>

ከኢትዮጵያ እና ከሕዝቧ እንደተጣሉ ያለፉት መለስ ዜናዊ እውነተኛ ማንነታቸው?!? (ውብሸት ታዬ)

ከኢትዮጵያ እና ከሕዝቧ እንደተጣሉ ያለፉት መለስ ዜናዊ እውነተኛ ማንነታቸው?!?

ውብሸት ታዬ
   ዛሬ የአቶ መለስ የልደት ቀናቸው ነው አሉ። የእሳቸውን የትውልድ ቀን፤ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ቋት በማራገፍና የሕዝብን ልጆች በመከራ ዕሳት ለ27 ዓመታት በመለብለብ የሚታወቁት ደጋፊዎቻቸውና ጀሌዎቻቸው በማሞካሸት እያከበሩት ይገኛሉ።
  ሰውየው የአገር ሉዓላዊነትንና የሕዝብን ክብር አስነዋሪ በሆኑ ቃላት የሚገልጹ(ሰንደቅ ዓላማን ጨርቅ፣ ወደብን የግመል ውሃ ማጠጫ የሚሉ)፤ በዚህም አሰብን ከከሐዲው ድርጅታቸው ጋር አብረው በግድ ለኤርትራ ካልሰጠን ብለው ያስፈጸሙ፣ የተማረን የሚጠሉ(የተማረ ሳይሆን ለፓርቲያችን ታማኝ ብቻ እንሾማለን) በማለትና ትውልድ ገዳይ የትምህርት ፖሊሲ በመቅረጽ በ(ጉዲት) በኩል አስፈጽመው የዕውቀት መዋቅሩን አፈር ያለበሱ፣ ምሁራንን በገፍ ያሳደዱ(42ቱ የዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሌሎች)…
   ምንም ኢትዮጵያዊ ግብረገብ አልነበራቸውምና እንደአንድ የአገር መሪ ሳይሆን እንደተራ ኪስ አውላቂ በፓርላማ ቀርበው ‘ሌብነት እስካልተያዙ ሙያ ነው’ ብለው ሌብነትን ያነገሱ፤ በዚህም የድርጅታቸው አባላት በ27ቱ ዓመታት ቆይታ ስልጣንን ሽፋን አድርገው 30 ቢሊዮን ዶላር(በጥቂቱ የአገራችን የሦስት ዓመት በጀት ያህል) ከአገር ስለማሸሻቸው የዓለም ባንክ ሪፖርት ያደረገበት(አሁን ለማስመለስ እየተሠራበት ያለ) የሌቦች አለቃ የነበሩ…
   ‘በስልጣናችን የመጣን ጣት እንቆርጣለን’ በማለት በገሃድ ፈክረው ብዙዎችን አካለጎዶሎ ያስደረጉ፣ በየእስር ቤቱ አሳፍነው ያስገደሉ፣ እንደዕውቁ ድምጻዊና የሕዝብ ልጅ ኤቢሳ አዱኛ ዓይነቶቹን ትንታጎች ደግሞ በጥይት አስደብድበው ሕይወታቸው ሳያልፍ በመኪና ያስጎተቱ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያከበረውና የወደደውን ሁሉ እንደጠሉና እንደታገሉ ኖረው ያለፉ በኢትዮጵያ ላይ የመጡባት ሰው ናቸው።
   በቅኝ ግዛት ዕሳቤ፤ በዜጎች መካከል ጥላቻ፣ ጥርጣሬና ያለመተማመን መንፈስ ያሰፈኑ ናቸው። እሳቸውና የድርጅታቸው አባላት አገር ለማምከን ተማምለው የዘሩት ዘር ጦስ እስካሁን አልለቀቀንም። እናውቀዋለን፤ ለወደፊቱም አንረሳውም !
Awwaala Wayyaanee irratt Nagaaf Tokkummaa biyya keenyaa haa ijaaruu !
ፍቅር፣ አንድነትና ሰላም ለኢትዮጵያ !
Filed in: Amharic