>

ለበረከት ስምዖን እና መሰሎቹ የሚመጥነውን ፍርድ ታሪክ-ጠቅሸ ልንገራችሁ! (መስቀሉ አየለ)

ለበረከት ስምዖን እና መሰሎቹ የሚመጥነውን ፍርድ ታሪክ-ጠቅሸ ልንገራችሁ!

(መስቀሉ አየለ)
ዛሬ ባህርዳር ላይ በዋለው ችሎት በጫካ ስሙ በረከት ስምዖን (ጌታቸው መብራህቱ) በተባለው አረመኔ ላይ የጥፋተኝነት ብይን እንሰተሰጠበት ተነግሯል። “የፍርድ ውሳኔው” ይቀራል። ችግሩ ግን ወዲህ ነው፤ የክሱ መልክ ከሙስና ጋር ብቻ የተያያዘ መሆኑ ነው። ለብዙ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በረከት የዘረፈው ንብረት ሁሉ ሁለተኛ ደረጃ መታየት የነበረበት ክስ ነበር። ለምን ቢባል እርሱ የስንቱን ህይወት የቀጠፈ በላየ ሰብእ የመሆኑ ነገር ሲሆን እንዳለመታደል ሆኖ ግን የዛሬው ብአዴን ደግሞ በረከት ስምዖንን በዘር ማጥፋትና መሰል ወንጀሎች ለመክሰስ የሚያስችል ቁመና የሌለው ጭንጋፍ መሆኑ ነው። ስለምን ቢባል በረከት አዛዥ እንጅ ታዛዥ ባለመሆኑ እርሱ ከላይ “መልኩ አስጠላኝ” ያለውን ሁሉ ሲረሽኑ፣ ሲሰቅሉና ሲገርፉ የነበሩት እዚሁ ብአዴን ውስጥ ተሰግስገው የኖሩት የትናንት ፍርፋሪ ለቃሚዎች የዛሬ ተደማሪዎች በመሆናቸው ነው። ከዚያ በመለስ ግን በረከትና ኩባንያው ላፈሰሱት ደም በግልጽ እንዲከሰስ ብቻ ሳይሆን ትውልድ የሚዘክረውና መቀጣጫ የሆነ የፍርድ ውሳኔ እንዲያገኝ ማድረግ ከዚህ ትውልድ የሚጠበቅ እዳ ነው።
አዎ፤ ያ ቀን ስጋ ለብሶ የሚታይበት ቀን ሊመጣ ይገባዋል። በእርግጥም  ደግሞ ከጋንቤላ እስከ ጅጅጋ፤ ከአርባ ምንጭ እስከ ሰሜን ጎንደር ጫፍ ደመ ከልብ ሆነው የትም የቀሩት ንጹሃን ከላይ ከመንግስተ ሰማያት  በአጸደ ነፍስ ሆነው ያንን ቀን እንደሚጠብቁት የታመነ ቢሆንም ነገር ግን የዚህን አረመኔ የወንጀል መጠን የሚመጥነው ፍርድ “የትኛው የወንጀለኛ መቅጫ አንቀጽ ነው ?” ለሚለው ጥያቄ  መልሱ ቀላል አይደለም።
 ይሕ ከዚህ በታች የምጠቅሰው ምሳሌ ከጥቂት አመታት በፊት በእዚሁ ድረገጽ ላይ ተጠቅሜበት የነበረ ቢሆንም ቅሉ ወደ ፊት በረከት ስምዖንን ጨምሮ በደደቢታዉያን ላይ የሚሰየም የወንጀል ችሎት ሁሉ እንደጥሩ ግብዓት ቢወስደው ማለፊያ ይሆናል …. ህጉ የተጻፈው በ1949 በመሆኑ ህጉ ሲቀረጽ እንዲህ አይነት ስማይጠሩ አረመኔዎችን የጭካኔ ጥግ የሚያውቅ ስነ ልቦና አልነበረንም። ስለዚህ ዘመኑን የሚዋጅ አዲስ እስታንዳርድ ሴት ማድረግ( setting the standard)  ይጠበቅብናል። ለምን ቢባል ነገ ደግሞ እንደ ሳሞራ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ጸሃየ፣ አዜብ ጎላ፣ ዴብረጽዮን ፣አርከበ ፣አዲሱ ለገሰ ፣አባይ ወልዱ፣ ደብረጽዮን ወዘተ  አይነት ጉግማንጉግ እጃችን ውስጥ የሚገቡት ቀን መምጣቱ አይቀርም እና ነው።
ወደ ፍሬጉዳዩ ስንገባ ደርግ  እንደ ተቋም ለፍርድ ቤት   የተሻለ ክብር ነበረው ማለት ይቻላል ። ለምን ቢባል ደርግ አንድን ሰው “ጠላቴ ነው” ብሎ ካመነ ምንም አይነት ማስመሰል ሳያስፈልገው ያመነበትን ፊት ለፊት ተናግሮ ባደባባይ የፍየል ወጠጤ የሚባል ቀረርቶ እያዘፈነ “አብዮታዊ እርምጃ” ይወስድበታል እንጅ  የሌለበትን ዲሞክራት ለመምሰል ብሎ በፍርድ ቤት እያመካኘ ሰው አያንገላታም ነበር። ይኽንን የሚያደርገው ደግሞ በተወሰነም ደረጃም ቢሆን ከወያኔ በተሻለ ለፍርድ ቤቱ ክብር ስለነበረው እንደሆነ አሌ አይባልም።
በዚህም የተነሳ አንድን አብዮቱ ላይ በማሴር የተጠረጠረ ግለሰብ ጉዳይ በጋጣሚ” በፍርድ ቤት ይታይ” የሚል ውሳኔ ካገኘ ዳኞቹ ያመኑበትን በነጻነት ይወስኑ እንደነበር ይታወቃል። በመሆኑም ለዛሬው ጉዳይ መነሻ ይሆነኝ በወቅቱ በናዝሬት ውስጥ በፍርድ ቤት ጉዳዩ ኢንዲታይለት ተላልፎ ስለተሰጠ የቀይ ሽብር ዘመን ሹመኛን ጉዳይ ይሆናል።
ታሪኩ እንዲህ ነው ። በቀይ ሽብር ብዙ ወጣቶችን የገደለ የደርግ ካድሬ ነበር አሉ፤ አቢዮቱን ከሚገባው በላይ በመለጠጥ “ያይኑ ቀለም ያስጠላውን” ሁሉ የሚገድልና ለቅርብ አለቆቹ ሳይቀር አስፈሪ ምጽአት እስከ መሆን የደረሰ ነፍሰ በላ። ውሎ አድሮ ግን ቀይ ሽብርም እረግቦና ድርግም ቀስ እያለ ሲረጋጋ ህዝብ ጋር መታረቅ የፈለገበት ወቅት ላይ ይደርሳል፤ በዚህ መሃል ይኽ ሰው ከጓደኞቹ ጋር ሆቴል በር ላይ ቆሞ በቀን ጎደሎ ለአንድ መናጢ ደሃ ጫማ ጠራጊ ጫማውን እንዲጠርግለት ያዘዋል። ሊስትሮውም ጫማውን ሲጠርግ እንደ መቸኮል አድርጎት ኖሮ የዚህን ሰው ካልስ ትንሽ ቀለም ቢያስነካበት ይኽ ቀይ ሽብር በመብረዱ የሰው ደም ሃራራ መንፈሱን ያሻቀለው ልቡሳነ ስጋ ሆዬ ምክንያት አገኘሁ ብሎ ይኽንን ምስኪን ጫማ ጠራጊ እንዳጎነበሰ ጭንቅላቱን በሽጉጥ አፈረሰው። በዚህም ሽብር እንዳዲስ ከተማውን ሲወረው ግዜ በሁኔታው ውስጣቸው ያረረው አለቆቹ ጉዳዩን ለዋናው መምሪያ ያቀርቡና አንድ ውስኔ ያስወስናሉ።
ውስኔውም ” ከስራ ባስቸኩዋይ ታግዶ ወደ ህግ ቦታ ይቅረብና ፍርድ ቤቱ እንደፈለገ ያድርገው” የምትል ነበረች። ዋናው ነጥብ ጉዳዩን ፍርድ ቤቱ ያመነበትን እንደሚወስን ግልጥ ነበር።
ዜናው የከተማው ከፍተኛ የመወያያ ርዕስ ነበርና ችሎቱን በጣም በርካታ ሰው ይከታተለው ጀመር፤ ነገሩን ከመጀመሪያው ጀምረው የያዙት ዳኞችም ጭብጡን ሲመረምሩ ከርመው በርካታ ወራት ከፈጀ ግልጽ ችሎት ቦሃላ አንድ ታሪካዊ የሚባል ውሳኔ አሳለፉ ። ይኽ ውሳኔ አገሪቱ እንደ አገር ደረጃውን በጠበቀው በአስራ ዘጠኝ አርባ ዘጠኙ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ መተዳደር ከጀመረችበት ግዜ ጀምሮ ያልታየና ያልተለመደ አዲስ አይነት ምልከታ የያዘ ውስኔ ነበር ማለት ይቻላል። የዚህን ሰው በላ መጨረሻ ለመታዘብ በጥፍሩ ቆሞ ውሳኔውን ሲጠብቅ የከረመው ህዝብ በታደመበት ችሎት ውሳኔው እንዲህ ተነገረ።
…. ጉዳዩን በቂ ግዜ ወስደንበታል። የሟችንም ሆነ የገዳይንም የኋላ ታሪክ መርምረናል። ገዳይ መንግስት የሰጠውን ስልጣን ያለአግባብ ተጠቅሞ የአንድን ለፍቶ አዳሪ ህይወት የቀጠፈበትን ምክንያትም ሆነ ይህንን ወንጀል እንዲፈጽም ያስቻለውን ሰብአዊ ቁመና ከየት አገኘው፣ እንዲሁም ይሕ የግፍ ጥግ ህዝባችን የቆመበትን የሞራል እና የታሪክ ልእልና የማናጋት አቅሙ ምን ያህል ነው፣
ወንጀለኛውን እንደ ወንጀለኛ ከመቅጣት ባሻገር ሕጉ የዚሕዝባችንን የሰባዊነት እሴት ከማስጠበቅ አኳያ የት ድረስ መሄድ አለበት፣ የህግ አውጭው አካል ወይንም የፍትሃ ነገስት ኮሚሲዮን ይህን የወንጀለኛ ህግ ከመደንገጉ በፊት ተዛማጅ ከሆኑ የወንጀለኛ መቅጫው አንቀጾች ጀርባ ያሉት መነሻ ምክኛቶች ወይንም መድረሻ አላማዎች ምን-ምን ናቸው …የሚሉትን ዝርዝር አመክንዮ በተጨባጭ መርምረን የሚከተለው ውሳኔ ላይ ደርሰናል።
እንደሚታወቀው የወንጀለኛ መቅጫው አላማ በቀል ሳይሆን አንድን ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ግለሰብ አርሞና አስተካክሎ የተሻለ ዘጋ ማድረግ ቢሆንም የዚህ ተከሳሽ ማንነት ሲታይ ግን በዚህ መንገድ ተሂዶ የሚደረስበት የስኬት ጫፍ አይኖርም የሚል ነው። የህጉ ተቀዳሚ ግብ  የዜጎቹን ኢንተረስት ማስጠብቅ ቢሆንም እንዲህ አይነቱን ታርሞ ወደ ሰውነት ደረጃ ሊያድግ የማይችልን ከሰባዊነት የጎደለ ፍጡር አስሮ በመቀለብ የአገርን ሃብት ማባከንም አስፈላጊ ነው ብለን አናምንም። እንዲሁም ደግሞ ተከሳሹ ከተከሰሰባቸው በርካታ አንቀጾች አንዱ የሞት ፍርድ እንዲፈጸምበት የሚጠይቅ ቢሆንም ይህንን ህግ ተፈጻሚ ለማድረግ ደግሞ መጀመሪያ ተከሳሹ ሰብአዊነት ሊኖረው ይገባል ። በመሆኑም ይህ ችሎት ዙሪያ ገባውን በማየት ከዛሬ ጀምሮ የተከሳሽን ሰው የመሆን መብት በዚህ ችሎት ፊት ኢንዲገፈፍ በአንድ ድምጽ ወስነናል። ይኽ ማለት ተከሳሹ ከዛሬ ጀምሮ አንድ ሰው የሚኖረው መብትም ይሁን ግዴታ የለውም ማለት ነው …ሲሉ ውሳኔውን ከነዝርዝር አንድምታው ለታዳሚው አሳወቁ እና ፈትተው ለቀቁት።
በሌላ አነጋገር ማንም ሰው ያለምንም በቂ ምክንያት እንዲሁ ከሜዳ ተነስቶ ቢገድለው ወይንም የሆነ ጉዳት ቢያደርስበት ሰው በመግደል ወንጀል ሊጠየቅ አይችልም ማለት ነው።
ይሕንን የሰማ ህዝብ ታዲያ ከዛን ቀን ጀምሮ እንደ ዱር አውሬ ከያቅጣጫው ተጠራርቶ እንደ ሙሴ ዘመን ፍርደኛ በያገኘበት  በዲንጋይ ሲወግረው፤ መንገድ ላይ ባገኙት ቁጥር እልሃቸውን ሲወጡበት፤ ከአካሉ የሆነ ነገር ሲጎድል፣በመጨረሻም እንዳበደ ውሻ በየሄደበት ልጋጉን ሲዘራ ከርሞ ትንሽ በትንሽ ከሰውነቱ እየጎደለ ሄዶ  በመጨረሻም አለቀ ማለቱ ይሻላል።
ሲጠቃለል በጎሳ ተስቦ በተመረዘ ዘረኛ የታክስ ሸፍጥ ወገቡ  ሲጎብጥ የኖረን ህዝብ እንደገና የወያኔን ቱጃሮች አስሮ ኢንዲቀልብ ግዴታ ሊኖርበት አይገባም። እነርሱም ባገርና በወገን ህልውና እንዲሁም በታሪክ እና በመጭው ትውልድ እጣ ፋንታ ላይ ጭምር ዘርተው ያለፉትን የመርዝ ሰንኮፋ ነቅሎ ለመጨረስ ከእለተ ምጻት በመለስ የሚተርፍ ቀን አይኖርም።
ስለዚህ ዛሬ በረከት ስምዖን ላይ የሚወሰነው ውሳኔ አንድ ስታዳርድ አስምሮ ቢያልፍ ነገ እነ ደብረጽዮን ላይ ተፈጻሚ ለማድረግ መንገድ ይከፍታል። ባጭሩ የባህር ዳሩ ችሎት ይህን አረመኔ ሰው የመሆን መብቱን ገፎ አሳልፎ ቢሰጠን እና ማለፊያ ታሪክ ቢሰራ መጭው ትውልድ ሲዘክረው ይኖራል ለማለት ነው ።
Filed in: Amharic