በገንዘብ ለመጠናከር ነው የተጠመደው ።
የዶ /ደብረጽዮን ቡድንም ስልጣን ከያዘበት ጀምሮ የክልላችን የልማት ፕሮጆክት ማስፈጸምያ የተመደበ ባጀት ምን ተሰራበት ለሚለው መልስ የለውም ። በመቐለ ከተማ እየሰሩት ያለ  ስፋልትም መንገድም  በክልሉ ባጀት ሳይሆን  በከተማችን መዛጋጃ ቤት ገቢ ነው ።እነ ዶ/ደብረጽዮን ለዚሁ ህዝብ ለማዳን  የሚያስቡ (የሚቆረቆሩ ) ከሆኑ ከፈደራል መንግስትም የሚያስፈልጋቸው (የሚገባቸው ) ገንዘብ ፣ቁሳቁስ  ጠይቀው በማምጣት ፣በክልሉ ያለው ገንዘብ ፣ቁሳቁስ ማጥጦው  በመጠቀም ከሚጠጣ ውሀ ጀምሮ ፣መድሀኒት ፣ማስክ ፣ጓንት ፣ ምግብ  ፣ኣልኮል ወይ ሌላ ከሚካል  በዝቅተኛ ክፍያ ማዛጋጀት ነበረበት ።በየከተማው ያሉ ስራ  ኣጥ ወጣቶች  በየኣዳባባይ ተሰብስበው ለሚፈጠረው አደጋ ተጋላጭ የሆኑ ፤ብራንዳ አዳሪዎች ፣በልመና የተሳማሩ  ወገኖች በምን መንገድ እናስተናግዳቸው ብለው እንደማሰብ ፋንታ በሁሉም አካባቢ  የሚገኙ የመንግስትና የህዋሓት መዋቅር ስለ ስልጣናቸው  እንዴት  እንደሚያራዝሙ ነው   ሲጨነቁ የሚታዩ ።
 ዶ/ ደብረጽያን እና ጓዶቹ  ለዚሁ ሰው ጨራሽ  አውዳሚ ለኮረና ቫይረስ ለመከላኸል እየሰጡት ያሉ አትኩሮት ፣ባለፈው ወር ከእነ ስልጣናች አለን ለማት እጅግ ግዙፍ ባጀት በማውደም ለለካቲት 11 የህዋት ልደት በአል ለማክበር እስከ ቀበሌ ወርደው  ያደረጉት እንቅስቃሴ ሲወዳደር ለኮረና ቫይረስ ለመከላከል  የሰጡት አትኩሮት እና ለለካት11 በኣል ለማክበር  የጡት ቦታ      2 % ቦታም አልሰጡትም ። የለካቲት 11 ለማክበር እኮ የዘመናችን ካድሬዎች እነ ስብሀት ነጋ ፣ስዩም መስፍን ፣ኣባይ ጸሀዬ ፣ ጸጋይ በርሀ ኣባዲ ዞሞ እስከ ገጠር ቀበሌዎች ወርደው እንደ ተራ የቀበሌ ካድሬ  ቀስቅሰዋል ።ታድያ በዝህች ቀውጥ ጊዜ ለምን ድምጻቸው ከውሀ እንደጠለቀች አይጥ  ጠፋች ? ምናልባች የኮረና ቫይረስ አዛውንት እየመረጠ ነው የሚቀጥፍ ስለተባለ ሰግተው በፕላኔት ሆቴል  የመከላከያ ከሚካል ረጭተው ለብቻቸው እድሚ ለማስቀጠል ተደብቀው ተዘግተው ይሆን ?ስልጣንና ገንዘብ ክፉ ። ታድያ ህዝብ ከሌለ ከማን ሊኖሩ  ያስቡ ይሆናለ ?
     እስኪ ተመልከቱ ለህዝባቸው ተቆርቃሪ መሪዎች  እያደረጉት ያሉ ዝግጀት ?
                        ይቀጥላል ፣ 
                    ኣስገደ ገብረስላሴ ፤ 
                                መቐለ
Filed in: Amharic