>

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ለተፈናቃይ ወገኖች  እርዳታ ለመስጠት ቢንቀሳቀስም ከመንግስት በወረደ ትእዛዝ ታግተዋል።!

እስክንድን ነጋን ጨምሮ የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች ታሠሩ !!!

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ
 ባልደራስ የግማሽ ሚልዮን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ የምግብ ሸቀጦችን በኮረና ቫይረስ ለተጠቁ፣ ኢኮኖሚ ያዊ መዳቀቅ ለደረሰባቸው፣ እንዲሁም ለተፈናቃይ ወገኖች  እርዳታ ለመስጠት ቢንቀሳቀስም  ከመንግስት በወረደ ቀጭን ትእዛዝ ታግቷል። 
 
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የኮሮና ተህዋሲ እያደረሰ ያለውን ምጣኔ ኃብታዊ ጫና ምክንያት በማድረግ ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የምግብ እህል ለማከፋፈል እየተንቀሳቀሰ ባለበት ወቅት አመራሮቹና አባላቱ ታስረዋል፡፡
 የፓርቲውን ፕሬዚደንት እስክንድር ነጋን ጨምሮ ከ15 በላይ አመራሮችና አባላት በአሁኑ ጊዜ በኮልፌ ቀራኒዮ፤ ካራ ቆሬ ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል፡፡ የእርዳት እህል ጭነው የነበሩት ሁለት አይሱዙ ተሸከርካሪዎችም ከነጭነታቸው በፖሊስ ተወስደዋል፡፡ ጠበቃዎችና ሌሎች አመራሮች ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ፖሊስ ጣቢያው አምርተዋል፡፡አሁን በደረሰን ዜና እነ እስክንድር ተፈተዋል።
Filed in: Amharic