>

ለምን_ ለምን ኢትዮጵያን??? (ዳንኤል ቶማስ)

ለምን –  ለምን ኢትዮጵያን???

ዳንኤል ቶማስ
 * በኢትዮጵያ ምድር ላይ ምን የታቀደ ስውር አጀንዳ ቢኖር ነው? የገንዘቡ የቁሳቁሱ እርዳታ  ሁሉ ለኢትዮጵያና በኢትዮጵያ በኩል እንዲሆን የተፈለገው??? ወገኔ_ንቃ !?!
 
የዓለም መንግስታት እና የዓለማችን ቢሊየነሮች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ ተቁዋማት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንደ ቅጠል እየረገፈ ያለው የሌላው አገር ህዝብና የራሳቸው አገር ህዝብ ምንም ያሳሰባችው አይመስልም:: ያሳሰባቸው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እምብዛም ጉዳት እየደረሰበት ያልሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነው! ለምን ኢትዮጵያ ብቻ ታሳዝናቸዋለች?
~ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ እስካሁን ድረስ የደረሰባት ጉዳት አነስተኛ ነው:: ከኤርትራ ቀጥሎ ኢትዮጵያ ናት አነስተኛ ቁጥር የያዘችው::ባሁኑ ሰዓት በቫረሱ የተያዙት ዜጎች ቁጥር 83 ሲሆን የሞቱ ዜጎች 3 ናቸው:: የዓለም አገራት እርዳታ የሚጎርፈው ግን ለኢትዮጵያ ብቻ ነው! ገና የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ሳይገባ የአሊባባ ግሩፕ ባለቤት ጃክ ማ 5 ሚሊዮን የመከላከያ ቁሳቁስ ብሎ ለኢትዮጵያ ላከ:: ዛሬ ደግሞ ቢልጌትስ ቫይረሱን እንደማንከላከለው እያወቀ ቫይረሱን ለመከላከል ይሁናችሁ ብሎ 200 ሚሊዮን ብር ለታከለ ኡማ ለገሰ::
~ቀደም ሲል ቻይና መድሃኒቱን የምሰጠው ለኢትዮጵያ ብቻ ነው አለች:: ዛሬ ደግሞ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አገሮች ለቫይርሱ መከላከያ በሙል ለኢትዮጵያ ብቻ 15 ሜትሪክ ቶን ቁሳቁስ ለገሱ::
ቻይና አገሩዋ ውስጥ የሚገኙ አፍሪካውያንን በተለይም ኢትዮጵያውያንን ከቤት ንብረታቸው ከስራ ገበታቸው እያፈናቀለች እያባረረች ነው:: ወደ አገራቸው መመለሻ ገንዘብ ያጡትን ኢትዮጵያውያን ሳይቀር የጎዳና ተዳዳሪ አድርጋቸዋለች:: ጥቁሮች ከቻይናውያን ጋር እንዳይገናኙ አድርጋለች:: ቻይና በአሁኑ ወቅት አገሩዋ ውስጥ ይኖሩ በነበሩ ጥቁሮች ላይ ከፍተኛ ግፍ እየፈጸመች ትገኛለች:: ነገር ግን መድህኒቴን ለኢትዮጵያ ብቻ ነው የምሰጠው ብላለች:: በሌሎች አገራት በ24 ሰዓት ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ ዜጎች እየሞቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የእነሱን ያህል ሞት ባልተመዘገበት ሁኔታ ለኢትዮጵያ ብቻ ብላለች:: ለምን ኢትዮጵያ ብቻ???
~ሳውዲ አረቢያ እና የዓረብ ኢምሬትስ አገሮች ኢትዮጵያውያንን ከአገራቸው እያስወጡ እያባረሩ ነው:: በየእለቱም በርካታ በስደት የቆዩ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተጠርዘው እየመጡ ነው:: ነገር ግን የዓረብ ኢምሬትስ አገሮች 15 ሜትሪክ ቶን ቁሳቁስ አልባሳት ግላቭ የአፍ መሸፈኛ ጨርቅ ወዘተ… ለኢትዮጵያ ብቻ ልካለች! የላከችው 30 ሜትሪክ ቶን ቁሳቁስ ነው:: ከ30 ሜትሪክ ቶኑ ውስጥ 15 ሜትሪክ ቶኑ ለኢትዮጵያ ብቻ ሲሆን ቀሪው 15 ሜትሪክ ቶን ደግሞ ለተቀሩት የአፍሪካ አገሮች የሚከፋፈል ነው:: ለዚያ ሁሉ የአፍሪካ አገር 15 ሜትሪክ ቶን! ለአንዲት አገር ለኢትዮጵያ ብቻ ግን የመላውን የአፍሪካ አገር ድርሻ 15 ሜትርክ ቶን ለብቻዋ እንድትወስድ ተደርጎዋል:: ለምን ኢትዮጵያ??
~የዓለማችን ቢሊየነር የአሊባባ ግሩፕ ባለቤት ጃክ ማ ገና ቫይረሱ ኢትዮጵያ ሳይገባ 5 ሚሊዮን ቁሳቁስ ወደ አዲስ አበባ ላከ::በዚያ ሰዓት ቻይና ብቻዋን ከዚህ በሽታ ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ነበረች:: በሺ የሚቆጠሩ ዜጎቹዋ እየሞቱ ነበር:: ጃክ ማ ግን ለገዛ አገሩ ለቻይና መንግስትና ህዝብ ምንም አይነት ቁሳቁስ ሳያበረክት ወደ ኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን ቁሳቁስ በነጻ ላከ:: ቀሪውንም ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች አዳርስ የተባለው አብይ ለመላው አፍሪካ አገር ድርሻ ድርሻቸውን ላከ::ጀግናው ኢሳያስ አፍወርቂ ብቻ ድርሻህን ውሰድ ተብሎ
የተላከለት ቁሳቁስ አልቀበልም ብሎ ቁሳቁሱን ጭኖ የሄደውን አውሮፕላን ከአስመራ አየር መንገድ አባርሮ አስመለሰ! እምቢ በማለት ብቸኛዋ አገር ኤርትራ ብቸኛውና የመጀመሪያው ምናልባትም የመጨረሻው የዘመናችን ጀግና መሪ ኢሳያስ ሆነ! ለምን?ከተባለ የኤርትራ የደህንነት መረብ ጠንካራ ስለሆነ ሴራው ገብቶት?አላውቅም ብቻ!ግን እምቢ ብሎ መለሰ! ሌላው የአፍርካ አገር የቫይረስ ድርሻውን ወሰደ! ወስዶም ለህዝቡ አከፋፈለ! የዓለማችን ቢሊየነር የሆነው
ቻይናዊው ጃክ ማ የቻይና እና የሌላው አገር ህዝብ በኮሮና ምክንያት እንዲያ ሲናጡ እያየ እነሱን ከመጤፍ ሳይቆጥርና የእርዳታ እጁንም ሳይዘረጋ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ቁሳቁሱን ወደ አዲስ አበባ ኤርፓርት በግዙፍ ካርጎ ጭኖ ላከ!በዚያ ሰዓት ኢትዮጵያ በኮሮና ምክንያት ምንም የሆነችው ነገር አልነበረም! ለምን ኢትዮጵያ???
~ዛሬ ደግሞ ቢልጌትስ ለታከለ ኡማ 200 ሚሊዮን ብር ለገሰ::የዓለማችን ቢሊየነር የሆነው አሜሪካዊው ቢልጌትስ በኮሮና ቫይረስ ስርጭትም ሞትም የመሪነቱን ስፍራ የያዘችው አገሩ አሜሪካ ናት:: አሜሪካውያን እያለቁ ነው::ስራ ፈትተው በየቤታችው ተቀምጠዋል:: ቢልጌትስ ግን እስካሁን ከኮሮና ጋር በተያያዘ ለገዛ አገሩ ለአሜሪካ ህዝብ ምንም አይነት እርዳታ አላደረገም:: የራሱ ዜጎች ሳያሳዝኑት ኢትዮጵያ አሳዘነችው::ትዝ አለችው::እና 200 ሚሊዮን ብርለገሰ::ለምን ኢትዮጵያ???
~ሌሎች ተዘርዝረው የማያልቁ የገንዘብና የቫይረስ ነክ ቁሳቁሶች በልገሳ እየጎረፉ ያሉት ለሌላው የአፍሪካ አገር አይደለም::ለኢትዮጵያ ብቻ እንጂ ለጣሊያን ወይም ለስፔን አይደለም::ለምን ኢትዮጵያ ብቻ ??? ብሎ መጠየቅ የማይችል ቢጠየቅ መልስ መስጠት የማይችል!መልሱ ቢነገረው የማይሰማ የማያምን ህዝብ ነው የገጠመን ጉዋዶች!
Filed in: Amharic