>
5:13 pm - Tuesday April 19, 6991

ወጀብ ሲመጣ መወላገድ ፤ ጎጥ ውስጥ መደበቅ፤ ውልብኝ ብሔርተኝነት ! (ወንድወሰን በየነ)

ወጀብ ሲመጣ መወላገድ ፤ ጎጥ ውስጥ መደበቅ፤ ውልብኝ ብሔርተኝነት !

ወንድወሰን በየነ
“All birds find a shelter during a rain but eagle avoids rain by flying above the clouds”.
 
“በዝናብ ወቅት አዕዋፎች ወደ መጠለያ ጎጇቸው ሲዘሙ ንስር ግን ራሱን ከዝናብ የሚከላከለው ከደመና በላይ ከፍ ብሎ በመብረር ነው ።” 
አዕዋፎች ሁሉ እንደ ንስር ክንፍ አላቸው ። ነገር ግን ችግራቸውን የሚፈቱበት መንገድ እንደ ንስር ከፍታን በመምረጥ ሳይሆን ትንሽዬ ክልል መሠል ጎጆ ውስጥ ራሳቸውን በመደበቅ ነው ። ይህቺ ትንሽየ ጎጆ ሌላ ወጀብ ሲመጣባት ጭራሹን ትጠፋለች ። አውሎ ንፋስ ሲመጣ ድራሿ ይጠፋል ። ንስር ግን በአደጋ ጊዜ ከራሱ በላይ የማታላውስ ጎጆ ውስጥ አይቀረቀርም ። ከአደጋው በላይ በከፍታ ሁሉን ይቃኛል ። ከሌሎቹ ወፍነን ባዮች ራሱን አልቆ ችግርንና መፍትሔውን ያያል ።
በአማራ ብሔርተኝነት ውስጥ ጎጤ ተነካ እያሉ ሲበጠረቁ የሚውሉት ችግሩንና መፍትሔውን ማየት የማይችሉ የአህያ ዓይነት ፀባይ ያላቸው እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚጫወቱ የብአዴን መጠቀሚያ የሆኑ ማንም እንዳሻው አሽቶ የሚቅማቸው ብአዴናዊ ውልብኝ ብሔርተኞች ናቸው ። አንድ ችግር ሲፈጠር አካባቢያችንን ክልል አድርገን እዛች ውስጥ እንደበቃል እያሉ ወፍነን ይላሉ ።
እነኝህ ውልብኝ ዲሞክራሲያዊ ብሔርተኞች ከጅምሩ የሚሰሩት ለብአዴን ነበር ። በመጀመሪያ ታችኛው አመራር ደህና ነው አሉ ። ቆየት ብለው ላይኛው አመራር ደግ ነው አሉ ። ዋል አደር ሲሉ ብአዴን እንደ ንስር ጥፍሩን ቆርጧል ተደመሩ አሉ ። አሁን ላይ የአማራ ሕዝብ ብአዴን የአማራ ጠላት ነው ብሎ ባደባባይ ሲወጣ የመጨረሻ አማራጫቸው አማራን በጎጥ መከፋፈል በመሆኑ ላይ ታች መፏጠል ጀመሩ ። provincialism is the final option they have on hand to keep their master ANDM on power! አለቃቸውን ብአዴንን በስልጣን ለማቆየት ያላቸው ብቸኛ አማራጭ ጎጠኝነት ነው ።
የጥቅሙ ተካፋይ ያልሆነው ተከታያቸው የጎጥ ዜማ የሚዘምሩት አመጣጣቸው ከብአዴን እንደሆነ ማወቅ አለበት ። ብአዴን በአሁኑ ስዓት ሉሲ በሚሏት አፅም ይመሠላል ። ደግፈው የያዙት የጎጥ አክቲቪስቶቹ ብቻ ናቸው ። ድርጅቱ በጣም በመበስበሱ አንዱ ብአዴን ሌላውን ብአዴን አሸንፎ ወይም አቸንፎ ለመውጣት እስከመፎካከር ይደርሳሉ ። ለዚህ ውስጣዊ ትግላቸው ድጋፍ ለማግኘት የጎጥ አጀንዳ ያራግባሉ ። የምታዩት የጎጡ ዝማሬ ከዚህ የተለየ መሠረት የለውም ። ላይ ላዩን ሰኔ 15 በሚል ቅባት ይቀቡታል ።
የሰኔ 15 ጉዳይ የተለያየ ሐሳብ ያላቸው ወደ መድረክ በመምጣት በውይይት ግልፅ መሆን ያለበት ግልፅ ይሆናል እንጂ ጎጥ ውስጥ ለመቀርቀር ምክኒያት ሊሆን አይችልም ። በታሪካችን እነ በላይ ዘለቀ ተገለዋል ። ከ1953ቱ መፈንቅለ መንግስት ከእነ አርበኛ ራስ አበበ አረጋይ መገደል ጀምሮ እስከ 1967ቱ የእነ ዶክተር አክሊሉ ሐብተ ወልድና የ62 የአገር አድባራት መገደል አልፏል ። ወደ ኋላ መለስ ስንልም ልጅ አባቱን እስከመገልበጥ የደረሰ ታሪክ አለን ። ለዚህም የወህኒ አምባን ታሪክ መለስ ብሎ ማየት ነው ። የሰኔ 15ቱም ጉዳይ ከነኝህ የተለየ ነገር አይደለም ። ነገር ግን ብአዴን ይህን ጉዳይ ለይቶ በማጦዝ የድክመቱ መደበቂያ አድርጎታል ።
ከብአዴን አቃጣሪ አክቲቪስቶች በተጨማሪ በግርግር የተወናበደ የፌስቡክ ተከታይ አለ ። ዳኛው ብአዴን ፤ አቃቢ ሕጉ ብአዴ ፤ መትማሪ ቡድኑ ብአዴን ሆኖ ሳለ የሰኔ 15 ጉዳይ የአማራ ሕዝብ ጉዳይ የሚመሥላቸውም ብዙዎች ናቸው ። ባንድም በሌላ በልዩነቱ ተጠቃሚው ብአዴን በመሆኑ ከአሉ ቧልታ ጽሑፍ ለሕዝብ የሚደርስ ግልፅ ውይይት ሊደረግበት ይገባል ። ውይይቱ ማዶና ማዶ ሆኖ በሚራኮተው መካከል እንጂ የራስን ተቃዋሚ ፈጥሮ የሸፍጥ ውይይት አደርጋለሁ ማለት መፍትሔ አይሆንም ።
ከዚህ ውጭ ሰኔ 15 ላይ ቁሞ መቅረት ከሰኔ 15 ቡኋላ የተገደለውን አማራ አለማየት ነው ። ብአዴን ሰኔ 15 ላይ ተቸንክረህ መቆምህን ይፈልገዋል ። ምክኒያቱም በአማራ ላይ ለሚደርሱ ጥፋቶች በሙሉ ተጠያቂው ብአዴን ስለሚሆን ወቅት እየጠበቀ አጀንዳ ያስቀይራል ።
Filed in: Amharic