>
5:13 pm - Monday April 19, 8483

ግልጽ መልእክት ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ! (ሀብታሙ አያሌው)

ግልጽ መልእክት ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ !

ሀብታሙ አያሌው

ሜቴክ በመባል ይጠራ የነበረው ተቋም ይመራበት በነበረው  የተበላሸ አሰራር በዝርፊያም ሆነ በአሰራር ብልሹነት ከፍተኛ የአገር ሃብት እንደባከነ  ከብርቱ ህዝባዊ ትግል በኋላ በመንግስት ደረጃ ጭምር ታምኖ እንደተገለፀ ይታወቃል።  ያም ሆኖ ሜቴክ እንደ ተቋም ቢያንስ እርስዎም አባል ለነበሩበት ለድንዝዙ ፓርላማም ቢሆን ሪፖርት ያቀርብ እንደነበረም በሚገባ ያስታውሳሉ።   መቼም ለዓመታት በፓርላማው ተሰይመው  እጅ እያወጡ የግፋ አዋጆችንም ሆነ የሜቴክን ሪፖርት ሲያፀድቁ እንዲት ቀን በስህተት “ለምን እንዲህ ይሆናል ?” የሚል ትችት አቅርበው የህዝብ ቀልብ ሳይገዙ ኖሩ ብዬ እግረ መንገዴን ጥያቄ ብሰነዝር የሚከፉ አይመስለኝም።
ያ’ አምርረን የታገልነው የኢህአዴግ ስርዓት በተሻለ ግልፅነት፤  ተጠያቂነትና አሳታፊነት ባለው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲተካ እንደነበረ በሚገባ ያውቃሉ።  ይሁን እንጂ ያንን ሁሉ ትግልና መስዋዕትነት ተሻግረን ጥቂት እንኳን ሳናርፍ ፋታ ወደ ማይሰጥ ሌላ ትግል እንድንሻገር ለምን እንደፈረዱብን ሳስብ ከልቤ የሚሰማኝን መሪር ህዘን እና ቁጣ ሳልገልፅልዎ አላልፍም።
እርስዎ ወደ መንበረ ስልጣን የመጡባት ያቺ የተስፋ ወራት እንደ አይን ጥቅሻ ፈጥና እንድታልፍ አድርገው  በሁሉም መስክ እየገነቡ ያሉት ያልተጠበቀ ግለሰባዊ አምባገነንነት ‘አጀብ የሰው ነግር’  ከማለት አሻግሮ ጅምር ሥርዓትዎ  እንደ ባቢሎን ግንብ ሳይጠነክር ትግላችን የቤተመንግስቱን አጥር እንዲነቀንቅ መግፍዔ እንደሆነ በአንክሮ ቢያጤኑት ምርጫዬ ነውና  አንድ ዜጋ እጠይቅዎታለሁ።
በግልፅ እንደሚረዱት  የእርስዎ ድርጊት የአሁኑ ይባስ ወደሚያሰኝ ቁልቁለት ማምራት ከጀመረ በእጅጉ ሰንብቷል። ገንዘብ ብቻ ሳይሆን “ነፍሰ በላ”  ብለው የረገሙት ሜቴክ እንደ ተቋም ይሰራ የነበረውን በግለሰብ ደረጃ ተክተው  የበርካታ በቢሊዮ ብሮች ፕሮጀክት  አድራጊና ፈጣሪ ይሆናሉ ብለን ብንጠረጥር  ቀድሞውኑ የሰዶ ማሳደድ ትግል ውስጥ ባልተነከርን ነበር።
በእውነቱ እምነትን መብላት ነውር እንደሆነ በሚገባ እንደሚያውቁ ተጠራጥሬ አላውቅም። አስቤ ልደርስበት ያልቻልኩት ግን ሜቴክን አውግዘው እራስዎ ተቋሙን ተክተው ሜቴክ ሆነው የተገኙበትን ምስጢር ነው። ፀብና ትግላችን ከድርጊት ጋር እንጂ ከማንነት ጋር አልነበረምና  ምክንያታዊ ትግላችን እንደ ትላንቱ ሁሉ ሰልፉን በደጃፍዎ ማድረጉ ምላስዎ ቢቆጣም ህሊናዎ ግን ለመርሃችን  ምስክር እንደሆነ ጥርጥር የለም።
የቀድሞዎቹ ጠቅላዮች መለስ ዜናዊም ሆነ ኃይለማርያም ደሳለኝ በዘመናቸው ከፍተኛ ገንዘብ የባከነባቸው ያለቁም ሆኑ በጅምር የቀሩ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች  እንደነበሯች ይታወቃል። ቢያንስ ግን ፕሮጀክቶቹ  ለሚንስትሮች ምክርቤትም ሆነ ለድንዝዙ ፓርላማ እና ለህዝብ በሚዲያ ይፋ ይደረጉ እንደነበረ ሁላችንም እናስታውሳለን።
ጠቅላያችን እርስዎ  ያንን የቀድሞ መሪዎች አሰራር በይፋ አብጠልጥለው አሰራሩን ተችተው ብክነትና ዘረፋ ያሉትን  በመረጡት መንገድ አጋልጠው እኔ እሻላለሁ ባሉ ማግስት በእጅጉ የባሰ አሰራር አንብረው ህዝብ ግራ ለማጋባት ከአንድ አመት በላይ አለመሻገርዎ ግን አጃይብ ነው።
እውነት እውነት እልዎታለሁ ከረባት አንጠልጥለው በዙሪያዎ የከበቡዎት ወዳጅዎ ቢሆኑ ይሄንን ስህተትዎን ለማሳየት መስታዎት በሆንዎ ነበር።  ይሁን እንጂ ወዳጆቼ  ያሏቸው የስልጣን ደጅ ጠኝ ተንበርካኪዎች እርስዎ  ከስህተት እንዲታረሙ  ከማድረግ ይልቅ  ለእርምትዎ የሚጠቅም አሳብ አቅራቢዎችን በማጣጣል እና በጠላትነት በመፈረጅ የቁልቁለት ጉዞዎን እያፋጠኑልዎት ይገኛሉ።
በዙሪያዎ የከበቡዎ የፖለቲካ ድኩማኖች የማይገዳቸው በአንፃሩ አገር ወዳዶችን የሚያስጨንቅ  የእርስዎን አደገኛ አካሄድ በምክንያት የመታገላችንን ጉዳይ ለአፍታ እንኳን የማንዘናጋበት መሆኑን አውቀው በአስቸኳይ እርምት ቢያደርጉ የሚበጅዎትን እንደ አንድ ዜጋ ልጠቁምዎ።
ከዚህ ሁሉ በጀት ማን ስንት ዘረፈ ??
=======================
1) የጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ እድሳት
    – በጀት – አልተገለጸም
    – ሥራ ተቋራጭ – አልተገለጸም
    – ሥራው ተጠናቅቋል
    – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
2) የታላቁ ቤተመንግሥት (አንድነት ፓርክ) እድሳት እና ፓርክ
    – በጀት – 5 ቢሊዮን ብር
    – ሥራ ተቋራጭ – ኤሜሬቶች
    – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
3) ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት
    – በጀት – 31 ቢሊዮን ብር
    – ሥራ ተቋራጭ – ቻይና
    – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
4) የአዲስ አበባ መዘጋጃ ቤት እድሳት
    – በጀት – 2 ቢሊዮን ብር
    – ሥራ ተቋራጭ – ከዱባይ
    – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
5) የፒያሳው የአድዋ ማዕከል
    – በጀት – 156 ሚሊዮን (ዶላር)
    – ሥራ ተቋራጭ – ቻይና
    – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
6) የስብሰባ ማዕከል
   – በጀት – 10 ቢሊዮን ብር
   – ሥራ ተቋራጭ – አልታወቀም
   – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
7) የአዲስ አበባ ቤተመጻሕፍት
   – በጀት – 2 ቢሊዮን ብር
   – ሥራ ተቋራጭ – ቻይና
   – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
8) አዲስ ነገ (Addis Tomorrow )
    – በጀት – 3 ቢሊዮን ዶላር
    – ሥራ ተቋራጭ – ቻይና
    – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
9) አዲስ አፍሪካ የስብሰባ ማዕከል
    – በጀት – 2.7 ቢሊዮን ብር
    – ሥራ ተቋራጭ – አልታወቀም
    – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
10) አንድነት ፓርክ የመኪና ማቆሚያ
    – በጀት – 2.5 ቢሊዮን ብር
    – ሥራ ተቋራጭ – ቻይና
    – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
11) መገናኛ የትራነስፖርት ተርሚናል
   – በጀት – አልታወቀም
   – ሥራ ተቋራጭ – አልታወቀም
   – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
12) መሶብ ታወር
   – በጀት – 681 ሚሊዮን ዶላር
   – ሥራ ተቋራጭ – አልታወቀም
   – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
13) እንጦጦ ፓርክ
   – በጀት – 1.5 ቢሊዮን ብር
   – ሥራ ተቋራጭ – አልታወቀም
   – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
14) ከመዘጋጃ ቤት – ለገሀር – መስቀል አደባባይ መልሶ
       ማልማት
   – በጀት – 2.5 ቢሊዮን ብር
   – ሥራ ተቋራጭ – ቻይና
   – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
15) ለገሀር መንደር (ሪልስቴት)
   – በጀት – 1.9 ቢሊዮን (ዶላር)
   – ሥራ ተቋራጭ – ከዱባይ
   – የኮንትራክተርም ሆነ ሰብኮንተራክተር ጨረታ  የለም
    – በጀቱንም ዕቅዱንም ያፀደቀ ተቋም የለም
    – ህዝብ እንዲያውቀው አልተደረገም
ከላይ የተዘረዘሩት በሙሉ  ASTU ዩኒቨርሲቲ በ30,000,000.00 ዩሮ እገነባዋለሁ ያለውን የሳተላይት መገጣጠሚያ እና ሌሎች በየቦታው የተጀመሩ በርካታ የዲዛይን ግንባታ (Design Build) ፕሮጀክቶች ሳይጨምር መሆኑ ነው።)
ከፕሮጀክቶቹ ግዙፍነት፣ ከሚፈስባቸው ከፍተኛ በጀት (የተወሰነው በእርዳታ እና በብድር የተገኘ) እና ከፍተኛ ሀገራዊ አጀንዳነት አንጻር  ሲታይ እንደዚህ ያሉ ፕሮጀክቶች  ያለ ግልፅነትና ተጠያቂነት መስራት ከሜቴክ የከፋ ሜቴክ ሆኖ መገኘት ነው።
Filed in: Amharic