>

የብልጽግናው ብልግና - የቤተ መንግስቱን አንበሳ በፒኮክ መተካት ፤ ቅርሶችን ማውደም!!! (አዲስ አበባ ባልደራስ)

የብልጽግናው ብልግና – የቤተ መንግስቱን አንበሳ በፒኮክ መተካት ፤ ቅርሶችን ማውደም!!!
አዲስ አበባ ባልደራስ
ቅርስ አይፍረስ፤ የድሮ ሰፈር አይበተን፤ የኢትዮጵያ ምልክቶች አይጥፉ… የሚል ጩኸት ቢያንስ “ለውጥ ከተባለው በኋላ” አንሰማም ብለን ነበር። ሆኖም የታሪክ ማጥፋቱ ሂደት አንከስ እያለ መምጣቱ አልቀረም!።
ባለፈው አንድ አመት የከተማው ምልክቶች በዝምታ ሲጠፉ እያየን ነው። ቡፌ ዳላጋርን እንዴት እንደሸራረፉት መጥቀስ ይቻላል። ሰሞኑን ደግሞ የመስቀል አደባባይን ማስፋፊያ ግንባታን መሰረት አድርጎ በተለምዶ “ሴጣን ቤትን” ሊያፈርሱ ደብዳቤ ልከውና ከመንግስት በማይጠበቅ ደረጃ እንደወንበዴ በእኩለ ሌሊት ዶዘር ልከው አጥር ካስፈረሱ በኋላ ጊዜያዊ ከንቲባው ኢንጂነር  ታከለ ኡማ ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው የሚል ቧልትና ቅርሱን እቃ ማከማቻ ብለው በማናናቅ በማህበራዊ ገፃቸው ገልፀው እንደማይፈርስ ዳርዳርታ አሳይተዋል።
.
“ሰይጣን ቤት” የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሲኒማ ነው የታሪካችን አንዱ አካል ነው። የአፍሪካም የኢትዮጵያ መዲና ምልክት ነው። ስለዚህ የሚመለከታችሁ አካላት ቅርሳችንን አታፍርሱብን። እንዳምናው ሁሉ ቅርስ አይፍርስም፤ ሀውልት ይመለስ… መፈክር ውስጥ አንግባ።
.
ቤተ መንግስት ላይ ያለው ፒኮክን እና ቤተመንግስቱም ምንም አልገባኝም። ፒኮክና ኢትዮጵያም ግኑኙነታቸው ሊገልባኝ አልቻለም።  እውነት ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ የቀድሞውን የኢትዮጵያን ነገስታት አርማ የሆነውን አንበሳን እንደማይወዱ “እርካብና መንበር” መጽሐፍ ላይ አንብበናል። ቤተመንግስቱን አንበሳ ያላቸው ትስስር ከባድና ሊጠፋ የሚችል ባይሆንም ፒኮክ በሩ ላይ ማድረግ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግኑኙነት ቢነገረን ወይም ከጠቅላይ ምኒስትሩ ጋር ያለውን ዝምድና ብናውቀው? ቤተ መንግስቱ ውስጥ ሌሎች ነገስታትም ነገ ስለሚገቡበት የፒኮኩንና የቤተመንግስቱን ግኑኙነት ነግረው ቢያሳምኑን ተረኛው እንዳያፈርሰው ይረዳል።
 
ፒኮክና  ቤተመንግስታችንምን አገናኛቸው?!?
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ፒኮክ ከተባለች የባእዳን ወፍ ጋር በፍቅር ወድቀዋል!ኧረ ከዛም አልፈው በታላቁ ቤተ መንግስት መግቢያ በር ላይ ሃውልት አሰርተውላታል። ለምን?ፒኮክ ማናት?
 
በኢትዮጵያ ከ25 ያላነሱ በየትኛውም ዓለም የማይገኙ ብርቅዬ አእዋፋት ይገኛሉ። አንዳቸውም ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን ልብ ማሸነፍ አልቻሉም። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ፒኮክ ከተባለች የባእዳን ወፍ ጋር በፍቅር ወድቀዋል!ኧረ ከዛም አልፈው በታላቁ ቤተ መንግስት መግቢያ በር ላይ ሃውልት አሰርተውላታል። ለምን?ፒኮክ ማናት?
ፒኮክ እንደ ህንድ ባሉ የዔዢያ ሃገሮች የምትገኝ እጅግ የተዋበች ወፍ ናት።ሴቷ ፒኮክ ከወንዱ ጋር መዳራት ስትፈልግ በአረንጓዴ ቡንኝና ሲልቨር ቀለሞች ያሸበረቀውን ክንፏን ትዘረጋለች። ወንዱም ከች ይላል። ይናጫሉ።ፒኮክ በአመጋገቧ  ስጋም እጽዋትም አትምርም። ከስጋ ትላትል ሶስትአጽቂ እንሽላሊት ትንሽ እባብ ወፍ  ማንቁርቷ የቻለውን ሁሉ ትመገባለች።ከክርስትና እምነት በፊት ጥንታዊ ባቢሎናዊያንና ፐርሺያዊያን(ያሁኖቹ ኢራቅና ኢራን)“ ፒኮክ ከሞተች በኋላ ስጋዋ አይበሰብስም” ብለው ያምኑ ነበር። እናም ወፏን “የዘላለማዊነት” አርማ ያደርጓት ነበር።  ክርስትና ከተጀመረ በኋላም ጥንታዊው ክርስትና በተለይም ምስራቁ ክፍል ሃሳቡን ከክርስትና አስተምሮ ጋር በማቀላቀል የክርስትና አካል አድርገዉታል። በብዙ ጥንታዊ የክርስትና ድርሳናት ላይም በስዕል በቅርጻ ቅርጽናበጹሁፍ ተሰንዶ ይገኛል። ለብዙዎቹ ክርስቲያኖች የፒኮክ ላባዎች ላይ የሚታዩት አይኖች ሁሉን የሚመለከተውን እግዚአብሄርን ይወክላሉ። ላንዳንዶች ግን ችርችን ይወክላሉ። ክርስትናን መሰረት ያደረጉ የአርት ስራዎች ሲሰሩ ፒኮክን ከህይወት ዛፍ ቀጥሎ እናገኛታለን። በመጽሃፍ ቅዱስ ፒኮክ ዘላለማዊ ህይወትን እና ሞቶ መነሳትን ወይም ትንሳዔን ትወክላለች። አማኞ ቹ ምክንያታቸውን ሲያስረዱን በየአመቱ ያረጀውን ላባቸውን እያስወገደች ሌላ  አዲስ ላባ መቀየር በመቻሏ ነው ይሉናል። በክርስትና ሃይማኖት አስተምህሮ የአበባ ማስቀመጫ በሚመስል ገንዳ ዉሃ የምትጠጣ ፒኮክ ምስል ፤ አንድ የክርስትና አማኝ ከዘላላማዊ ህይዎት ዉሃ እንደሚጠጣ ተደርጎ ይተረጎማል። ተጨማሪ ተሪካዊ ምስሎችን ኮመንት ላይ ተመለከቱ።
Filed in: Amharic