>
5:33 pm - Tuesday December 5, 7820

አለማችን በቫይረሱ ከ81 ሺህ በላይ  ሰዎችን አጥታለች፤ ከአንድ ሚልዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል (ታደለ ጥበቡ

አለማችን በቫይረሱ ከ81 ሺህ በላይ  ሰዎችን አጥታለች፤ ከአንድ ሚልዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል

ታደለ ጥበቡ
እግዚኦ ማህረነ ክርስቶስ!!! በ24 ሰዓት ውሰጥ ከ6,394 በላይ ሰዎች ሞተዋል።እስካሁን በአለም #በኮሮና ቫይረስ ከ81 ሺህ በላይ  ሰዎች አፈር ተመልሶባቸዋል።
ከ1,411,332 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።ያገገሙት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች ናቸው።ይኼ አሃዝ በየደቂቃው የሚጨምር ነው።
#አሜሪካ በ24 ሰዓት ተጨማሪ 1,403  ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሞተዋል አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 12,274 ደርሷል።
 #ፈረንሳይ  በ24 ሰዓት ተጨማሪ 1,417 ሰዎች በኮሮና ሞተዋል አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 10,328 ደርሷል።
#በጣሊያን ባለፉት 24 ሰዓት የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር 604 ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 17,127 ደርሷል።
#በእንግሊዝ በ24 ሰዓታት ውስጥ 786 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ሳቢያ ሞተዋል።ይህም በኢንግላንድ አጠቃላይ የሟቾቹን ቁጥር 6,159  አድርሶታል።
#ስፔን  በ24 ሰዓት ተጨማሪ 556  ሰዎች ሞተዋልአጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 13,897 ደርሷል።
#ጀርመን  በ24 ሰዓት ተጨማሪ 131  በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል።አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 1,941 ደርሷል።
#ቤልጀም  በ24 ሰዓት ተጨማሪ 403 በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል።አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 2,035 ደርሷል።
እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው።ጥንቃቄ እናድርግ‼️
Filed in: Amharic