>

ጦርነቱ ቢነሳ ኢትዮጵያ የ5ቢሊዮን ዶላር ግድቧን ልታጣ ትችላለች ፤ ግብፅ ግን ሁለመናዋን ታጣለች!!!" (ሄርናድይ ኦላሪ - የመካከለኛ ምስራቅ ፓለቲካ ተንታኝ) 

ጦርነቱ ቢነሳ ኢትዮጵያ የ5ቢሊዮን ዶላር ግድቧን ልታጣ ትችላለች ፤ ግብፅ ግን ሁለመናዋን ታጣለች!!!”

ሄርናድይ ኦላሪ  የመካከለኛ ምስራቅ ፓለቲካ ተንታኝ 
 


በአንድ Quora በሚባል ዌብ ሳይት ላይ “ኢትዮጵያና ግብፅ ወደ ጦርነት ቢያመሩ ማን ሊያሸንፍ ይችላል?” የሚል ወሳኝ ጥያቄ ተነስቶ አንድ
Hernaday Oleary የተባለ የመካከለኛ ምስራቅ ፓለቲካ ተንታኝ የሰጠው ምላሽ ስላስደመመኝ ለካፍላችሁ ተገደድኩ!!..
እንደዚህ ይላል፦….”ከጦርነቱ ግብፅ በቀላሉ አትወጣም ኢትዮጵያን ማሸነፍ የማይታሰብ ነው፤ከሷ በጣም የተሻሉ ሀገሮች እንኳን ሞክረው አልተሳካላቸውም ፤ግብፅም ብትሆን በተደጋጋሚ ሞክራ አልተሳካላትም።
በርግጥ ግብፅ አሁን ከኢትዮጵያ የተሻላ ጦር አላት የተሻለ አየር ሀይል የተሻለ ባህር ሀይል ገንብታለች ነገር ግን ኢትዮጵያኖች በጦርነት ላይ ያላቸው ሞራልና ሀገራቸውን ከውጪ ጥቃት ለመከላከል ያላቸው ቁርጠኝነት ለማሰብ እራሱ የሚከብድ ነው፤የ 3ሺ አመት ታሪካቸውም ይህንን ነው የሚያሳየው።
ዛሬ ምን የሚያስቀይር ነገር አለ? የብሔር ክፍፍልና የፓለቲካ ልዩነት? እመነኝ ሀገራቸው ስትጠቃ ለመሰባሰብ አንድ ቀን እንኳንአይፈጅባቸውም!!…በእርግጥ ግብፅ ግድባቸውን ልታጠቃ ትችላለች ኢትዮዮጵያም ተመሳሳይ አፀፋዊ እርምጃ ትወስዳላች፤ ለዚህም እንዲሆናት በቅርቡ ከፈረንሳይ የግብፅን የአስዋን ግድብ ለመምታት የሚያስችሏትን የጦር ጄቶችን ግዥ ፈጽማለች።
አስዋን ግድብ ተመታ ማለት ካይሮን ጨምሮ ሁሉንም የግብፅ ከተሞችን አጥቦ ወስዶ ቀይ ባህር ላይ ይቀላቅላል፤የአየር ሀይሉ ማዘዣ ጣቢያዎችም በውሃ ይዋጣሉ ታንኮቹም ቢሆኑ ውሃ ውስጥ መንቀሳቀስ አይችሉም በአጭሩ የግብፅ መከላከያ ሰራዊት ሽባ ሆነ ማለት ነው።የዛኔ የኢትዮጵያ ሰራዊት ግብፅን ወሯት የፈለገውን ማድረግ ይችላል፤ያ ብቻ አይደለም ሌላ ኢትዮጵያውያኖች ምን ሊያደርጉ እንደምችሉ ታውቃለህ? ናይል/አባይ የብዙ ገባር ወንዞች ጥርቅም ነው፤ገባር ወንዞቹን በሙሉ ለመስኖ ጠልፈው በማስቀረት ናይልን ያደርቃሉ ይህ ደግሞ ለግብፅ ብቻም ሳይሆን ለሱዳንም መጥፎ እድል ነው።.
…..ስላዚህ በጦርነቱ ኢትዮጵያ የ5ቢሊዮን ዶላር ፕሮጄክት የሆነውን ግድቧን ልታጣ ትችላለች ግብፅ ግን ሁለመናዋን ታጣለች!!!”…. ብሎ ይደመድማል!!!
Filed in: Amharic