>

የሐረር ፖሊስ በአፈና ላይ ተሰማርቷል!!! (ይልማ ኪዳኔ)

የሐረር ፖሊስ በአፈና ላይ ተሰማርቷል!!!

ይልማ ኪዳኔ
*  የሐረር ፖሊስ ኮምሽን ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆነችውን ኤልሳቤት ከበደን ከአዲስ አበባ ከተማ እንደ ማፊያ አፍኖ ወደ ሐረር ወስዶ አሰሯታል። የክልል ባለስልጣናት ጥጋብና ማናአለብኝነት የሚገርም ደረጃ ላይ ደርሷል።
……
ምን “ወንጀል” ሰርታ ነው የታሰረችው??? የሰራችው ወንጀል” ሐረር ውስጥ ያለውን የአፓርታይድ ህግ አጥብቃ መቃወሟ ብቻ ነው። ” ሀረር ውስጥ የመንግስት ስራና ሹመት ለማግኘት የኦሮሞ፣ የሐረሪ ወይም የሶማሊ ተወላጅ መሆንን ይጠይቃል። ይህን ዘረኛ ህግ ተቀብሎ በገዛ አገሩ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ መኖር የሚፈልግ ሰው የለም!” በማለቷ ብቻ ለአፈና እና ለእስር ተዳርጋለች
……
  በሃረር እና ድሬዳዋ የሚተገበረውን የአፓርታይድ ስርአት 40 40 20 እና 50 50 0 ን በመቃወም የምናውቃት ኤልሳቤጥን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይዞ ለሃረር ፖሊስ አሳልፎ ሰጥቷታል። ክሷም “የሃረር ባለስልጣናትን ሰድባለች” የሚል እንደሆነ ተነግሯል።
  ሁላችን እንደምናውቀው ልጅቷ የምትታገለው ላለፉት የህወሃት ዘመን በአካባቢው ማንኛውም የስራም ሆነ የሌላ እድል ለኦሮሞ 40% ለሱማሌ 40 % 20% ለሌሎች በሚል ብዙወጣቶችን በተወለዱበት ሃገር የበይ ተመልካች ሲያደርግ የኖረውን የአፓርታይድ ህግ እንዲቀየር እና ዜጎች ሁሉ እኩል መብት እንዲያገኙ ነው።
   1, ትሳደባለች ብዬ አላምንም፤ ተሳድባ እንኳ ቢሆን አዲስአበባ ሆና ተሳድባ ሃረር ተወስዳ የምትታሰርበት ምክንያት የለም። ግለሰብ የሚከሰሰው እና ወንጀሉ የሚጣራው ‘ወንጀሉን በፈፀመበት ቦታ ባለ ፖሊስ ነው’
 2, ጠቅላይ ሚንስትሩን ሳይቀር “ዲቃላ” እያለ የሚሳደበውን ቀና ብለህ ሳታይ ፤ አንዲትን የመብት ተሟጋች “ሰደበች” በሚል ሰበብ ከአዲስአበባ አንጠልጥለህ ወስደህ ሃረር ማሰርህ እኔ እንደሚገባኝ
   ሀ- ብልፅግናን እየሰበክህ ፤ የአፓርታይዱ ስርአት እንዲቀጥል አስበሃል።
   ሁ , አፈና በህወሃት ጊዜ ልክ አይደለም በኛ ተራ ሲሆን ልክ ነው፡ እያልክ ነው
   ሂ , ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ፤ስሟን ጅግራ ይሏታል
   ሃ , የመብት ተሟጋችን የማፈንን ውጤት ከህወሃት ባለመማርህ ነው።
  ሄ , የዜጎች እኩልነት በሌለበት የአፓርታይድ ስርአት ውስጥ በሰላም ሚንስትር ሰላም ይመጣል ብለህ በማመንህ ነው።
  ህ , እጃችንን በመታጠብ፣እርቀታችንን በመጠበቅ ኮሮናን እንከላከል፤  አፈናን በመቃወም አምቧገነንን እንታገል።
ፍትህ ለኤልሳቤት ከበደ!!! ፍትህ ለኤልሳቤት ከበደ!!! ፍትህ ለኤልሳቤት ከበደ!!!
ፍትህ ለኤልሳቤት ከበደ!!! ፍትህ ለኤልሳቤት ከበደ!!! ፍትህ ለኤልሳቤት ከበደ!!!
Filed in: Amharic