>
5:13 pm - Thursday April 18, 4312

"በሀገራችን ተጨማሪ ስምንት ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውን ተከትሎ የህሙማኑ ቁጥር 52 ደርሷል!!!" (ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር)

“በሀገራችን ተጨማሪ ስምንት ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውን ተከትሎ የህሙማኑ ቁጥር 52 ደርሷል!!!”

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
 
* በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 264 ሰዎች ውስጥ 8 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው ተረጋገጠ!!!
በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል አንዱ ኤርትራዊ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ይህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎችን ቁጥር 52 አድርሶታል።
በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጠ ስምንቱ ሰዎች መካከል አምስቱ ከዱባይ የመጡና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው። ከእነዚህም ውስጥ አንድ የዘጠኝ ወር ህጻንና ወላጅ እናቱ ይገኙበታል።
አንድ የ25 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ከታይላንድ መጥታ በለይቶ ማቆያ ክትትል ስታደርግ የነበረች ሲሆን፤ አንድ የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የውጭ አገር ጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን የንክኪ ሁኔታውም በመጣራት ላይ።
ሌላኛዋ የ30 ዓመት ሴት ኤርትራዊት ስትሆን ከእንግሊዝ ለንደን መጥታ በአዲስ አበባ በለይቶ ማቆያ ክትትል እያደረገች የምትገኝ ናት።
በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክልል ከተሞች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ አቅም እየጨመረ ሲሆን በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ይገኛሉ።
አራቱ ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ ሀገራቸው ተሸኝተዋል።
Filed in: Amharic