>

"በጀብሀ ምርኮኛው ደብረፅዮን  የሚመራው ወያኔ ታሪክ ሊሆን ነው!!!"  (የ"ፈንቅል " መሪ የማነ ንጉሴ)

“በጀብሀ ምርኮኛው ደብረፅዮን  የሚመራው ወያኔ ታሪክ ሊሆን ነው!!!”

 የ”ፈንቅልን ” መሪ የማነ ንጉሴ
አለባቸው ደሳለኝ 
ትግራይ በለውጥ ማዕበል ስትግል የቀድሞ የጀብሀው ምርኮኛ
 ዶ/ ደብረ ፅዮን አይኔን ግንባር ያርገው ብለውናል  ::
 እውነታው ግን 45 ዓመታት  ሙሉ የሰቆቃ ስቃይ  በወያኔ የባርነት አገዛዝ በስሙ እየነገዱ ፍዳውን ያስቆጠሩት  ጡረተኛ ፖለቲከኞች በቃችሁ ለማለት የትግራይ ህዝብ ውሳኔው በግልፅ አሳውቋል ::
ፈንቅልን” የሚመራው የለውጥ ኃይል
 የማነ ንጉሴ  እንደሚለው ከሆነ የትግራይ ሕዝብ ከለውጥ ባቡር ላይ ለመሳፈር ”  የግዜ ጉዳይ እንጂ የማይቀር ነው በማለት  በይፋ አስታውቀዋል ::
ኢትዮጵያን ባለፉት የ27 ድቅድቅ የጨለማ አመታት ዘርፈውና ቀምተው  ያለ የለለ   የሀገሪቱን አንጡራ ሐብት አሟጠው  መቀሌ ላይ
በመፈርጠጥ የተከረቸሙት ሳልባጅ  የትግራይ  ፖለቲከኛ ወያኔዎች ከአረመኒያዊ ስርአታቸው ጋር አብሮ ለመቅበር  ፈንቅል የትግራይ የወጣቶች አመፅ እንቅልፍ ነስቶ እያዝረከረካቸው ነው   ::
የጀብሀው ምርኮኛ ኤርትራዊ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል  እጅግ በጣም ተንኮለኛ መርዘኛ እባብ ፣ ቁጡና ገልፍተኛ ባህሪ እንዳላቸው ቢነገርም ተሳዳቢምና ቂመኛ ሰው በመሆናቸው የፈንቅልን የለውጥ ኃይል ለማፈንና ለማጥቃት እየተንቀሳቀሱ ነው ::
 ቂመኛው ደብረ ፅዮን   ምኞታቸውን እቅደውና  በድብቅ የሚያከናውኑ ፤ በማር የተለወሱ  መርዘኛ አስመሳይ እባብ ባህሪ ያላቸው ሰው በመሆናቸው የወጣቱን የፈንቅልን አብዮት ለማፈን የትግራይን ክልል ልዩ ኃይል  በአንደኛ ተጠቀቅ ላይ እንዲሆን ለጦር መሪዎቹ መመሪያ መስጠታቸው አጠያያቂ ሆኗል ::
የጀብሀው ምርኮኛ ደብረ ፅዮን የዃላ ታሪካቸው ሲፈተሽ:-
 አስመራ ተወልደው ያደጉ ሲሆን በአስመራ ዩኒቨርሲት የኢጂነሪንግ ተማሪም ነበሩ ::
ነገርግን ትምህርታቸውን አቋርጠው  ተ.ሓ.ኤ. (ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ) ጀብሃ ጋር በሽፍትነት ነት  ተቀላቀሉ።
ለመጀመሪያ ጊዜ  ጀብሀን ሲቀላቀሉ   በድርጅቱ ውስጥ  ሰልጥነው በአስመራ ውስጥ የጀብሃ ስዉር ፈዳያን (ፈዳያን የአረብኛ ቃል ነው ትርጉሙ ሽብርተኛ፤ ገዳይ፤ ነብስ አጥፊ ማለት ሲሆን በእንግሊዝኛው TERRORIST ማለት ነው) የተሰማሩት በዚህ የገዳይ ቡድን ውስጥ ነበረ ::
ቢሆንም ስልጠና በወሰዱበት ሞያ በአስመራ ከተማ ውስጥ  እየተሹለከለኩ  የበርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወት በነፍሰ ገዳይነት (ፈዳያን ) ሁነው ተሰማርተው የቀጠፉ ሰው ናቸው ::
በዎቅቱም የደብረ ፅዮንን መሰሪ ስራና የጀርባ   ታሪካቸውን አበጥረው የሚያውቁት አውስትራሊያ የሚገኙት የቀድሞው የወያኔ ታጋይ አቶ ገብረመድህን ምስክረነታቸው በቃልም በፅሁፍም  ገልፀውታል ::
በነገራች ላይ ጀብሀ የአረብ ሶሻሊዝምን ፍልስፍና ይከተል የነበረ ኤርትራ ውስጥ በ1961 አመተ ምህረት በስደት ይገኙ በነበሩ ኤርትራውያን ተማሪዎች አማካኝነት ካይሮ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ድርጅት ነው ::
ሆኖም በኢሳያስ አፈወርቅ ሻቢያ ተጠራርጎ እስከ ተደመሰሰበት ጊዜ ድረስ ኤርትራን ለመገንጠል የመጀመሪያው የሽፍታ ቡድን ነበር:’
 በመጨረሻም ሻቢያ ጀብሀን ድምጥማጡ አጠፍቶ የበላይነቱን ወስዶ የትግሉ እንቅስቃሴ ሲያበቃ ፣ ብዙ የጀብሃ ሽፍቶች  ተማረኩ::
  ከነዚህም ምርኮኞች አንዱ ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል ነበሩ ::
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምርኮኞቹ ወደ ምትፈልጉት አገር ሂዱ በማለት ሻዕብያ በነፃ ሲያሰናብታቸው  ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ድርጅታቸው ጀብሀን ድምጥማጡን አጥፍቶ እስቸውን ለምርኮ ካበቃቸው ሻቢያ ጋር ኤርትራ ውስጥ  ለመኖር አስቸጋሪ መስሎ ስለታያቸው  መጠግያ ፍለጋ ወደ ህወሓት ሸራሮ ሄዱው ከወያኔ ጋር ተቀላቀሉ  ።
አቶ ገብረመድህን እንደሚሉት ከሆነ ደብረ ፅዮን እንዴት ወደ ወያኔ እንደተቀላቀሉ  ሚስጥሩን የሚያውቅ የነበረው ተክሉ ሓዋዝ ብቻ ነበረ ::  እሱም ከዚህ ዓለም በሞት ስለተለየ ወያኔ ጋር የተቀላቀሉበትን ሚስጢር በደንብ የሚያውቁት በወቅቱ የወያኔ  ከፍተኛ አመራር የነበሩት  ስብሀት ነጋ አባይ ፀሀየና መለስ ዜናዊ ናቸው  ይላሉ ::
ውድ የፌስ ቡክ ወዳጆቼ  እኔም ወደፊት በማደርገው ጥናት
የትግራዩን የጀብሀ ምርኮኛ የዶክተር ደብረ ፅዮንን  ታሪክ በሰፊው ይዤ እመለሳለሁ ::
ምናልባት   ወደፊት ታሪክ ሁሉንም እስኪገልፀው ድረስ ጊዜን  መጠብቅ የግድ ስለሆነ ለዛሬው በዚሁ አበቃሁ በሌላ ዝግጅት እስክንገናኝ ቸር እንሰንብት  :: ለማንኛውም  ሊንኩን ተጭነው ይህን ቪድዮ ይጋበዙልኝ :: https://m.youtube.com/watch?feature=share&v=_gN2IzVkHGY
Filed in: Amharic