>

እስክንድር ነጋን በአስቸኳይ አዋጁ ኮማንድ ፖስት የእስር ትእዛዝ ወጥቶበት ፖሊስ አሰሮታል!!! (ስንታየሁ ቸኮል)

እስክንድር ነጋን በአስቸኳይ አዋጁ ኮማንድ ፖስት የእስር ትእዛዝ ወጥቶበት ፖሊስ አሰሮታል!!!

  ስንታየሁ ቸኮል
የባልደራስ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ የታሰረበት ምክንያት ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 05 የድሆችን ቤት ፈረሳን አስመልክቶ “ለምን ተገኘህ ለምን ድምጻቸውን ለህዝብ ታደርሳለህ..  ” እንደተባለ ገልጾልኛል!
አሁን በስልክ በደረሰኝ መረጃ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋ በስልክ ያናገርኩት ሲሆን ዛሬ ሚያዚያ 17/2012 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ከቤቱ ወደ እንደወጣ በአስቸኳይ አዋጁ ኮማንድ ፖስት የእስር ትህዛዝ ወጥቶ በኮልፌ ወረዳ 25 ፖሊስ መምሪያ በጊዚያዊነት እንደታሰረ ነግሮኛል።
86 ንፁሃንን ያሳረዱትን የራሳቸውን ሰዎች ሕዝብን ሰብስበው “አብረናቸው እንሰራለን” ያሉ ሰዎች፣ ቤታቸው ላያቸው ላይ ለፈረሰባቸው ምስኪኖች ጥብቅና የቆመውን እስክንድን ነጋ አስረዋል። በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት አከራዮች ኪራይ እንዳያስከፍሉ የሰበኩ ሰዎች፣  በዚሁ ወረርሽኝ ወቅት የዜጎች ቤት ሲፈርስ ለንፁሃን ጠበቃ የሆነን ሰው አስረዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ እውነት ከዚህ ደረጃ ደርሷል። መሸለም የነበረበት እስክንድር እየታሰረ፣ መታሰር የነበረበት ሰው በገዥዎቹ  ጥበቃ ሲደረግለት ከርሟል። መንግስት ማለት እንዲህ ኃላፊነት የጎደለው፣ ስርዓትና ሕግ የማያውቅ ሆኗል። መንግስትነት የሕዝብ ጠበቃን እያሳደደና እያሰረ፣ እውነተኞችን እያጎረ የቀደሙትን አፋኞች ተግባር ማስቀጠል ሆኗል።
የባልደራስ ፕሬዝደንት አቶ እስክንድር ነጋ በፖሊስ የታሰረበት ምክንያት ኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 05 የድሆችን ቤት ፈረሳን አስመልክቶ ለምን ተገኘህ ለምን ድምጻቸውን ለህዝብ ታደርሳለህ እንደተባለ ገልጾልኛል።
እስንክንድ ነጋ በአሁኑ ሰዓት በእስር እንደሚቆይ ተነግሮት የእጅ ስልኩን እንደቀሙት እና ወደ ማሰሪያ ክፍል እየገባ መሆኑን ገልጿል።
Filed in: Amharic